Monday 13 April 2015

ወያኔ ካለው በላይ የሚያሳይና ከሚያውቀው በላይ የሚናገር ግብዝ መንግስት መሆኑ....

ዜና /01 07 2007 ዓ.ም
አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ በወያኔ መንግስት ላይ ማንኛውንም ኃይል ወይንም የአፀፋ ግብረ ኃይል በየትኛውም፣ ጊዜ በማናