Wednesday 25 March 2015

ወ/ት እየሩሳሌም አበረ, የአዲስ አበባ የኢህአዴግ የሴቶች ሊግ ም/ል ሊቀመንበር

“ኢህአዴግ የህዝቡ ብሶት አደጋ እንደሚያስከትል አውቋል” ስትል የአዲስ አበባ የኢህአዴግ የሴቶች ሊግ ም/ል ሊቀመንበር ተናገረች
መጋቢት ፲፮(አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሊጉ ም/ል ሊቀመንበር በመሆን ለአመታት ያገለገለችው ወ/ት እየሩሳሌም አበረ ከኢሳት ጋር ባደረገችው ቃለምልልስ “የአዲስ አበባ ህዝብ እንደሚገነፍል ድስት እፍ እፍ እየተባለ ቢያዝም፣ አሁንም
በርካታ የዲሞክራሲ እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን እያነሳ ነው” ብላለች።
የታፈነ የመልካም አስተዳደር እና የዲሞክራሲ ጩኸት አለ የምትለው ወ/ት እየሩሳሌም፣ ገዢው ፓርቲም ህዝቡ በከፍተኛ ብሶት ላይ እንደሚገኝና አደጋ ሊያስከትል እንደሚችልም ጠንቅቆ ያውቀዋል ብላለች።
ከምርጫ 97 በሁዋላ ኢህአዴግ የተሳካለት ነገር ቢኖር ተቃዋሚዎችን ማፈን ነው የምትለው ኢየሩሳሌም፣ ህዝቡ በሚታየው ነገር ሁሉ ባለመርካቱ ገዢው ፓርቲ ቁጥጥሩን በማጥበቅ የህዝቡን ብሶት ለማፈን ይሞክራል ስትል አክላለች።
ወ/ት እየሩሳሌም ድርጅቱን ጥላ ስደትን መርጣለች። ለረጅም አመታት የአዲስ አበባ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ እና በሌሎችም የስልጣን ሃላፊነቶች ላይ ሲሰሩ የቆዩት የኦህዴድ ድርጅት አባል የሆኑት ወ/ሮ አበባ ገብረስላሴም በቅርቡ ኢህአዴግን በመተው፣ በአሜሪካ
ጥገኝነት ጠይቀዋል። ከወ/ት እየሩሳሌም ጋር የተደረገው ቃለምልልስ ሰሞኑን ይቀርባል።

የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ መልዕክት ለ8ኛ ጊዜ ተመለሰ


የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ መልዕክት ለ8ኛ ጊዜ ተመለሰ
• ኢብኮና የአዲስ አበባ አስተዳደር መገናኛ ኤጀንሲ የሰማያዊ ፓርቲን የቅስቀሳ መልዕክት መልሰዋል
• ‹‹አማራጫችን እንዳናቀርብ እየተከለከልን ነው›› አቶ ዮናታን ተስፋዬ
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እና የአዲስ አበባ አስተዳደር መገናኛ ኤጀንሲ የሰማያዊ ፓርቲን የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክት ‹‹አናስተላልፍም›› ብለው መመለሳቸውን ድርጅቶቹ ለፓርቲው በላኳቸው ደብዳቤዎች ገልጸዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ መጋቢት 16/2007 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የብሔራዊ ራዲዮ በአማርኛ ስርጭት የሚተላለፍ ‹‹መንግስታዊ አወቃቀር›› የሚል የቅስቀሳ መልዕክት ልኮ የነበር ሲሆን ባለፉት 24 አመታት ተግባራዊ የሆነው የጎሳ ፌደራሊዝም ለግጭት መንስኤ መሆኑን በመረጃ ዘርዝሮ ማቅረቡን የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡
ይሁንና ኢብኮ ይህን የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ መልዕክት ‹‹በተለያዩ ጊዜያት በብሔር ብሔረሰቦች መካከል ተከሰቱ ያሉትን ግጭቶች በመዘርዘር በህዝቦች መካከል ሌላ ግጭት እንዲቀሰቀስና እንዲባባስ የሚያደርጉና ግጭት የሚያራግቡ፣ አንዱን ብሔር ከሌላ ብሔር የሚያገጩ ናቸው፡፡›› በሚል እንደማያስተላልፍ ገልጾአል፡፡ ከዚህም ባሻገር በመልዕክቶቹ ውስጥ ‹የህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት›፣ እንዲሁም ‹የህወሓት/ኢህአዴግ ስርዓት› የሚለው አገላለጽ የፓርቲውን ህጋዊ መጠሪያ የማይወክል በመሆኑ›› በሚል እንደማያስተላልፍ ገልጾአል፡፡
በሌላ በኩል እነዚህ ግጭቶች በአሁኑ ወቅትም የቀጠሉና የጎሳ ፌደራሊዝሙ እስካለ ድረስ ብዙ ዋጋ የሚያስከፍሉ መሆናቸውን የገለጸው የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ መልዕክቶቹ ከፓርቲው ማንፌስቶ የወጡ፣ ኢብኮ እንዳለው ለግጭት ሳይሆን ከግጭቶቹ መማር እንዲቻልና አሁን ያለው የጎሳ ፌደራሊዝም ከተስተካከለ ችግሮቹ እልባት እንደሚያገኙ በሚያሳይ መልኩ የተላለፈ መልዕክት ነው ብሎአል፡፡ ‹‹እኛ ያቀረብነው አማራጫችን ነው፡፡ አማራጫችን ስናቀርብ ደግሞ የጎሳ ፌደራሊዝም የፈጠረውም ቀውስም በማሳያነት ማቅረብ አለብን፡፡ ይህን እውነታ የአገር ውስጥና የውጭ ተቋማት ዘግበውታል፡፡ አብዛኛዎቹ መንግስትም ያመነባቸው ናቸው፡፡ ነገር ግን ስርዓቱ የሰራቸው ጥፋቶች ይፋ አውጥተን እንዳናቀርብ ስለተፈለገ መልዕክቱን መልሰውታል፡፡ በግልጽ አማራጫችን እንዳናቀርብ ተከልክለናል›› ሲል ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡
በተመሳሳይ የአዲስ አበባ አስተዳደር መገናኛ ኤጀንሲ የሰማያዊ ፓርቲን የቅስቀሳ መልዕክት ‹‹ከሀገሪቱ ሰንደቅ                                            አላማ ጋር የሚጻረር፣ ብሔር ብሄረሰቦችን ወደ አላስፈላጊ ግጭት እንዲያመሩ

                                        የሚገፋፋ፣ የሌላ ፖለቲካ
ፓርቲን ስም የሚያጎድፍ ይዘት የተካተተባቸው›› ናቸው በሚል መልሷል፡፡ ይህ የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ
ቅስቀሳ መልዕክት ሲመለስ ለ8ኛ ጊዜ መሆኑ ነው፡፡

