Sunday 28 February 2016

ሰበር ዜና) 6 የኦሮሞ ነፃነት ግንባሮች በቅንጅት አንድ ላይ ሊመጡ ነው * 4ቱ ተዋህደዋል

ሰበር ዜና) 6 የኦሮሞ ነፃነት ግንባሮች በቅንጅት አንድ ላይ ሊመጡ ነው * 4ቱ ተዋህደዋል
OLF Army

(ዘ-ሐበሻ) አርበኞች ግንቦት 7 በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የሕወሓትን ሰራዊት የማጥቃቱ ዜና በተጧጧፈበት ወቅት የኦሮሞ ነፃነት ግንባርም በሐረር የሕወሓት የጦር ሰፈር ላይ በከፈተው ጥቃት 28 የሕወሓት ወታደሮችን መግደሉን ትናንት ድርጅቱ መግለጹን ዘ-ሐበሻ ማስነበቧ ይታወሳል:: ዛሬ በደረሰን ሰበር ዜና 6 የተለያዩ ኦሮሞ ነፃነት ግንባር ስም የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ወደ አንድ ላይ በመቀናጀት ለለውጥ መዘጋጀታቸውን ነው::
ለዘ-ሐበሻ የደረሰው ሰበር መረጃ እንደሚያመለክተው
1ኛ. የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (በቦንሳ ሰባ የሚመራው)
2ኛ. የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (በዶ/ር ኑሮ ደደፎ የሚመራው)
3ኛ. የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ጊዜያዊ አባሎች (በአቶ ድሪባ ወርዶፋ የሚመራው)
4ኛ. የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ታጋዮች ቡድን (በአብደታ ሹኬ የሚመራው) ከጁን 27 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በአንድ ላይ በመወሃድ በጋራ መስራት ጀምረዋል:: በቅርብ ቀናት ውስጥም የጀነራል ከማል ገልቹ እና በዳዑድ ኢብሳ የሚመሩት ኦነጎች ወደዚሁ ጥምረት እንደሚያመሩና በቅንጅት ትግሉን ለማጧጧፍ መዘጋጀታቸውን ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ተናግረዋል::
ጁን 27 2015 የተዋሃዱት አራቱ በኦሮሞ ነፃነት ግንባር ስም የሚንቀሳቀሱት ድርጅቶች በአንድ አመራር ስር የሆኑ ሲሆን በጀነራል ከማል ገልቹም ሆነ በኦቦ ዳውድ ኢብሳ የሚመሩት ኦነጎች ይጠቃለላሉ ተብሎ ይጠበቃል::
ትግሉ እጅግ በጣም እየተቀጣጠለ በመጣበት በዚህ ወሳኝ ወቅት ላይ የተከፋፈሉና ትግሉን ወደ ኋላ የሚጎትቱ የኦነግ አመራር አባላት ላይ በውስጥም ሆነ በውጭ ከፍተኛ የሆነ ጫና እያጋጠማቸው መሆኑን ለዘ-ሐበሻ የሚደርሱ መረጃዎች ይጠቁማሉ::
በ6ቱ በኦነግ ስም በሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች መካከል የሚደረገው ውህደትና ጥምረት በወቅቱ መራራ ትግል ላይ ከፍተኛ የሆነ ለውጥ ያመጣል ተብሎ በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እና በየጫካው የሚገኙ ብረት አንስተው በሚታገሉ ወገኖች ዘንድ ተስፋ ተጥሎበታል::በር ዜና) 6 የኦሮሞ ነፃነት ግንባሮች በቅንጅት አንድ ላይ ሊመጡ ነው * 4ቱ ተዋህደዋል
OLF Army
(ዘ-ሐበሻ) አርበኞች ግንቦት 7 በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የሕወሓትን ሰራዊት የማጥቃቱ ዜና በተጧጧፈበት ወቅት የኦሮሞ ነፃነት ግንባርም በሐረር የሕወሓት የጦር ሰፈር ላይ በከፈተው ጥቃት 28 የሕወሓት ወታደሮችን መግደሉን ትናንት ድርጅቱ መግለጹን ዘ-ሐበሻ ማስነበቧ ይታወሳል:: ዛሬ በደረሰን ሰበር ዜና 6 የተለያዩ ኦሮሞ ነፃነት ግንባር ስም የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ወደ አንድ ላይ በመቀናጀት ለለውጥ መዘጋጀታቸውን ነው::
ለዘ-ሐበሻ የደረሰው ሰበር መረጃ እንደሚያመለክተው
1ኛ. የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (በቦንሳ ሰባ የሚመራው)
2ኛ. የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (በዶ/ር ኑሮ ደደፎ የሚመራው)
3ኛ. የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ጊዜያዊ አባሎች (በአቶ ድሪባ ወርዶፋ የሚመራው)
4ኛ. የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ታጋዮች ቡድን (በአብደታ ሹኬ የሚመራው) ከጁን 27 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በአንድ ላይ በመወሃድ በጋራ መስራት ጀምረዋል:: በቅርብ ቀናት ውስጥም የጀነራል ከማል ገልቹ እና በዳዑድ ኢብሳ የሚመሩት ኦነጎች ወደዚሁ ጥምረት እንደሚያመሩና በቅንጅት ትግሉን ለማጧጧፍ መዘጋጀታቸውን ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ተናግረዋል::
ጁን 27 2015 የተዋሃዱት አራቱ በኦሮሞ ነፃነት ግንባር ስም የሚንቀሳቀሱት ድርጅቶች በአንድ አመራር ስር የሆኑ ሲሆን በጀነራል ከማል ገልቹም ሆነ በኦቦ ዳውድ ኢብሳ የሚመሩት ኦነጎች ይጠቃለላሉ ተብሎ ይጠበቃል::
ትግሉ እጅግ በጣም እየተቀጣጠለ በመጣበት በዚህ ወሳኝ ወቅት ላይ የተከፋፈሉና ትግሉን ወደ ኋላ የሚጎትቱ የኦነግ አመራር አባላት ላይ በውስጥም ሆነ በውጭ ከፍተኛ የሆነ ጫና እያጋጠማቸው መሆኑን ለዘ-ሐበሻ የሚደርሱ መረጃዎች ይጠቁማሉ::
በ6ቱ በኦነግ ስም በሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች መካከል የሚደረገው ውህደትና ጥምረት በወቅቱ መራራ ትግል ላይ ከፍተኛ የሆነ ለውጥ ያመጣል ተብሎ በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እና በየጫካው የሚገኙ ብረት አንስተው በሚታገሉ ወገኖች ዘንድ ተስፋ ተጥሎበታል::

Monday 22 February 2016

የቆሰለው አውሬ አገራችንን ይበልጥ ሳያቆስል በጊዜ እንነሳ!

