Wednesday 29 April 2015

ማህሌት ፋንታሁን
- ሙሉ ልብሴን እንዳወልቅ ተገድጄ ራቄቴን በወንድ መርማሪዎች ፊት ስፓርት አንድሰራ እገደድ ነበር ፡፡ “ሴትነትሽ አንዲህ ከሚዋረድ አመጽ እንዳነሳሳሽ እመኚ ተብያሁ”
- በሌሊት ግርፋት የሚፈጸምበት ክፍል ውስጥ ገብቼ ጫማሽን አውልቂ ተብዬ ጫማዬን አውልቄ ከቆምኩ በኋላ ውስጥ እግርሽን ከምትገረፊ አመጽ ማነሳሳትሽን አምነሽ ፈርሚ ተብያለሁ፡፡
- ሰጠሁት የተባለው ቃል ሰዎች በሚቀጥለው ክፍል እየተደበደቡ የጩኀት ድምጻቸው እየተሰማ ፈርሚ ተብዬ የተባልኩት ቦታ ላይ ሳላነብ በፍርሃት ፈርሜያለሁ።
- በተለያዬ ምርመራ ወቅቶች "ለነጭ አገሪትዋን የሸጥሽ ሸርሙጣ ውሻ ባንዳ..." አንዲሁም ለመጸፍ የሚከብዱ አፀያፈ ስድቦች በየቀኑ እሰደብ ነበር ፡፡
(*ይህ ጽሁፍ ለኢትዬጲያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከገባው አቤቱታ ተቀንጭቦ የተወሰደ ነው)

No comments:

Post a Comment