Tuesday 24 March 2015

አበባ ገብረ ሕይወት ህወሓትን ከዳች

የአዲስ አበባ የኢህአዴግ ጽ/ቤት ድርጅት ጉዳይ ኃላፊዋ ህወሓትን ከዳች
ከምርጫ ዘጠና ሰባት በኋላ በኢሕአዴግ አደረጃጀት ዉስጥ ትልቅ ቦታ የነበራት ናት። ከሴቶች አደረጃጀት ሃልፊ ነበረች። ከዚያም በአዲስ አበባ የኢሕአዴግ ጽ/ቤት የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ ሆና እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ትሰራለች። በአዲስ አበባ ይለ የኢሕአዴግ አባል የማያወቃት የለም።
ከአዲስ አበባ የኢሕአዴግ ጽ/ቤት የድርጅቱ ጉዳይ ሃላፊነቷ በተጨማሪ በአዲስ አበባ የሴቶች መዋቅርም የአድን ክላስተር ሃላፊም ነበረች። አበባ ገብረ ሕይወት ትባላለች።አበባ በቅርቡ ለአንድ ስብሰባ ወደ አሜሪካን አገር ባቀናችበት ወቅት አጋጣሚዉን በመጠቀም፣ የፖለቲካ ጥገኝነት ለመጠየቅ እንደወሰነችና ወደ አገር ቤት የመመለስ ሀሳብ እንደሌላት ለርሷ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ጠቁመዋል፡፡
በተለይም በኢሕአዴግ ዉስጥ ፍጹም የሆነ የሕወሃት የበላይነት ከመኖሩ የተነሳ፣ በሞያቸውና በእውቀታቸው የመወሰንና የማገልገል እድል የሌላቸውና፣ የታዘዙትን ብቻ ማድረግ የሚጠበቅባቸው ሌሎች የኢሕአዴግ አባላት ደስተኛ እንዳልሆኑ በስፍት ይነገራል። ብዙዎች ባላቸው አጋጣሚ ሁሉ ኢሕአዴግን እየከዱ እንደሆነ፣ ያሉት ደግሞ ከዉስጥ መረጃዎች በማቀበል ከአዝዙ ያላቸውን ጥላቻ በማሳየት ላይ መሆናቸው በግልጽ እየታየ ነው።
ከዚህ በፊትም ሚኒስቴር ዴታ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ኤርምያ ለገሰን ጨምሮ ብዙዎች ኢሕአዴግ እንደከዱ ይታወቃል።

ጎንደር ዝምታውን ሰብሯል

 የመከላከያ ሰራዊት አባላት በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ታዘዋል
መጋቢት ፲፬(አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ሰሞኑን በሰሜን ጎንደር አካባቢ የታየውን የጸጥታ መደፍረስ ተከትሎ የአገሪቱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ካለፈው ሃሙስ ቀን ጀምሮ በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ታዛዋል።Ethiopian soldiers in Barentu
የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የአየር ሃይል አባላት ካለፈው ሃሙስ ጀምሮ ከግቢ እንዳይወጡ ሲታዘዙ የተወሰኑት ደግሞ ከደብረዘይት እና ድሬዳዋ አየር ሃይል ወደ መቀሌ አምርተዋል። ብዛት ያለው የእግረኛ ሰራዊትም ወደ ኤርትራና ሱዳን ድንበሮች አቅንቷል።
ወታደራዊ ልምምዶችና አዳዳስ ምልመላዎችም እየተካሄዱ መሆኑንም ምንጮች ገልጸዋል።
ማንነታቸው በውል ያልታወቀ የተቃዋሚ ሃይሎች ጎንደር ከተማ ውስጥ የሚሊሺያ አዛዥ የሆነውን ኮማንደር ተፈራን ገድለው ካመለጡ በሁዋላ፣ እነሱን ለመያዝ መጋቢት 12 አርማጭ ልዩ ቦታው እንኮይ ተራራ ላይ በተደረገ ጦርነት ፣ ከተቃዋሚዎች በኩል ሻምበል ይርዳውና
አዲሱ የተባሉ ሲገደሉ፣ ከመንግስት ታጣቂዎች በኩል ደግሞ የልዩ ሃይል አባል የሆነው እባበይ እንዲሁም አንድ ስሙ በውል ያልታወቀና ሁለት የሚሊሺያ አባላት ተገድለዋል። ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት ጀምሮ እስከ ምሽት በቀጠለው የተኩስ ልውውጥ፣ አንድ ተማሪ በመንግስት
ሃይሎች ተገድሏል። የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ምሽት ላይ አካባቢውን ጥለው መውጣታቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስትን አስተያየት ለማካተት የተደረገው ጥረት አልተሳካም።

Thursday 19 March 2015

ተቀላቀሉን፤ ካልሆነም በያላችሁት ተደራጁ!