የንቅናቄያችን ሊቀመንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በቅርቡ በዋሽንግተን ዲሲ ተገኝተው ለኢትዮጵያውያን ባደረጉት ንግግር ወያኔ የቆሰለ አውሬ ሆኗል ብለው ነበር። ፕ/ር ብርሃኑ በንግግራቸው፣ የቆሰለ አውሬ በህይወት ለመቆየት ሲል ያለ የሌለውን ሃይል በመጠቀም ጥቃት በሰነዘረበት ግለሰብ ላይ የበቀል እርምጃ ከመውሰድ ወደ ሁዋላ የማይል በመሆኑ፣ ጥቃቱን ለመከላከል በቂ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ አሳስበው ነበር። አውሬነት የጭካኔ ደረጃንና ሁዋላቀርነትን የሚያሳይ ገላጭ ቃል ነው፤ አውሬነት ወያኔ በህዝባችን ላይ ለሚፈጽመው ግፍ ጥሩ ወካይ ቃል ነው፤ ነገር ግን ወያኔ ከአውሬ አልፎ የቆሰለ አውሬ ሆኗል፤ አደገኛነቱም ጨምሯል።

ፕ/ር ብርሃኑ በትክክል እንዳሉት የወያኔ የጥቃት ኢላማዎች ወያኔን የሚታገሉት የነጻነት ሃይሎች ብቻ አይሆኑም። መላው የአገራችን ህዝብ በቆሰለው አውሬ ከመጎዳት አያመልጥም። በነፍስ ግቢና ውጪ መካከል የሚገኘው የቆሰለው አውሬ አፈር ልሶ ከቁስለቱ አገግሞ እንዳይነሳ ጥፋቱን እየተከላከሉ፣ ሞቱ የሚፋጠንበትን መንገድ መቀየስ ከእያንዳንዱ ዜጋ ይጠበቃል። የቆሰለ አውሬ ወዳጅ ጠላት መለየት የማይችል፣ ፊት ለፊት ባገኘው ላይ ሁሉ እርምጃ ለመወሰድ የሚንደፋደፍ በመሆኑ፣ ሁሉም ዜጋ የጥቃት ጥፎሮቹ እሱም ላይ እንደሚያርፉ በመገንዘብ አውሬውን ለማጥፋት መረባረብ ይኖርበታል።

ሰሞኑን በኦሮሚያ አካባቢ እየተቀጣጠለ በመጣው ህዝባዊ እምቢተኝነት ወደ ከርሰ መቃብር እየተገፈተረ መሆኑ የገባውና የቆሰለ አውሬነት ባህሪውን በይፋ ማሳየት የጀመረው ይህ የወያኔ አገዛዝ አጥፍቶ ለመጥፋት አንዱን ሃይማኖት ከሌላው ሃይማኖት፡ አንዱን ብሄር ከሌላው ብሄር በማጋጨት የመፈራገጥ እርምጃውን ተያይዞታል:: ተጨማሪ ጊዜና እድል ከተሰጠውም ሌሎች ከዚህ የከፉ ድርጊቶችንም ሊፈጽም እንደሚችል ልብ ማለት ያሻል። ከዚህ ቀደም በተለያዩ አካባቢዎች በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል ፍንዳታዎችን ሲያካሄድ የነበረ አገዛዝ ወደዚያ ልማዱ ተመልሶ ጉዳት ለማድረስ ወደኋላ የማይመለስ ብቻ ሳይሆን ተሰሚነት አላቸው የሚባሉትን ወይም ከሌላ ብሄረሰብ የሆኑትን በማስገደል በቀል ሊያስነሳ የሚችል ግጭት ሊቀሰቅስ እንደሚችል ይጠበቃል:: በኦሮምያና ተቃውሞ በሚያይልባቸው ሌሎች አካባቢዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ ህዝቡን በርሃብ ከመቅጣትም ወደ ኋላ የመለሳል ብሎ ለማሰብ ይከብዳል:: ማምሻም እድሜ ነው እንደሚባለው ወያኔ ህዝባችንን በማጋጨት እስትንፋሱን ለአንድ ቀን የሚያረዝም እስከመሰለው ድረስ የሚችለውን ሰይጣናዊ መንገዶች ሁሉ ከመሞከር የማይታቀብ ፍጡር መሆኑ ጥርጣሬ ውስጥ የሚገባ አይደለም:: ይህ ሁሉ ሙከራ ከከሸፈበትና እንደማያዋጣው ከተረዳ በዘረፋና በሙስና የሰበሰበውን ሃብትና ንብረት ማሸሹን አጠናክሮ ይገፋበታል።

አርበኞች ግንቦት7 በ11ኛው ሰአት የሚገኘውን የቆሰለውን አውሬ ጥፋት ለመቀነስም ሆነ ግብዓተ መሬቱን ለማፋጠን ፣ በወታደራዊው እና በህዝባዊ እምቢተኝነቱ መስኮች ተግቶ እየሰራ ነው። ንቅናቄው ሁኔታዎችን ሁሉ አጥንቶ ተስማሚ ሆኖ ባገኘበት ሰዓት በቆሰለው አውሬ ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ ለኢትዮጵያ ህዝብ በተደጋጋሚ ገልጿል። ንቅናቄያችን አገራችንን ከቆሰለው አውሬ ቁጥጥር ሙሉ በሙሉ ካላቀቀ በሁዋላ፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በጋራ መክሮና ዘክሮ የሚገነባት የነጻነትና የእኩልነት አገር እንዲኖረን ለማስቻል አቅም የፈቀደለትን ሁሉ ከማድረግ ለአፍታም ቢሆን ወደ ኋላ እንደማይል ፣ የንቅናቄው ሊቀመንበር እና የመላው አባላቱ ተወካዮች በቅርቡ ባካሄዱዋቸው ጉባኤዎች በድጋሜ አረጋግጠዋል።