pg7-logoህወሓት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ስለሚያደርሰው ዘርፈ ብዙ በደል ብዙ የተነገረለትና የተፃፈበት ብቻ ሳይሆን እየኖርንበት ያለ ሀቅ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብም የሚደርስበትን ስቃይ መታገስ ወደማይችልበት ጫፍ መድረሱ በሰበብ አስባቡ በሚፈነዳዱ ተቃውሞዎች የሚታይ ሀቅ ሆኗል።
በሌሎች አገሮች እንዲህ ዓይነት የሕዝብ ምሬት ሲኖር በጥቂት ግለሰቦችና ቡድኖች ጥሪ ሕዝብ ግልብጥ ብሎ አደባባይ ይወጣል። ከሕዝብ አብራክ የወጣው ጦር ሠራዊትና ፓሊስ ከተበደለው ሕዝብ ጎን በመቆም አምባገነኖችን አስወግዶ የሽግግር መንግሥት ያቆማል። በቅርብ ጊዜያት በሕዝባዊ እምቢተኝነት መንግሥት በተቀየረባቸው አገሮች ያየነው እንደዚህ ዓይነቱን ሀቅ ነዉ።
አገራችን ውስጥ ያለው ሁኔታ ግን ከዚህ በእጅጉ ይለያል። ህወሓት ኢትዮጵያ ውስጥ የገነባው የጦርና የፓሊስ ሠራዊት አመራር በዘር የተደራጀ በመሆኑ የሕዝቡን አጠቃላይ ብሶት ደግፎ ሊቆም ይችላል ብሎ መጠበቅ አይቻልም። ሠራዊቱ እንደ ተቋም ከተበደለው ሕዝብ ጎን እንዲቆም በመጀመሪያ በራሱ በሠራዊቱ ውስጥ ሥር ነቀል ለውጥ መካሄድ አለበት።በዚህ አቅጣጫ የሚሠሩ ሥራዎች እንደተጠበቁ ሆነው፤ ሠራዊቱ ዘረኛ ገዢዎቹን አስወግዶ እስኪመጣ መጠበቅ አይቻልም፣ አይገባምም። በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ፣ ሕዝባዊ እምቢተኝነት በሕዝባዊ አመጽ መታገዝ አለበት የሚለው ሁለገብ የትግል የትግል ስትራቴጂ ተመራጭ እንዲሆን ያደረገው ዋነኛ ምክንያት የሠራዊቱ ዘረኛ አወቃቀር ነው። በመረጥነው የትግል ስትራቴጂ መሠረት በሁለቱም ግንባሮች – ማለትም፣ በሕዝባዊ አመጽ እና በሕዝባዊ እምቢተኝነት ግንባሮች ሥራዎች መሠራት አለባቸው። ሁለገብ የትግል ስትራቴጂ እምንፈልገው ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ላይ እንዲያደርሰን የኢትዮጵያ ሕዝብ በሁለቱም የትግል ስትራቴጂዎች አኳያ መደራጀት ይኖርበታል። ሕዝባዊ የአርበኛ ሠራዊት ማደራጀት እንደሚያስፈልግ ሁሉ በኢትዮጵያከተሞችና ገጠሮች፤ በሥራና በመኖሪያ አካባቢዎች በምስጢር የተደራጁ ሕዝባዊ የአርበኛ ሲቪል ክበቦችም በብዛት መደራጀት ይኖርባቸዋል።
በዚህም ምክንያት አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ ከህወሓት ዘረኛ ፋሽስታዊ አገዛዝ ነፃ ለመውጣት የሚመኝ ኢትዮጵያዊ ሁሉ እንዲደራጅ ጥሪ ያቀርባል! እያንዳንዱ ነፃነት ፈላጊ ኢትዮጵያዊ ከሚያምነውና ከሚመስለው ወዳጁ ጋር ይቧደን፤ ቡድኑንም በሥርዓትና በሚስጢር ያደራጅ።
ከእንግዲህ “ምን እንሥራ? ትግሉን እንዴት እንርዳ?” እያሉ ለሚጠይቁ ወገኖቻችን በሙሉ መልሳችን “ከቻላችሁ ተቀላቀሉን፤ ካልሆነም በያላችሁት ተደራጁ” የሚል ነው። ድርጅት ኃይል ነው። መደራጀት በራሱ ትልቅ ሥራ ነው። ድርጅት ድርጅት የሚሆነው ደግሞ በሥርዓት ሲዋቀርና በሥነሥርዓት ሲመራ ነው። ስለሆነም ነፃነት ናፋቂ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሌላ አደራጅና አስተባባሪ እንዲመጣለት ሳይጠብቅ በራስ አነሳሽነት እንዲደራጅ ይህ ጥሪ ተላልፏል።
በሥርዓት የተደራጀ ስብስብ ሲኖር የሚሠራ ሞልቷል። ይህንን መንገርም አያስፈልግም። የተደራጀ ስብስብ ራሱ ሥራዎችን አቅዶ መሥራትም ይችላል። የሚከተሉት ነጥቦች ለአብነት ተዘርዝረዋል።
  1. የተደራጀ ስብስብ ጠላትና ወዳጁን ይለያል። የጠላቱን ጥንካሬና ድክመቱን ከራሱ ጥንካሬና ድክመት ጋር መዝኖ የወገን ኃይልን ጥንካሬ የሚያጎለብቱ፤ ድክመቶቹን የሚቀንሱ እርምጃዎችን በመውሰድ አቅሙን ይገነባል።
  2. የተደራጀ ስብስብ የጠላትን እንቅስቃሴ እየሰለለ መረጃ ለነፃነት ኃይሎች እንዲደርስ ያደርጋል።
  3. የተደራጀ ስብስብ የተቀናጀ የሕዝባዊ እንቢተኝነት ተግባራትን ይፈጽማል። ለምሳሌ፣በሥርዓቱ የደረሰበትን ምሬት በወረቀት ገንዘብ፣ በአስፋልት፣ በታክሲዎችና በግድግዳዎች ላይ ይጽፋል፤ ገንዘቡን የኤፈርት ንብረት ከሆነው ውጋጋን ባንክ ያስወጣል፤ መዋጮዎችና ግብር ያጓትታል ከዚያም አልፎ አልከፍልም ይላል።
  4. የተደራጀ ስብስብ በሥርዓቱ ላይ ለማመጽ ሁኔታዎችን ያመቻቻል። ሁኔታች ተሟልተው አመጽ ሲቀሰቅስ ደግሞ ትግሉ ግቡን ሳይመታ እንዳይበርድ ፀንቶ ይቆማል።
  5. የተደራጀ ስብስብ ወዳጆቹን አስተባብሮ በጥንካሬው ላይ ተመርኩዞ በአካባቢው ባለ የህወሓት ኃይል ላይ ክንዱን ያነሳል።
በአርበኞች ግንቦት 7 እምነት የኢትዮጵያ ሕዝብ አስተባባሪና መመሪያ የሚጠብቅበት ጊዜ አልፏል። ህወሓት የዘረጋው የአፈና ሥርዓት የጠበቀ ትስስርና ቁጥጥር ያለው ድርጅት ማቆም እንዳይቻል አድርጓል። ስለሆነም ያለን አማራጭ በርካታ ያለዘወትር የበላይ አካል ትክክል ራሳቸውን በራሳቸው ማስተዳደር የሚችሉ ስብስቦችን በመላው የአገራችን ክፍሎች በአፋጣኝ ማደራጀት ነው። ይህንን ደግሞ ማድረግ ይቻላል።
ወቅቱ ህወሓትን ከጫንቃችን ላይ ለማውረድ የምንደራጅበት ነው። ድርጅት ኃይል ነው፤ አደራጅና አስተባባሪ ሳንጠብቅ በራስ ተነሳሽነት ዛሬውን እንደራጅ!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

Wednesday 11 March 2015

why we care so much more about ethnicity than before

The strength of all Ethiopia is our oneness—our unity—our love—our respect for each other! Our oneness should represent the protection for us from more years of misery, from the image of our country of death, famine, skinny children, prostitutes, beggars, of hopelessness, injustice, inequality, ethnic hatred, revenge, envy, division—all symbols of evil that have come as a result of ethnic apartheid policy and our wrongful attitudes towards each other. If we look at it all honestly, we are worse off today than we were a hundred years ago.
We are more divided, more filled with hatred and tribalism than our ancestors were. We have become a nation of strangers—like a family standing together inside elevators where no one talks to anyone else—as if it were a social rule that applied to us! This lack of reaching out to others and making meaningful relationships, across ethnic boundaries, is why the TPLF is control our country and we are where we are today—all suffering!
We Ethiopians really need to wonder why we care so much more about ethnicity than before—what has happened? Why do we devalue others? My answer is that the TPLF ethnic apartheid policy and our narrow-minded ethnic politicians or leaders have inflamed these feelings. They carry banners of hatred, division, revenge for the benefit of their own agendas to gain power, wealth, oil and land. The deaths that result from these agendas do not resolve our conflicts, but deepen them.
Right now we,the people have been seduced into this kind of poison thinking that must be rejected individually if we ever are going to see all of us sit down together. If we do not change our thinking, we will end up a nation and a people in ruin. We will be responsible for increased suffering across every ethnic line even if we just sit by and do nothing.
Obang.

Tuesday 10 March 2015

Ethiopia’s Foreign Minister and the teenage girl


By Tedla G Woldeyohannes
Does truth matter in politics? Many would answer this question with an affirmative, i.e., a “yes”, but would immediately add, what is the point of talking about truth in politics since politicians in general are liars? But is this true? Many would respond to this question affirmatively. Now it is not hard to find evidence for many politicians for falling short of being truthful about what they say and do. We should not overgeneralize this since it is hard for all politicians to be liars all the time. Since politicians are acutely aware of the fact that many people believe that politicians are generally liars, when opportunities arise to advance whatever they want to advance, it becomes much easier for them to lie. Now it is not hard to imagine that the widely held belief that politicians are generally liars breeds politicians that are actually liars, if not always, but on many occasions. Since politicians don’t fall from the sky, this cycle of belief about politicians generally as liars and politicians actually lying continues. Now what has all of this got to do with the Ethiopian Foreign Minister and the 14 year old girl’s story from Melbourne, Australia? The following.
Truth is nowhere to be found in the claims reported in the news story about the Ethiopian Foreign Minister and Beritu Jaleta. An embarrassing exposure of the lies about the story has been written by journalist Abebe Gellaw. This news report provides one of the endless opportunities to consider the question whether truth matters in politics—in this case, in the Ethiopian context. This article raises some questions that arise in relation to the story reported about Beritu Jaleta and Dr. Tedros Adhanom, the Ethiopian Foreign Minister. In the link I referred to above, Journalist Abebe Gellaw raises a number of questions that are mainly aimed at getting the facts straight in order to get to the truth about what is reported. After reading Abebe’s initial repor at getting the facts and truth about the story, I was left with one important question that neither Abebe’s report nor the press conference would provide an answer to. Since there is no easy answer, I decided to think about a possible answer that would sit well with the politics of lies and deception of the Ethiopian government. But still the question needs to be raised and an answer needs to be sought. Hence, this article is one attempt at gesturing in the direction of an answer to this question: What is the point of this whole story or drama about the 20 million Australian
dollars that is reported to be used to build schools in Gara Muleta, Eastern Harargie? Is it really true that Beritu was awarded 20 million Australian dollars the way she announced about it? I refer readers to Abebe’s findings whether Beritu was actually awarded such a prize of that magnitude. Whether she was awarded the 20 million Australian dollars or there was something else going on, uncertainty about the truth about this aspect of the story need not distract us from the more pressing question about the role of Dr. Tedros, in his capacity as the Ethiopian Foreign Minister. What was he doing in this story? Was his involvement in this story as innocent as the role of a mere 14 year old girl? I don’t think so. To think of a high profile Ethiopian government official as innocent about what he is doing in his capacity as a Minister of Foreign Affairs would be absurd. What would be the best explanation for all the drama behind this story?
I propose what I take to be the best explanation for the story: Start with the apparent ethnic background of Beritu. The way the current Ethiopian government deals issues raised by the Oromo people is too obvious for anyone who is familiar with the brutality the Oromo people suffered. Note the ongoing controversy regarding the so called “Master Plan” and how this controversy has led to the brutal killing of university students in Ambo. Now add this: In various social media there is a growing vocal outcry of the sundry ways the Oromo people suffer injustice in the hands of the Ethiopian government. It is not hard to imagine now how the social media savvy Ethiopian Foreign Minister can quickly make use of the news about the alleged humanitarian investment by a 14 year old child of Oromo ethnic heritage. This posture Dr. Tedros assumed in the story has a clear message for those who expose the injustice the Ethiopian government commits against the Oromo people. The message is to suggest that the Ethiopian government is openly working and promoting the interest of the Oromo, including from the Diaspora. This story about Beritu is intended to promote the government’s willingness to work for the interest of the Oromo with the Oromo people. Would Dr.Tedros and the Ethiopian government make political profit from the commitment made to work with Beritu? There is no doubt that is the hope.
A moment’s reflection shows that to engage in this scheme for someone in Dr. Tedros’ capacity is an insult to millions of Ethiopians. The insult now has a deeper dimension to it because it involves the life of a 14 year old. With zero piece of evidence to support that this story is true, hence it is not unjustified to call it is a scam, and that it has been staged to boost the public relations image for Dr. Tedros and his Office, this would suggest that Dr.Tedros shows a remarkable failure in his judgment using a child in this whole scheme. If and when all the things said and pledges made come to nothing, what will this young girl become? Considering all the routine human rights abuse Dr. Tedros’s government has been committing against its citizens and particularly the Oromo people, it is not difficult to imagine that using a 14 year old child to make a political profit would be of no concern to him and his office.
Furthermore, the other aspect of the insult to the millions is this: I take it that there is something Dr. Tedros knows about the facts regarding the alleged prize Beritu announced that she had won. Note that the spokesperson for the Ministry of Foreign Affairs (MFA), Tewolde Mulugeta, indicated in the press conference held at the office of MFA that the MFA has received some evidence or document about Beritu’s award. However, in a statement shared on his Facebook page, on March 7th, 2015 Dr Tedros claimed that he has basically JUST BELIEVED what a 14 year old told him without any need to make sure the accuracy of her claim. To justify or to make his story BELIEVABLE he has said that children are innocent and hence they should be trusted about what they tell us. He said that if to trust innocent children is a mistake, then he would rather choose to admit such a mistake. He added that he chose to believe what Beritu told him and thinks others would agree with him about his justification to believe the story without a need for evidence whether the story is true or not. Essentially his Facebook message is an attempt to justify his trusting what he was told by an innocent school girl boils down to: Probably what Beritu told me was not true, even if it was not true, her motive is not bad because she is a young girl and the young are generally innocent. And, probably, it was a mistake for me to trust what she told me [but note that he did not say he has made any mistake], but I would rather trust what innocent children or young tell me rather not. This reasoning is preposterous when it is displayed by a Foreign Minister of any country. In sum, this justification to cover up lies behind this political drama shows a serious failure in his judgment regarding his role as a Minster of Foreign Affairs. His poor judgment in handling this issue for some political profit would do more damage to his office than he seems to have realized.
The other serious insult surrounding this scam is to the people of Ethiopia, in general, whose Minister of Foreign Affairs he is, and to the Oromo community, in particular, is this: This level of blatant lie and the way Dr. Tedros tried to cover one lie with another shows the degree of contempt he and those in leadership position like him have to their fellow citizens. To script this ridiculously naïve political drama and to act it out in public, including using the social media,
Facebook, to target those who have access to the social media, is to tell fellow citizens that this is what they deserve. But this contempt to fellow citizens has turned out to be a double-edged sword in that it is the Minister’s poor judgment that has been exposed more than anything. This is an example of a person who trivializes truth and ends up trivializing himself. It is not the first time, nor is it the last time for the Ethiopian government officials to engage in blatant lies and perpetuating more lies and deceiving fellow citizens, but using a 14 year old girl for political agenda is outrageous, to say the least.
The bottom-line: In the days and weeks to come, numerous lies will be told in various forms and shapes because the 2015 election is coming. Stories such as Beritu’s are intended to bolster the image of the EPRDF government in the days leading up to the farce election to legitimize the regime in power to remain in power so that the abuse of power can continue. In addition, the Oromo people who opposed the implementation of the so-called Master Plan seem to be among the intended targets of this disastrous drama with the pseudo-goal that the Ethiopian government is promoting the interests of the Oromo, including the Diaspora Oromo to work with the Ethiopian government in fighting poverty. As those who are on Facebook and other social media area aware of, the most trenchant criticisms regarding the so called Master Plan comes from members of the Oromo community in Melbourne, Australia.
It is no coincidence why Beritu, who is also a member of the Oromo community in Melbourne, Australia was chosen to play a role in this poorly thought-out and acted political drama. One of the key purposes of this whole scam and drama is to give the Oromo community a distraction from the most scathing criticism of the Ethiopian government’s relation to the Oromo people that comes from Melbourne, Australia among other Diaspora Oromo communities.