በአገር ቤትና በውጪ የሚኖረው ህዝባችንም በበኩሉ ይህ የቆሰለ አውሬ የሚወስዳቸውን እርምጃዎች ለማክሸፍ ከዚህ የሚከተሉትን እርምጃዎች እንደአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ መውሰድ ይኖርበታል።

1ኛ. በየቀኑ የሚካሄዱ ህዝባዊ እንቅስቃሴዎችን ትኩረት ሰጥቶ መከታተልና መረጃ መሰብሰብ:: ያገኛቸውንም መረጃዎች ወዲያውኑ ለመገናኛ ብዙሃን ማቀበል

2ኛ. የቆሰለው አውሬ አንዱን ሃይማኖት ከሌላው ሃይማኖት፣ አንዱን ብሄር ከሌላው ብሄር ለማጋጨት የሚያደርገውን ጥረት ማክሸፍንና ፣ ማጋለጥ።

3ኛ. ለዚህ እኩይ ስራ የሚሰለፉ ሃይሎችን ማስጠንቀቅ፣ ማጋለጥና እንደ አስፈላጊነቱ ተመጣጣኝ እርምጃ መውሰድ።

4ኛ. በየአካባቢው የተቀሰቀሱ ተቃውሞዎችን ትንሽ ትልቅ ሳይባል መቀላቀል። በተለይ የወያኔ የነርቭ ማእከል ናቸው በሚባሉት ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰድ።

5ኛ. የወያኔን አገዛዝ ለመለወጥ በትግል ላይ ያሉ ድርጅቶችን በማቴሪያል፣ በገንዘብና በማንኛውም ነገር መርዳት።

6ኛ. በሁለገብ ትግሉ እየተሳተፉ ያሉ ሃይሎችን በአካል መቀላቀል፣ ካልተቻለም መረጃ በማቀበል ማገዝ።

7ኛ. ወያኔ በመካከላችን የዘረጋውን የልዩነት አጥር በማፍረስ ጥርጣሬና አለመተማመን እንዳይኖር ማድረግ፡ እያንዳንዱ ለሁሉም ሁሉም ለያንዳንዱ ወገናዊነቱን መግለጽ፤ የጎንዮሽ ሽኩቻዎችን ማቆምና የፖለቲካ መስመር ልዩነቶቻችንን ለማጥበብ ዝግጁ መሆን።

8ኛ. የእርስ በርስ ትብብርን ማጠናከር አንዱ ሲጎዳ ሌላው እያከመ፣ ሁሉም ተቃውሞውን በየአቅጣጫው መጀመር።

አርበኞች ግንቦት7 እንደቆሰለ አውሬ መፈራገጥ የጀመረው የወያኔ አገዛዝ በአገራችንና በህዝባችን ላይ ሊያደርስ የሚችለው አደጋ እንዲቀንስና ድህሬ ወያኔ የህዝቦቿን አንድነት በእኩልነት የምታረጋግጥ የተረጋጋች ፣ ሰላምና ብልጽግና የሰፈነባት አገር ለመመሥረት ከሚሹ የአገሪቱ ልጆች ሁሉ ጋር እጅ ለእጅ በመያያዝ የነጻነት ቀን እንደሚያቃርብ እርግጠኛ ነው ።

የወያኔን የሥልጣን እድሜ ለማሳጠር ሁላችንም ለተግባራዊ ትግል ዛሬውኑ ታጥቀን በቆራጥነት እንነሳ!

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !
አርበኞች ግንቦት7

የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ጎንደር ውስጥ በህወሓት ከአቅሙ በላይ የታጠቀ ጥምር ኃይል ላይ ጥቃት ፈፅሞ ከባድ ጉዳት አደረሰ፡፡

የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ጎንደር ውስጥ በህወሓት ከአቅሙ በላይ የታጠቀ ጥምር ኃይል ላይ ጥቃት ፈፅሞ ከባድ ጉዳት አደረሰ፡፡

የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሰራዊት በጎንደር ታች አርማጭሆ ሳንጃ ዶጋው የተባለ ቦታ ውስጥ ይንቀሳቀስ በነበረው እና ከመከላከያ፣ ከልዩ ኃይል፣ ከፀረ-ሽምቅ እና ከሚሊሻ ጦር ተውጣጥቶ በልዩ ሁኔታ የተደራጀ የህወሓት ኃይል ላይ የካቲት 10 2008 ዓ.ም ከቀኑ 5 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት በከፈተው ድንገተኛ ጥቃት ከፍተኛ ድልን ተቀዳጅቷል፡፡

የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በጥምሩ የህወሓት ኃይል ላይ ድንገተኝነትን በማትረፍ ጠንካራ ምት አሳርፎ 35 ገድሎ 52 በማቁሰል እንዳልነበረ በማድረግ በታትኖታል፡፡
(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)

በአዲስ አበባ የዶ/ር መረራ ጉዲና ፓርቲ ቢሮ በወታደራዊ ኮማንዶዎች ተከቦ እየተፈተሸ ነው።

በመላው ኦሮሚያ ክልል እየተደረገ ያለው ሕዝባዊ ተቃውሞ ከቀን ወደቀን ጨምሮ ባለበት በዚህ ሰዓት በአዲስአበባ የሚገኘው እና በዶክተር መረራ ጉዲና ሊቀመንበርነት የሚመራው የኦሮሚያ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ቢሮ በወታደራዊ ኮማንዶዎች ተከቦ እየተበረበረ ነው።
የጽ/ቤቱን ሃላፊ ጨምሮ የቢሮ ሰራተኞች እንዲሁም በቢሮ ውስጥ የነበሩ አባላት በመንግስት ኮማንዶዎች ቁጥጥር ስር ውለዋል::የተያዙት አባላት ከፍተኛ ድብደባ እና መጉላላት እየተደረገባቸው መሆኑን በአካባቢው ላይ የሚገኙ የአይን እማኞች ገልጸዋል::የድርጅቱ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና በቢሮ ውስጥ እንዳልነበሩ የሚገልጹት ምንጮች ሁኔታው አስፈሪ ነው ይላሉ::
የኢትዮጵያ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅ/ቤት ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸው ረዳ ከአንድ ቀን በፊት ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ “የኦሮሚያ ፌዴራሊስት ኮንግረስ አባላትን ሁሉ አላሰርንም።በቁጥጥር ሰር ያዋልናቸው ጥቂቶች ናቸው።በሰላማዊ መንገድ እየተንቀሳቀሱ ያሉትን አልነካንም “ባሉ ማግስት የተፈጸመው ድርጊት ስርዓቱ ወዴት እየሄደ ነው ብዙዎች ይላሉ።