Friday 6 March 2015

የአድዋ ድልን እያከበርን ለዛሬ ነፃነታች ቃል እንግባ!


pg7-logoመቶ አስራ ዘጠነኛውን የአድዋ ድል በዓል እየዘከርን እንገኛለን። እንደዛሬው ሁሉ ያኔም ቀደምቶቻችን በርካታ የውስጥና የውጭ ችግሮች ነበሩባቸው። እንደዛሬው ሁሉ ያኔም በመካከላቸው የሀሳብና የጥቅም ልዩነቶች ነበሩ። ያም ሆኖ ግን ቀደምቶቻችን በአገር ነፃነት ጉዳይ ላይ ሰፋ ያለ መግባባት ላይ መድረስ በመቻላቸው በዘመናዊ የጦር መሣሪያዎችና ድርጅት የተጠናከረውን የአውሮፓ ጦር በጥቁር የጦር አዛዦችና ተዋጊዎች መመከት ቻሉ። ከአድዋ በፊት አፍሪቃ በተለይም ኢትዮጵያ ውስጥ አውሮፓዊያን የተሸነፉባቸው ተናጠል አውደ ውጊያዎች ነበሩ፤ ጦርነትን ሲሸነፉ ግን አድዋ የመጀሪያው ነው። በዚህም ምክንያት ነው የአድዋ ድል የአፍሪቃውያን ከዚያም አልፎ የጥቁር ሕዝቦች ሁሉ ድል ተደርጎ የሚወሰደው።
ዛሬ ግን እኛ ያኔ የነበሩት አያትና ቅድመ አያቶቻችን እደረሱበት የመግባባት ደረጃ ላይ መድረስ ባለመቻላችን አገር በቀሉን ቅኝ ገዢ – ህወሓትን – ከኢትዮጵያዊያን ጫንቃ ላይ ማውረድ አቅቶን አገራችንና ሕዝቧን ከባዕድ በባሰ ሁኔታ እያዋረደ በመግዛት ላይ ይገኛል።
ያኔ ለሀገሩ፣ ለነፃነቱና ለክብሩ ቀናዒ የሆነው ኢትዮጵያዊ ራሱን ወታደር አድርጎ በየጎበዝ አለቃው አዝማችነት በጠላት ላይ ዘምቶ ድልን ተቀዳጅቷል። ዛሬ ግን ቁጥሩ ቀላል ያልሆነ የመከላከያ ሠራዊት አባል ለህወሓት አዛዦች ሎሌነት አድሮ የራሱን ወገን ይፈጃል። ያኔ በአገዛዙ ላይ ብሶት የነበረው እንኳን ሳይቀር ብሶቱን ችሎ ለሀገር ሉዓላውነትና ክብር ሲል ተዋድቋል። ዛሬ ግን ቁጥራቸው ቀላል ያልሆኑ ወገኖቻችን የኢትዮጵያን ዘላቂ ጥቅም ከብሶቶቻቸው በላይ አሻግረው መመልከት ተስኗቸዋል።
ዛሬ 119ኛውን የአድዋ ድል በዓል አያቶቻችንን በማድነቅ ብቻ ልናሳልፈው አይገባም። የአያቶቻችንን ገድል ስናከብር ዛሬ የምንገኝበትን ሁኔታ መመዘን ይገባናል። ራሳችንን ከእነሱ ጋር በማስተያየት እንደምን ያለን ውለታ መላሽ ያልሆንን የልጅ ልጆች መሆናችንን መመዘን እና ራሳችንን መውቀስ ይገባናል። የሚሳዝነው ዛሬ ራሱን ከሚወቅሰው በላይ አያቶቹን የሚወቅስ መብዛቱ ነው። እነሱ ችግሮችን ተሻግረው የምንኮራበትን ድል አቀዳጅተውን አልፈዋል። እኛ ግን እነሱ ያቆዩልንን ድል እንኳን ማስጠበቅ አልቻልንም። ከአድዋ ድል አንድ መቶ አስራ ዘጠኝ ዓመታት በኋላ አገራችንን ለህወሓት የአገር ውስጥ ቅኝ አገዛዝ ማስረከባችን ሊያመንና ሊያንገበግበን ሲገባ ድሮ ሊደረጉ ሲችሉ አልተደረጉም በምንላቸው ነገሮች ላይ እየተከራከርን ግዜያችንን እናጠፋለን።
አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ታላቁን የአድዋን ድል ለአጎናፀፉን ቀደምቶቻችን ያለንን ክብር መግለጽ ያለብን ዛሬ አገራችን ከህወሓት የአገር ውስጥ ቅኝ አገዛዝ ነፃ ለማውጣት በምንገባው ቃል ኪዳን ነው ብሎ ያምናል። አገራችንን በቅኝ ግዛትነት እያስገዛን የቀደምቶቻችንን ድል መዘከር ለእኛ ለልጆቻቸዉ የሚያሳፍር ተግባር ነው ብሎ ያምናል። አርበኞች ግንቦት 7 የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት አገር በቀል ቅኝ ገዥ በሆነው ሕወሓት እየተመራ የኢትዮጵያን ሕዝብ የማዳከሙን ተግባር በአስቸኳይ ማቆም ይኖርበታል ብሎ ያምናል። ስለሆነም የመከላከያ ሠራዊት አባላት ልባችሁንም ክንዳችሁንም ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር አድርጉ። ቀደምት አባቶቻችን አድዋ ላይ ድል የነሱት ቅኝ ገዥ ዛሬ ቀለሙን ለውጦ “ህወሓት” ተሰኝቶ ያንተ አዛዥ ሆኗል። መሣሪያህን በህወሓት አዛዦችህ ላይ የምታዞርበት ወቅት አሁን ነው። ንቃ፤ ተነስ!
አገርን ለጠላት አስረክቦ በቀደምት ጀግኖች ታሪክ መኩራት አሳፋሪ ነው። አባቶቻችን በነፃነት ያቆዩልን አገር የህወሓት መፈንጫ ሆና ማየት የሚያሸማቅቅ ነው። የጀግኖች አያቶቻችን የልጅ ልጆች መሆናችንን የምናስመሰክረው አገራችንን ከህወሓት አገዛዝ ነፃ ስናወጣና የዜጎቿ መብቶች የተከበሩባት ፍትህና እኩልነት የሰፈኑባት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ስንመሠርት ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዚህ ታላቅ ዓላማ ይነሳ ሲል አርበኖች ግንቦት 7 ጥሪ ያስተላልፋል።
አርበኞች ግንቦት 7: የአድዋ ድልን እያከበርን ዛሬ ነፃነታችንን ለማስከር ለመታገል ቃል እንግባ ይላል።


    ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

    ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ለኢትዮጵያ መከላክያ ሰራዊት ያስተላለፉት ጥሪ

    እኛ ቀንድ ያለን ሰዎች አደለነም ታውቀናለክ እኔ ብርሃኑ ነጋ ነኝ በምርጫ የኢትዮጵያ ህዝብ የመረጠኝ ሰው ነኝ ለአዲስ አበባ ከንቲባነት በምርጫው ግዜ ምን ስናወራ ምን ስንከራከር እንደነበር ይህ ህዝብ ጠንቅቆ ያውቃል so የሚመጣው ሃይል ህዝብን የመከላክያን ጦር ለማጥፋት ሚመጣ ሃይል አደለም ወያነን የወያነን ስረአት ለማጥፋት ሚመጣ ነው የወያነን ስረአት ማጥፍት ደሞ ህዝብም መከላክያም ሚፈለገው ነገር ነው በአየር ሃይልም ሆነ በሁሉም ነገር መቸ ነው ይህ ነገር ሚጀመረው የሚል ሃይል እንዳለ እናውቃለን ስለዚ ግንቦት ሰባት አርበኞች መጡብክ ሊያጠፉል ነው ቢሉ አትስማቸው ለሃገርክ ታገል::

    መንገዶች ሁሉ ወደ ሰሜን ይወስዳሉ

    ከዚህ በፊት በአዲስ አበባ ተጀምሮ የነበረው ወያኔን የሚያወግዝ‬ ፣ የህዝባዊ አመፅና ተቃውሞ ጥሪ የሚያስተላልፉ ፅሁፎችን መበተንና በተለያዩ ቦታዎች መለጠፍ ዛሬ በተለያዩ ከተሞች ተከናውነዋል። 

    በዚሁ መሰረት ተመሳሳይ መልዕክት ያላቸው ነገር ግን በተለያዩ እጅ ፅሁፎች የተፃፉ ፅሁፎች በወልቂጤ፣ በአምቦ፣ በደብረብርሃን፣ በመሃል ሜዳ ፣በአዋሳና በአዲስ አባባ በተመሳሳይ ስዓት ተበትነዋል ተለጥፈዋል።
    ከዚህ ጋር ተያይዞ የተግባሩ ዋና ፈፃሚዎች ውስጥ እስከዛሬ አንድም ሰው ያልተያዘ ሲሆን ፣ ኮልፌቀራንዮ ክፍለከተማ ውስጥ በመኖሪያው ቤት አካባቢ ሞት ለወያኔ ፣ አርበኞች ግንቦት ፯ ያሸንፋል የሚል ፅሁፍ በመለጠፉ ምክንያት ዳንሄል ተስፋዪ የተባለ ወጣት አሸናፊ በሚባል ልዪ ስሙ ልኳንዳ ተራ የ ታክሲ ተራ አስከባሪ በመሆን ለወያኔ በሚሰልል ግለሰብ ጠቁሚነት ተይዞ በደቂቃዎች ልዩነት ተለቋል፣ ወጣቱ ከድርጊቱ ጋር ግንኙነት አልነበረውም።
    ከተላለፉት መልዕክቶች መካከል
    ፨ መንገዶች ሁሉ ወደ ሰሜን ይወስዳሉ ! ከአርበኞች ግንቦት፯ጋር እንቀላቀል! አግ፯ ያሸንፋል ! የታሰሩ ይፋቱ! የነፃነት ታጋዮች አሸባሪ አይደለንም ! ወያኔዎች ወዮላቹ ! በረሃብ ሳይሆን ለነፃነቴ ታግይ በጥይት እሞታልው ! የግፍ አገዛዝ ይብቃን ! ሞት ለወያኔ ! ይገኙበታል።

    Thursday 5 March 2015

    በጄኔቫ የሚገኘው የኢትዮጰያ ኤምባሲ “የተቃዋሚ ደጋፊዎች ናችሁ”ላላቸው ኢትዮጰያውያን ፓስፖርት አላድስም አለ።
    የካቲት ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በስዊዘርላንድ የዙሪክ ነዋሪ የሆኑት አክቲቪስት ፊዮሬላ ሮማኖ ለኢሳት እንደገለጹት ፓስፖርታቸውን ለማሳደስ ቀጠሮ አስይዘው ከሚኖሩበት ዙሪክ ኤምባሲው ወደሚገኝበት ጀኔቫ የ3 ሰዓት መንገድ ተጉዘው ቢሄዱም፣ የኤምባሲ ስራተኞቹ በአካል ሲያዩዋቸው በተቃውሞ እንቅስቃሴ እንደሚሳተፉ ስለለዩዋቸው አገልግሎቱን ሳይሰጡ መልሰዋቸዋል።
    ኤምባሲው እንደደረሱ ጎይቶም በሚባል ሰራተኛ የተሰጣቸውን ፎርም ከሞሉና ፎቶግራቸውን ከሰጡ በሁዋላ በስዊዘርላንድ ለምን ያህል ዓመት እንደቆዩ ጥያቄ የቀረበላቸው ወይዘሮ ፊዮሪና፤ ለ13 ዓመት መቆየታቸውን ሲናገሩ ፦” በ 13 ዓመታት ውስጥ ለሀገርዎ ምን ሰሩ?” የሚልና ከፓስፖርት እድሳቱ ጋር ተያያዥነት የሌለው ተጨማሪ ጥያቄ እንደቀረበላቸው ተናግረዋል።
    ለቀረበላቸው ጥያቄ በደፈናው፦”እሱን ሀገሬ ስሄድ የማምንበትን ጉዳይ እፈጽማለሁ” የሚል ምላሽ መስጠታቸውን የገለጹት ወይዘሮ ፊዮሪና፤ ይኽኔ ፦”አንቺን በደንብ እናውቅሻለን፤ ለጊዜው ፓስፖርት ማደስ አቁመናል” እንደሏቸው ገልጸዋል።
    ቀጠሮ አስይዤ ደርሶ መልስ የ6 ፡00 ሰዓት መንገድ ተጉዘው ከመጡ በሁዋላ የዚህ ዓይነት ምላሽ በማግኘታቸው የተበሳጩት ወይዘሮ ፊዮሪና፤ በጊዜው ኤምባሲ ለመሄዳቸውና የፓስፖርት እድሳት ጥያቄ ለማቅረባቸው ማረጋገጫ ደብዳቤ እንዲጻፍላቸው ቢጠይቁም ኤምባሲው በእምቢተኛነቱ መጽናቱን ገልጸዋል።
    ጉዳዩን ለስዊዘርላንድ ፖሊስ ባመለከቱት መሰረትም የፖሊስ የማረጋገጫ ወረቀትና ፊርማ ይዘው መመለሳቸውን ተናግረዋል።
    ይኽኔ፦”መንግስትን መቃወምም ሆነ መደገፍ መብት እስከሆነ ድረስ ከኤምባሲ አገልግሎት እንዳናገኝ ምክንያት ሊሆን አይችልም” ስላቸው ፦”እሱን ሄደሽ ኢሳት ላይ ተናገሪ” አሉኝ የሚሉት ወይዘሮ ፊዮሪና፤ በተቃውሞ ሰልፎች በመሳተፋቸውና የኢሳት ደጋፊ በመሆናቸው ከኤምባሲው አገልግሎት ማግኘት አለመቻላቸውን በዝምታ እንደማያልፉት ተናግረዋል።
    “እኔ ብቻ ሳልሆን በርካታ እንደኔ ያሉ ህጋዊ ነዋሪዎችም ተመሳሳይ ችግር እየደረሰባቸው ነው” ያሉት ወይዘሮ ፊዮሪና፤ ከሀገራችን ተሰደን እዚህም ሁለተኛ ስደተኛ መሆን ስለሌለብን የኔ ዓይነት ተመሳሳይ ችግር ከደረሰባቸው ወገኖቼ ጋር በመሰባሰብ በኤምባሲው ላይ ተከታዩን ህጋዊ እርምጃ ለማስወሰድ ተዘጋጅተናል ብለዋል።
    ወይዘሮ ፊዮሪና ፦”ኤምባሲው ለኢትዮጰያውን በእኩልነት አገልግሎት መስጠት ካልቻለና የቤተሰብ ኩባንያ ከሆነ እኛ ባለንበት ሀገር ሊኖር አይገባም”ያሉት ወይዘሮ ፊዮሪና፤ ኢትዮጰያውያን ያለምንም ፍርሀት ተባብረን ልንነሳ ይገባል ብለዋል። ወይዘሮ ፊዮሪና ሀሳባቸውን ሲያጠቃልሉም ፦ እኔን ኢትዮጰያዊ ያደረገኝ ጥንት አያቶቼ የከፈሉት የደም መስዋእትነት እንጂ ትናንት የመጣ ወያኔ አይደለም “ብለዋል።