Thursday 18 February 2016

እነ ሳሙኤል ግደይ የሞትና የእድሜ ልክ እስራት ተበየነባቸው

   #የህወሓትን አገዛዝ በመቃወም ኤም.አይ-35 ሄሊኮፕተር ይዘው ከሀገር የወጡት እነ ሳሙኤል ግደይ የሞትና የእድሜ ልክ እስራት ተበየነባቸው፡፡
 
   ሳሙኤል ግደይ፣ ፀጋ ዘአብ ግደይ እና ቢልልኝ መኮንን የህወሓትን አገዛዝ በመቃወም ኤም.አይ-35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር በማብረር ከምስራቅ አየር ምድብ ድሬዳዋ በውሎ የጠፉት በ2007 ዓ.ም ሲሆን የህወሓት አገዛዝ የጦር ፍርድ ቤት የካቲት 4 2008 ዓ.ም በሌሉበት በሞትና እድሜ ልክ እስራት ቀጥቷቸዋል፡፡
 
የሄሊኮፕተሯ ዋና አብራሪ ሳሙኤል ግደይ በሞት ሲቀጣ ፀጋ ዘአብ ግደይ እና ቢልልኝ መኮንን የእድሜ ልክ እስራት ተበይኖባቸዋል፡፡
  ከእነ ሳሙኤል ግደይ በፊትም በ1993 ዓ.ም ካፒቴን ተሾመ ተንኮሉ ኤል-39 ተዋጊ ጀት እያበረረ ከመቀሌ ተነስቶ ኤርትራ መግባቱ፤ መቶ አለቃ በኃይሉ ገብሬ እና መቶ አለቃ አብዮት ማንጉዳይ ኤም.አይ-35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር እያበረሩ ጅቡቲ ማረፋቸው  የሚታወስ ነው፡፡ መቶ አለቃ በኃይሉ ገብሬና አብዮት ማንጉዳይ በጅቡቲ መንግስት ለህወሓት ተላልፈው ተሰጥተው የእድሜ ልክ እስራት እና የ15 አመት እስር ተፈርዶባቸው መቶ አለቃ አብዮት የእስር ጊዜውን ጨርሶ በመፈታቱ በአሁኑ ጊዜ አርበኞች ግንቦት 7ን ተቀላቅሎ ኤርትራ በረሃ እንደሚገኝ መዘገባችን አይዘነጋም፡፡
 
የኤም.አይ-35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር አዛዥ እና የበረራ አሰተማሪ የነበረው ሻለቃ አክሊሉ መዘነም ከአመታት በፊት ስርዓቱን በመቃወም ወደ ኤርትራ መጥቶ አርበኞች ግንቦት 7ን በመቀላቀል ትግል ላይ ይገኛል፡፡

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ

Tuesday 16 February 2016

የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ተገኔ ጌታነህ ከአገሪቱ ብልሹና ጣልቃገብ አሰራር የፍትህ ስርኣት ራሳቸውን አገለሉ

በሕወሓት የፍትህ ስርኣት ደስተኛ ያልሆኑት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ተገኔ ጌታነህ ስራቸውን በፈቃዳቸው ከስራቸው የለቀቁ መሆኑን ፎርቹን ጋዜጣ ገልጿል::የጠቅላይ ፍ/ቤቱ ፕሬዝዳንቱ ከሳምንት በፊት መልቀቂያ ደብዳቤ ያስገቡ መሆኑ የታወቀ ሲሆን የመልቀቂያቸው ምክንያት ከጤና ጋር የተያያዘ መሆኑን በደብዳቤያቸው አስፍረዋል። ይህ ቢሆንም ፕሬዝዳንቱ በጤንነት ያሳቡ እንጂ በሕወሓት የፍትህ ስርዓት ውስጥ ባለው ብልሹ እና ጣልቃገብ አሰራር ደስተኛ እንዳልነበሩ የሚያውቋቸው ተናግረዋል።በዚህ ሳምንት ሕገመንግስቱ ይከበር ሕወሓት ከዳኝነት ስራ እጁን ያውጣ ያሉ ከዳኝነት ስራቸው መባረራቸው ይታወሳል:: ‪‎


Saturday 13 February 2016

የህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣናትና የአማራ ክልል ሹሞች በጎንደር ጎሃ ሄቴል ለሦስት ተከታታይ ቀናት ያደረጉት ድብቅ ስብሰባ ያለምንም ውጤት በፀብ ብቻ ተቋጨ፡፡

የህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣናትና የአማራ ክልል ሹሞች በጎንደር ጎሃ ሄቴል ለሦስት ተከታታይ ቀናት ያደረጉት ድብቅ ስብሰባ ያለምንም ውጤት በፀብ ብቻ ተቋጨ፡፡ በህወሓቶችና በብአዴኖች መካከል የተካረረ ፍጥጫና ንትርክ ተከስቶ የነበረ መሆኑም ተደርሶበታል፡፡

በጎንደር ከተማ ጎሃ ሆቴል ውስጥ ከጥር 28 እስከ የካቲት 1 2008 ዓ.ም በድብቅ በተካሄደው ስብሰባ ላይ የተገኙት የህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣናት አባይ ፀሐዬ፣ ስብሃት ነጋ፣ ደብረ ፂዮን ገ/ሚካኤል፣ አባይ ወልዱ እና የትግራይ ክልል አስተዳደርና ፀጥታ ሹም ናቸው፡፡
ገዱ አንዳርጋቸው፣ አለምነው መኮንን እና መኳንንት /የአማራ ክልል ፀጥታ ሹም/ ደግሞ ከብአዴን ወገን የተገኙ የአማራ ክልል ሹማምንቶች ነበሩ፡፡
የህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣናትና የህወሓት ዲቃላ የሆነው ብአዴን ባለስልጣናት በጎንደር ጎሃ ሆቴል ተሰብስበው የተነታረኩባቸው አጀንዳዎች ሁለት ሲሆኑ የወልቃይትን የአማራ ማንነት ጥያቄ እና ብረት ያነሱ የነፃነት ድርጅቶችን /በተለይም አርበኞች ግንቦት 7ን/ በሚመለከት ነው፡፡
የትጥቅ ትግል እያደረጉ የሚገኙ የነፃነት ድርጅቶችን በሚመለከት ህወሓቶች "ሰተት ብለው ከበረሃ ወደ ህዝቡ እንዲገቡ እያደረጋችኋቸው ነው..." በማለት ብአዴኖችን ወቅሰዋቸዋል፡፡
ከወልቃይት ህዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ደግሞ የትግራይ ክልል አስተዳዳሪና የህወሓት ሊቀ መንበር የሆነው አባይ ወልዱ እንዲህ ብሏል፡፡
"ወልቃይት የትግራይ ነው! የአማራነት ጥያቄው በዚህ የማያቆምና ተጠናክሮ የሚቀጥል ከሆነ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን...!"
ቀጥሎም አባይ ወልዱ የአማራ ክልልን አስተዳዳሪ ገዱ አንዳርጋቸውን
"አንተ የአማራን ህዝብ የጦር መሳሪያ ያስታጠከው ሆነ ብለህ በትግራይ ላይ ጦርነት ለማወጅ ነው..." በማለት ተናግሮታል፡፡
ገዱ አንዳርጋቸውም በበኩሉ
"እኔ ህዝቡ በሀብቱ ገዝቶ ከጥንት ጀምሮ ታጥቆት የቆየውን ጦር መሳሪያ ህጋዊ ፈቃድ በመስጠት አፀናሁለት እንጂ ልክ እንዳንተ ከመንግስት ግምጃ ቤት አውጥቼ በገፍ አላስታጠቁትም፡፡ በትግራይ ህዝብ ላይ ጦርነት አወጅክ ላልከኝም የትግራይን ህዝብ ሰብስበህ በወልቃይት ህዝብ ላይ እርምጃ እንወስዳለን ብለህ በይፋ ጦርነት ያወጅከው አንተ ነህ፡፡" በማለት ለአባይ ወልዱ መልስ ሰጥቶታል፡፡
የጦር መሳሪያን በሚመለከት ደብረ ፂዮን ገ/ሚካኤል ገዱ አንዳርጋቸው የአማራን ህዝብ እንዳስታጠቀ ወቀሳ ሰንዝሯል፡፡ ደብረ ፂዮን ስለ ወልቃይት ህዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ የሚከተለውን በማለት ቁልጭ ያለ አቋሙን አስቀምጧል፡፡
"የወልቃይት ጉዳይ ክልል አንድን እንጂ ማንንም አይመለከተውም፤ ውሳኔውም ሊሆን የሚችለው የክልል አንድ ብቻና ብቻ ነው፡፡"
ለዚህ የደብረ ፂዮን ንግግር ገዱ አንዳርጋቸው ሲመልስ
"እኛ ሄደን ኑ አንላቸውም፤ ከመጡ ግን የማንቀበልበት ምንም ምክንያት የለም፤ ደግሞም ውሳኔ ማስቀመጥ ያለበት ራሱ የወልቃይት ህዝብ ነው፡፡"
በመሆኑም በሁለቱ ክልሎች /በትግራይና አማራ/ አስተዳዳሪዎች ማለትም በአባይ ወልዱና ገዱ አንዳርጋቸው መካከል ስብሰባው ውስጥ የተካረረ ፍጥጫ ተከስቶ ነበር፡፡
ህወሓቶች ለገዱ አንዳርጋቸው ከባድ ማስጠንቀቂያ ሰጥተውታል፡፡
በአጠቃላይ በጎንደር ጎሃ ሆቴል ከጥር 28 እስከ የካቲት 1 2008 ዓ.ም በድብቅ የተካሄደው የህወሓቶችና የብአዴኖች ውይይት ያለምንም መግባባት በፀብ ብቻ ተጠናቋል፡፡

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ

Thursday 11 February 2016

የሱዳን መንግስት የኢትዮጵያ ድንበር በርካታ ኪሎሜትሮች በመግፋት ኣዲስ የኢሚግሬሽን ህንፃ በልጉዲ ከተማ ገንብተዋል

ኣዲስ የኢሚግሬሽን ህንፃ በልጉዲ ከተማ ገንብተዋል።

ሱዳን በኣቶ መለስ የተሰጣት መሬት ለመረከብ ሽርጉድ እያለች ትገኛለች።

በ2002 ዓ/ም ሃገራቀፍ ምርጫ ወቅት ኣቶ ስዬ ኣብራሃ በኢትዮ_ሱዳን ድንበር ከ35_65 ኪ/ሜ የሚሸፍን የኢትዮጵያ ቆዳ መሬት ለሱዳን ለመስጠት ተደራድረው እንደጨረሱ ኣጋልጠው ነበር።

በዚህ መሰረት እንደ መተማ ዮውሃንስ፣ ቋራ፣ ልጉዲና ሌሎች ለም መሬቶች ለሱዳን ሊሰጡ በሁለቱ መንግስታት ዝግጅት መጠናቀቁ እየተገለፀ ነው።

በወቅቱ የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን ለማስረከብ ሁለቱ መንግስታት ከ17 ግዜ በላይ በድብቅ እየተደራደሩ የነበሩ ሲሆን የዚህ ድንበር ውጤትም ሱዳን በሑመራ በኩል ከነበረው ባህረሰላም የሚባለው የኢትዮጵያ ድንበር በርካታ ኪሎሜትሮች ወደ ኢትዮጵያ በመግፋት ልጉዲ በተባለው የድንበር ከተማ ኣድርገው በመትከል የሱዳን የኢሚግሬሽን ፅሕፈት ቤት ( Passports Office )ኣዲስ ህንፃ ገንብተዋል።

የሱዳን መንግስት በኢትዮጵያ መንግስት ለቀረበለት ገፀ በረከት ለመረከብ ከታች በምስሉ የምትመለከቱት ኣዲስ ህንፃ በልጉዲ ከተማ ገንብተዋል።

*መንግስት እነ ሃፀይ ዮውሃንስ ደማቸው ያፈሰሱበት፣ እነ ሃፀይ ቴድሮስ የተወለዱበት የኢትዮጵያ ሉኣላዊ መሬት ቆርሶ ለባእድ ኣገር መለገሱ ያቁም…!