    Wednesday 4 March 2015

    ም/ል ጠ/ሚኒስትሩ ተቃውሞ ገጠማቸው

    ም/ል ጠ/ሚኒስትሩ ተቃውሞ ገጠማቸው
    የካቲት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የአልጀሪያው -ኤል ኡልማ ቡድኖችን ጨዋታ ለማየት በባህርዳር ስታዲየም በእንግድነት የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ደመቀ መኮንን ከጨዋታው በፊት ንግግር እንዲያደርጉ በተጋበዙበት ሰአት ጨዋታውን ለመመልከት በስቴዲየሙ የተገኘው ሕዝብ በታላቅ ቁጣ የተቃውሞ ድምጽ በማሰማቱ ንግግራቸውን እንዲያቋርጡ መገደዳቸውን የክልሉ ወኪላችን ገልጻለች፡፡
    አብዛኛው ህዝብ ከተቃውሞ ድምጹ ጋር የተቀናቃኝ ፓርቲዎችን የምርጫ ምልክት በእጁ በማሳየት አቶ ደመቀ ንግግራቸውን እንዲያቋርጡ አስገድዷቸዋል፡፡
    የጊዮርጊስ ጨዋታ ወደ ባህርዳር የተላለፈው-የህውሃት 40ኛ አመት ዝግጅትን ለማካሄድ ሲባል አዲስ አበባን ከሁሉም ትኩረት ከሚስቡ ነገሮች ነጻ በማድረግ ነዋሪው በሙሉ ልቡ የዕለቱን ዝግጅት በቴሌቪዢን መስኮት እንዲመለከት በማሰብ እንደሆነ ከአዲስ አበባ ቡድናቸውን ለመደገፍ የመጡ ተመልካቾች ለዘጋቢያችን ገልጸውላታል። በተሰጠው አስተያየት ዙሪያ የፌደሬሽኑን አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።
    በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊበን ዝቋላ ወረዳ አዱላላ ከተማ በሚገኘው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ዙሪያ የእሳት ቃጠሎ መቀስቀሱን የገዳሙ መነኰሳት እየተናገሩ ነው፡፡ ከጠዋቱ 2፡00 ገደማ የተቀሰቀሰው የእሳት ቃጠሎው የጀመረው ወንበር ማርያም እየተባለ በሚጠራው በገዳሙ ሰሜናዊ አቅጣጫ ነው፡፡ ይህ አቅጣጫ፣ የገዳሙ ሞፈር ቤት የሚገኝበት መውጫ መንገድ ሲኾን በአኹኑ ሰዓት በበርካታ ቦታዎች ጭስ እንደሚታይ በመነኰሳቱ ተገልጧል፡፡ የቃጠሎው መንሥኤ በውል ባይታወቅም እሳቱ በአካባቢው ባለው ከባድ የነፋስ ኃይል ወደ ገዳሙ መውጫና በገዳሙ ዙሪያ እንዳይስፋፋ ተሰግቷል፡፡ የአቅራቢያው ነዋሪ ኅብረተሰብ በጥሩንባ በተላለፈው የድረሱልን ጥሪ የተሰባሰበ ሲኾን ወደ ወረዳው ጽ/ቤትም ተደውሎ የአስተዳደሩ አባሎችና የፖሊስ ኃይል በስፍራው መድረሳቸው ተገልጧል፡፡ ‹‹ቃጠሎውን በቅጠልና በአፈር ለመከላከልና መዛመቱን ለመቀነስ የነፋሱን ጋብ ማለት እየተጠባበቅን ነው ብለዋል፤›› አንድ የገዳሙ መነኰስ፡፡ በጥንታዊውና ታሪካዊው ገዳም ዙሪያ የእሳት ቃጠሎ ሲደርስ የአኹኑ የመጀመሪያ አይደለም፡፡ መጋቢት ፲ ቀን ፳፻፩ ዓ.ም. በደረሰው የእሳት ቃጠሎ እንደ አርዘ ሊባኖስና የሐበሻ ጥድ ያሉት አገር በቀል ዛፎች በስፋት ወድመዋል፡፡ መጋቢት ፰ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. የተቀሰቀሰው ቃጠሎ ደግሞ ተኣምራዊና ግራ አጋቢ ጠባይዕ የታየበት ነበር፡፡ በምሥራቃዊ አቅጣጫ በሚገኘው የመንግሥት ደን ውስጥ ተከሥቶ በአንድ ገጽ ኃይሉ ሲቀንስ በሌላ አቅጣጫ እየተዛመተ ገዳሙን ጨርሶ ለማጥፋት በተቃረበበት ኹኔታ ከአዲስ አበባ፣ ከቢሾፍቱና ከአዳማ በተመሙ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች፣ በጎ አድራጊ ምእመናንና አካላት መተባበር እንዲኹም በመከላከያና በፖሊስ ኃይሎች እገዛ መገታቱ የሚታወስ ነው፡፡

    Monday 2 March 2015

    10991087_874868705903662_4415005467626026122_nየኰሚኒኬሽን ምክትል ሃላፊ የሆነው ሽመልስ ከማል ባለፈው ሳምንት አሜሪካ መግባቱን ምንጮች አስታወቁ። ከሬድዋን ሁሴን ጋር የከረረ ፀብና አለመግባባት ውስጥ የገባው ሽመልስ ለረጅም ሳምንት ከስራ ገበታው ርቆ መቆየቱን ያስታወሱት ምንጮቹ አሜሪካ የመጣው በግሉ እንደሆነ አስታውቀዋል። በዲሲ ቆይታ ካደረገ በኋላ ኒውዮርክ ወደሚገኘው ወንድሙ ዘንድ ያቀናው ሽመልስ የፖለቲካ ጥገኝነት በመጠየቅ አሜሪካ ለመቅረት ሃሳብ እንዳለውና እንደሚፈልግ ምንጮቹ አጋልጠዋል። ሽመልስ ከማል – አፋኙን የፕሬስ ህግ በማርቀቅ፣ በመቶ የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች ከአገር እንዲሰደዱ በማድረግ፣ ጋዜጦችንና መጽሔቶችን ከህትመት ውጭ እንዲሆኑ በማድረግ፣ በቅንጅት አመራሮችና ጋዜጠኞች ላይ የሞት ቅጣት እንዲበየን በመጠየቅ፣ እነእስክንድር ነጋ በሽብርተኝነት እንዲፈረድባቸው በማድረግ፣ የሙስሊም ማህበረሰብ ተወካዮች እስር ቤት እንዲገቡና በሽብርተኝነት እንዲከሰሱ በማድረግ እንዲሁም ሙስሊሙንና ተቃዋሚዎችን በጅምላ በመስደብና በማንጓጠጥ፣ ብርቱካን ሚዴቅሳ ለ2 አመት በጨለማ እስር ቤት እንድትማቅቅ በመፍረድ..ወዘተ የመብት ረገጣ ያካሄደና በበርካታ ወገኖች ህይወት ላይ የጭካኔ ፍርድ ያሳለፈ እንደሆነ ይታወቃል።

    ቴድሮስ አድሃኖም ያራገቡት የ20 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት የፈጠራ ወሬ መሆኑ ተረጋገጠ