*መንግስት ስለ በሁለቱ መንግስታት እየተካሄደ ያለው ድርድር ለህዝብ በይፋ ይግለፅ…!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር።
Mereja

Tuesday 9 February 2016

በኢትዮጵያ የጸጥታ ሁኔታ አላስተማመነም

ጎልጉል

በኢትዮጵያ የጸጥታ ሁኔታ አላስተማመነም የዕርዳታ ሠራተኞች ወደ መስክ እንዳይወጡ ተከለከሉ

በኢትዮጵያ ያለው የጸጥታና ደኅንነት ሁኔታ አስተማማኝ ሁኔታ ላይ አለመሆኑ ተነገረ፡፡ የዕርዳታ ድርጅት ሠራተኞች ወደ መስክ የሚያደርጉት የሥራ ጉብኝት ተከለከለ፤ የፕሮጀክት ሥራዎች ሊደናቀፉ እንደሚችሉ ተገምቷል፡፡

በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ያለው የጸጥታ ሁኔታ አስቸጋሪ ደረጃ ላይ በመድረሱ ኢህአዴግ የዕርዳታ ድርጅት ሠራተኞችን ወደተወሰኑ የአገሪቱ ክፍሎች እንዳይንቀሳቀሱ ማስጠንቀቂያ የሰጣቸው መሆኑን መረጃው የደረሳቸው ለጎልጉል አስታውቀዋል፡፡

በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ በተለይ የአማራ ክልልና በምዕራብ ደግሞ የጋምቤላ ክልል አካባቢ ያለው ውጥረት እጅግ እያየለ በመምጣቱ በቦታዎቹ ላይ የሚንቀሳቀሱ የዕርዳታ ድርጅት ሠራተኞች ሊደርስባቸው ስለሚችል ጉዳት ተጠያቂ እንደማይሆን ኢህአዴግ በሰጠው ማሳሰቢያ አስታውቋል፡፡

ማስጠንቀቂያ ከተሰጣቸው የዕርዳታ ድርጅቶች መካከል የካቶሊክ ዕርዳታ አገልግሎት አንዱ ሲሆን በውሳኔው ምክንያት ድርጅቱ በተለይ በጋምቤላ የሚያከናውነው ፕሮጀክት ችግር ላይ እንደሚወድቅ ተነግሯል፡፡

ኢህአዴግ ማስጠንቀቂያውን ካስተላለፈ በኋላ በተዋረድ ከአለቆቻቸው ትዕዛዝ የተሰጣቸው ሠራተኞች ወደ ተጠቀሱት ቦታዎች እንዳይሄዱ መከልከላቸውን የዜናው አቀባዮች ለጎልጉል አስታውቀዋል፡፡

በኢትዮጵያ እያየለ የመጣው ሕዝባዊ ተቃውሞና እምቢተኝነት ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ መምጣቱ በገሃድ የሚታይ ሆኗል፡፡ በተለይ የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ተከትሎ የተነሳው ተቃውሞ ለወራት መቀጠሉ በአገዛዙ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ማምጣቱ ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚሰሙት መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚታየው የጸጥታ መደፍረስ በኢንቨስትመንት፣ በቱሪዝም፣ እና በሌሎች ክፍለኢኮኖሚዎች ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ቀላል እንደማይሆን ባለሙያዎች አሳማኝ ግምቶች ይሰጣሉ፡፡

ህወሃት እንደ ጭቃ ጠፍጥፎ የሠራቸው የአማራውና የኦሮሞው ድርጅት አባሎች ለአንድ ብሔር የበላይነት አንገዛም የሚሉ ጥያቄዎች እያነሱ መምጣታቸው በመለስ አዝማችነት ህወሃት ሁሉ ቦታ ከለኮሰው የዘር እሣት ጋር ተዳምሮ የአገሪቱ መጻዒ ዕድል የሚያሳስባቸው ወገኖች ሁኔታው መላ ሊፈለግለት ያሻዋል ይላሉ፡ 

Friday 5 February 2016

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የምስክርነት ቃሉን ሰጠ

"የህሊና እስረኛ ነኝ" እስክንድር ነጋ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

በሽብርተኝነት ወንጀል ጥፋተኛ ተብሎ 18 አመት እስር ተፈርዶበት በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የመከላከያ ምስክርነት ቃሉን ሰጥቷል፡፡

Eskinder Nega and Zelalem
ከግራ ወደ ቀኝ፡ እስክንድር ነጋ እና ዘላለም ወርቃገኘሁ
በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ አንደኛ ተከሳሽ ለሆነው አቶ ዘላለም ወርቃገኘሁ መከላከያ ምስክር ሆኖ ልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ከእስር ቤት የቀረበው ጋዜጠኛ እስክንድር ዛሬ ጥር 27/2008 ዓ.ም ምስክርነቱን ሊያሰማ ችሏል፡፡

ያለጠበቃ በግሉ የሚከራከረው ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ ጋዜጠኛ እስክንድር እንዲያስረዳለት የሚፈልገው ጭብጥ ጡመራ ምንድነው፣ ከወንጀል ጋርስ ግንኙነት አለው ወይ፣ እና ሰብዓዊ መብት እና ዴሞክራሲ ላይ ስልጠና ስለሚሰጡ ድርጅቶችና የስልጠናው ይዘትን በተመለከተ እንደሆነ ቢያስታውቅም በጭብጡ ላይ አቃቤ ህግ ተቃውሞውን አሰምቷል፡፡ በዚህም አቃቤ ህግ ጡመራ ምንድነው፣ ወንጀልስ ነው ወይ የሚለው በምስክር ሳይሆን በህግ ድንጋጌዎች የሚረጋገጥ እንደሆነ በመግለጽ ተቃውሟል፡፡ ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን ከሰማ በኋላ ጡመራ ወንጀል ስለመሆን አለመሆኑ የተያዘውን ጭብጥ ውድቅ በማድረግ ስለ ስልጠናውና አሰልጣኝ ተቋማት የተመዘገበው ጭብጥ ላይ ምስክሩ እንዲመሰክሩ ብይን ሰጥቷል፡፡

ብይኑን ተከትሎ ምስክሩ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ችሎት ፊት የቀረበ ሲሆን በመጀመሪያ በፍርድ ቤቱ የቀረቡለትን ጥያቄዎች መልሷል፡፡ ምስክሩ ሙሉ ስሙን፣ እድሜውን፣ ስራውንና ለምን እንደመጣ፣ እንዲሁም ከተከሳሾች ጋር ስለመተዋወቁ ለቀረቡለት ጥያቄዎች መልስ ሰጥቷል፡፡ እስክንድር ‹‹ስራ›› ተብሎ ሲጠየቅ፣ ‹‹ጋዜጠኛ ነበርኩ›› ብሏል፡፡ ‹‹አሁንስ›› የሚል ጥያቄ ፍርድ ቤቱ አቅርቦለት፣ ‹‹አሁን የህሊና እስረኛ ነኝ›› ሲል መልሷል፡፡

ተከሳሹ ዘላለም ወርቃገኘሁ በዋና ጥያቄ ተከሳሹ ውጭ ሀገር ሊወስደው ነበር ተብሎ በክሱ ላይ ስለተጠቀሰው ስልጠና ምስክሩ እንዲያብራሩለት ጠይቋል፡፡ ምስክሩም ‹‹ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ሀገራትንም የሚያሳትፍ ስልጠና በሰብዓዊ መብት፣ በሚዲያ ‹ኢቲክስ›፣ እና በዴሞክራሲ ላይ ይሰጣሉ፡፡ ድርጅቶቹ የተለያዩ ቢሆንም በሰብዓዊ መብት ጉዳይ ላይ መርሃቸው ተመሳሳይና ዓለም አቀፍ ነው›› በማለት መስክሯል፡፡

ድርጅቶቹን በስም መጥቀስና የሚገኙበትንም ሀገር ለፍርድ ቤቱ መግልጽ ይቻል እንደሆነ ምስክሩ ተጠይቆ ‹‹የተቋማቱ መገኛ ምዕራቡ ዓለም ነው፡፡ በዴሞክራሲ የዳበሩ ሀገራት ነው ዋና መቀመጫቸው፡፡ ሲ.ፒጄ፣ ፍሪደም ሀውስ፣ አምንስቲ ኢንተርናሽናል እና አርቲክል 19 የመሳሰሉትንም በስም መጥቀስ ይቻላል፡፡ እኔም ከነዚህ ተቋምት ውስጥ በአንዱ የተሰጠ ስልጠና አዲስ አበባ ላይ ተካፍየ ነበር፡፡ ስልጠናው ስለ ሰብዓዊ መብት፣ ስለ ሚዲያ፣ ስለ ዴሞክራሲ የሚያስተምር ነው፡፡ ስልጠናው ከሽብር ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፤ ይህ እንደማስረጃ መቅረቡ ኢትዮጵያን ትዝብት ውስጥ የሚከትና የሚያሳዝን ነው›› ሲል ምስክርነቱን ሰጥቷል፡፡

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ መቼ እንደታሰረ በመስቀለኛ ጥያቄ ተጠይቆ ‹‹መስከረም 2004 የሀሰት ክስ ቀርቦብኝ፣ በግፍ ተፈርዶብኝ ታስሬ እገኛለሁ›› ሲል መልሷል፡፡ እስክንድር ነጋ ጥቁር ሱፍ በደብዛዛ ሸሚዝ ለብሶ፣ ሙሉ ጥቁር መነጸር አድርጎና ነጠላ ጫማ ተጫምቶ ችሎት ፊት ቀርቧል፡፡

አንደኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ ምስክሩ ምስክርነቱን ማጠቃለሉን ተከትሎ በመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡለት የጠራቸው ሌላኛው ምስክር አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በተደጋጋሚ እንዲቀርቡለት ትዕዛዝ እንዲሰጥለት የጠየቀ ቢሆንም እስካሁን አለመቅረባቸው መንግስት ግለሰቡን ለማቅረብ ፍላጎት እንደሌለው ያሳያል ሲል ቅሬታውን አሰምቷል፡፡ ‹‹አሁን የተረዳሁት ነገር ከሳሼ የሆነው መንግስት አቶ አንዳርጋቸውን ከሚያቀርብ እኔን በነጻ መልቀቅ እንደሚቀለው ነው›› ብሏል ተከሳሹ፡፡

ተከሳሹ ከአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጋር በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች እንደተገናኜ አቃቤ ህግ መጥቀሱን በማስታወስ ምስክሩ መቅረባቸው ያለውን ተገቢነት አስረድቷል፡፡ ‹‹ምስክሩ እንዲቀርቡልኝ እፈልጋለሁ፡፡ ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ፍርድ ቤቱ ከምስክሩ ጋር በተገናኘ ያለውን የክሱ ፍሬ ነገር አውጥቶ በቀሪው ላይ ብይን ይስጥልኝ›› ብሏል ተከሳሹ አቶ ዘላለም፡፡

ፍርድ ቤቱም ምስክሩ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲቀርቡ ትዕዛዝ በመስጠት ምስክርነታቸውን ለመስማት በሚል ለየካቲት 16/2008 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
Ecadf

ሰሞኑን በጋምቤላ በደረሰው የእርስበርስ ፍልሚያ እስከመቶ የሚጠጉ መሞታቸውን የክልሉ ነዋሪዎች ተናገሩ

“የሟቾች ቁጥር እስከ መቶ ሊደርስ ይችላል” ነዋሪዎች
* “የሞቱት 14 ሰዎች ናቸው” ኢህአዴግ

ከጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

ሰሞኑን በጋምቤላ በደረሰው የእርስበርስ ፍልሚያ እስከመቶ የሚጠጉ መሞታቸውን የክልሉ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ ኢህአዴግ በበኩሉ የሞቱት 14 ብቻ ናቸው ይላል፡፡ ዘረኝነትንና ጠባብ ጎሰኝነትን ለኢትዮጵያ እንደ “ገጸ በረከት” ያመጡት መለስ በየቦታው የጫሩት እሣት ለፍርድ ሳያቀርባቸው ሾልከዋል፡፡ እሣቱ ግን አሁንም እየነደደ ነው፡፡