    Monday, March 2, 2015 @ 01:03 PM ed

    የአውስትራሊያ መንግስት እና የሮተሪ ፋውንዴሽን በሪቱ ጃለታን አናውቃትም ገንዘብም አልሰጠንም አሉ


    በአበበ ገላው  
    (አዲስ ቮይስ) ሰሞኑን የህወሃት መራሹ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሆኑት ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በአንድ የአውስትራሊያ ትምህርት ቤት የ8ኛ ክፍል ውድድር አሸናፊ በመሆን እና አስደናቂ ውጤት በማምስመዝገብ 20 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር በማሸነፍ ያገኘችውን ገንዘብ ለልማት ለማዋል ኢትዮጵያ ትገኛለች የተባለችን የ14 አመት ልጅ በመገናኛ ብዙሃን እና በማህበራዊ ድረ ገጾች ከማስተዋወቅ አልፈው በቢሯቸው ከልጅቷ ጋር ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል።
    ሚኒስትሩ በሪቱ ጃለታ አህመድ ገና በለጋ እድሜዋ ይህን ያህል ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ለልማት በማዋሏ ለኢትዮጵያዊያን በተለይ ደግሞ ለዲያስፖራው አርአያ መሆኗን በይፋ አውጀው ነበር። ወጣቷ የሽልማት ገንዘቡን በሙሉ አባቷ አቶ ጃለታ አህመድ በተወለዱበት በምስራቅ ሀረርጌ፣ ጋራ ሙለታ፣ ትምህርት ቤት ልታሰራበት ማቀዷን ለጋዜጠኞች በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተገኝታ ከሚኒስትሩ ጋር በጋራ በሰጠችው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ይፋ ያደረገች ሲሆን  ገንዘቡ የተገኘው ከፊሉ ከአውስትራሊያ መንግስት፣ ከፊሉ ደግሞ ከአውስትራሊያ የሮተሪ ክለብ መሆኑን ይፋ አድርጋ ነበር።
    ይሁንና ሸልማቱን አዘጋጀ የተባለው ባደን ፓወል ኮሌጅ በመባል የሚጠራው የመንግስት ትምህርት ቤት ስለጉዳዩ ምንም የሚያውቀው ነገር ባለመኖሩ ግራ በመጋባት ጉዳዩን ለምርመራ ወደ ፖሊስ መምራቱን ለማረጋገጥ የቻልን ሲሆን የአውስታራሊያ መንግስት እና ሮታሪ ፋውንዴሽን በበኩላቸው ለአዲስ ቮይስ በተናጠል በሰጡት መግለጫ እንዳረጋገጡት ለታዳጊዋ ምንም አይነት ገንዘብ አለመስጠታቸውን እንዲሁም ስለ እርሷም ሆነ ስለተባለው ውድድርና ሽልማት ሰምተው እንደማያውቁ አረጋግጠዋል።
    የአውስትራሊያ የውጭ ጉዳይና ንግድ ሚኒስቴር በጹሁፍ በላከልን መግለጫ አንደገለጸው የአውስትራሊያ መንግስት በኢትዮጵያ ጋራ ሙለታ ትምህርት ቤት ለማሰራት 10 ሚሊዮን ዶላር ሰጠ መባሉን አስተባብሏል። ሚኒስቴሩ አክሎም በኢትዮጵያ ለትምርት በቀጥታ ድጋፍ ባይሰጥም ኢትዮጵያ ከሌሎች ሃገሮች ጋር ተጠቃሚ በሆነችበት አለም አቀፍ የትምህርት የጋራ ትብብር (Global Education Partnership) በኩል ድጋፍ እንደሚሰጥ ጠቁሞ ኢትዮጵያ በትብብሩ በኩል በሚሰጠው የገንዘብ እርዳታ ተጠቃሚ ነች በማለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ጄና ሃንድ አክለው ገልጸዋል።
    በአውስትራሊያ የሮታሪ ፋውንዴሽን ስራ አስኪያጅ የሆኑት ብሩስ አለን በበኩላቸው ስለ ተሸላሚዋም ልጅም ይሁን ስለሽልማቱ ከዚህ በፊት ሰምተው እንደማያውቁ አስገንዝበው ድርጅቱ የተባለውን ያህል መጠን ያለው ገንዘብ እንኳን ለልጅ ሊሰጥ ለራሱም የበጎ አድራጎት ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ በቂ ገንዘብ እንደሌለው አስረግጠው ተናግረዋል። ስራ አስኪያጁ አክለው እንደገለጹትም ባለፈው አመት የበጀት አመት ሮተሪ በ አውስትራሊያ ያሰባሰበው ገንዘብ መጠን 5.6 ብቻ መ
    Bruce Allen.jpg
    ሆኑን ጠቁመው 10 ሚሊዮን ዶላር ለልጅቷ በሽልማት መልክ ሰጠ መባሉ በጣም የሚያሳዝን ክስተት መሆኑን ገልጸዋል። ባለፈው አመት ሮታሪ ኢንተርናሽናል በአለም አቀፍ ለትምህርት ነክ እንቅስቃሰዎች የሰጠው ገንዘብ 6.5 ሚሊዮን ዶላር በቻ የበረ ሲሆን ይህም ገንዘንብ ለ66 ፕሮጄክቶች መከፋፈሉን ለማወቅ ተችሏል።
    ከዚህ በፊት በአለም ላይ ተሰምቶና ታይቶ የማይታወቀውን ይህን “ታልቅ ውድድር” እና የ20 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት አዘጋጀ የተባለው የአውስትራሊያው የመንግስት ትምህርት ቤት1800 ተማሪዮችና 180 ሰራተኞች የሚሆኑ ያለከፍያ በበጎ አቃድ የሚሰሩ ሰራተኞች ያሉት ሲሆን አመታዊ በጀቱ 12 ሚልዮን የአውስትራሊያ ዶላር ነው። ይህም ማለት የትምህርት ቤቱ አመታዊ በጀት ለ14 አመቷ ልጅ ሰጠ ከተባለው ሽልማት በ8 ሚሊዮን ዶላር የሚያንስ ሲሆን የሽልማት ገንዘቡን ትምህርት ቤቱ እንዴት እንዳሟላው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩም ይሁኑ ተሸላሚዋ በጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ ማብራሪያ አልሰጡም።
    ሌላው አስገራሚ ጉዳይ በሪቱ ሽልማቱን አገኝ በተባለው ያለፈው የበጀት አመት የአውስትራሊያ መንግስት በገዘብ እጦት ምክንያት ከሰሃራ በታች ላሉ የአፍሪካ አገሮች የሚሰጠውን እርዳታ መጠን ከ225 ሚሊዮን በ37በመቶ በመቀነስ ወደ 133 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር በመቀነሱ በአለም አቀፍ ደረጃ ሲተች የበነረ ሲሆን የበጀት ቅነሳ ያደረገው ለልጅቷ ለመስጠት አለመሆኑን ግን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ መግለጫ ለመረዳት ተችሏል።
    ይሁንና ይህ ጉዳይ በዙዎች ዘንድ ሆን ተብሎ ለስውር አልማ የዋለ የህወሃት ውስብስብ ተንኮል ጋር የተያያዘ ነው በማለት ጥራጣሪያቸውን በስፋት በመግለጽ ላይ ይገኛል ።