ጎልጉል ከአካባቢው ነዋሪዎችና ጉዳዩን በቅርብ ሲከታተሉ ባገኘው መረጃ መሠረት በግጭቱ የሞቱት እስከ መቶ እንደሚደርስ ይነገራል፡፡ ግጭቱ ከመነሻው በቀላሉ የተነሣ ቢሆንም ወዲያውኑ ወደከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ ሥር የሰደደ ፖለቲካዊ ምክንያት እንዳለው ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡ ይህንኑ ዜና ኢሳት ሲዘግብ የሟቾቹ ቁጥር ከመቶ እንደሚያልፍ ምንጮቹን ጥቅሶ አስታውቋል፡፡

ጸረ ቁጥር የሆነው ኢህአዴግ ወራትን ባስቆጠረው የተማሪዎች ዓመጽ ከሁለት መቶ በላይ ሞተው ሟቾች ከአስር ያልበለጡ ናቸው ከማለቱ በፊት መጀመሪያ ምንም የሞተ የለም፤ ቀጥሎም የሞቱት አምስት ናቸው ማለቱ ይታወሳል፡፡ አሁን ደግሞ የኢህአዴግ አፈቀላጤ ጌታቸው ረዳ በጋምቤላው ግጭት የሞቱት ቁጥሩን እርግጠኛ ለማስመሰል ይመስላል 14 ናቸው ብለዋል፡፡

አቶ መለስ በአዛዥነት ከሌሎች የህወሃት ሹማምንት ጋር በመሆን በሰጡት ቀጥተኛ ትዕዛዝ 424 የአኙዋክ ጎሣ አባላት በግፍ መጨፍጨፋቸው ይታወሳል፡፡ በወቅቱ የጭፍጨፋው አስፈጻሚ የነበሩት እና ኢህአዴግን ከድተው በውጪ አገር የሚገኙት የቀድሞው የክልሉ ኃላፊ ኦሞት ኦባንግ ኦሉም ከህወሃት ጋር ሆነው የተከሉት መርዝ ለሰሞኑ ግጭት መባባስ ምክንያት እንደሆነ ጉዳዩን የሚከታተሉ ወገኖች ይናገራሉ፡፡

በትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) የዘር ጭፍጨፋ ከተካሄደባቸው በኋላ መሬታቸውን በግፍ ከተነጠቁት አኙዋክ ወገኖች መካከል ከዘር ማጥፋቱ ያመለጡት በበርካታ ሺዎች የሚቆጠሩት አገር ለቅቀው ተሰደዋል፡፡ በዓለምአቀፍ ድርጅቶች ዘንድ በቁጥር ደረጃ ለመጥፋት የተቃረቡ ከሚባሉት አኙዋኮች በህይወት የቀሩት ደግሞ አሁን ለዘር እንዳይቀሩ ሆነው እየተጨፈጨፉ ይገኛሉ፡፡ የአሁኑን ለየት የሚያደርገው ግጭቱ እርስበርስ መሆኑ ነው፡፡

ከዚህ ሌላ ህወሃት ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ጋር ያለው “የጫጉላ ጊዜ” በማብቃቱ ለተቀናቃኛቸው ሬክ መቻር ግልጽ ድጋፍ እየሰጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከዚህ አኳያ የኑዌር ተወላጅ የሆኑት ሬክ መቻር ወደ ጋምቤላ እንደፈለጉ ሲወጡና ሲገቡ መክረማቸውን ጎልጉል ከዚህ በፊት ዘግቦ ነበር፡፡ የመቻርን ኃይል ለመደገፍ ከጋምቤላ በርካታ ኑዌሮች ወደ ደቡብ ሱዳን ገብተው ከሳልቫ ኪር የዴንቃ አባላት ጋር ጦርነት መጋጠማቸውና ከሞቱት መካከልም “የመከላከያ ሠራዊት” አባላት ለመሆናቸው ማስረጃ ስለመገኘቱ ጉልጉል በተደጋጋሚ መረጃ ደርሶታል፡፡

አሁን በተከሰተው ግጭት ቀድሞውኑም የታጠቁት የኑዌር አባላት አሁን ደግሞ ከደቡብ ሱዳን ግጭት ጋር በተያያዘ የመቻር ኃይል ያስታጠቃቸው ድንበር እያለፉ በመዝለቅ በአኙዋኮች ላይ የሚያደርሱት ጥቃት አሁንም አልቆመም፡፡ የአኙዋክ ጎሣ አባላትም ራስን ከመከላከል ጀምሮ መልሶ እስከ ማጥቃት በሚያደርጉት ምት በገጠር ቀበሌዎች የሚገደሉት ንጹሃን ቁጥር እጅግ እየጨመረ መሄዱ ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ለጎልጉል አስታውቀዋል፡፡
“ኢትዮጵያውያንን እንደ እህል በዘር ከረጢት እየሠፈረ ለዚህ ሁሉ ዓይነት ስቃይና መከራ እንዲሁም ለማያባራ የዘር ግጭት የዳረገው መለስ ነው፤ ወደ ህይወት ማምጣት ብችል አስመጥቼ ፍትህ እንዲበየን ማስደረግ እፈልግ ነበር፤ ሙት አይወቀስም ይባላል፤ ልክ ሊሆን ይችላል አባባሉ ግን ለመለስ አይሠራም፤ እኔ ፍትህ የጠማኝ ነኝ” በማለት የመረረ አስተያየቱን ለጎልጉል በውስጥ መስመር የሰጠው ወጣት ይናገራል፡፡

ህወሃትና መለስ በኢትዮጵያ የተከሉት የዘር ፖለቲካ በአገሪቱ በበርካታ ቦታዎች የማንነት ጥያቄ ከማስነሳት አልፎ የህይወት መስዋዕትነት እያስከፈለ ነው፡፡ እምቢባዮችን “ልክ እናስገባለን” በማለት እየፎከረ አገር በነጻ አውጪ ስም የሚገዛው ህወሃት፤ የህይወት ዑደቱን እስኪያጠናቅቅ “ባለ ራዕዩ መለስ” ያስቀመጡለትን “ራዕይ” በትጋት እያስፈጸመ ይገኛል፡፡

Zhabesha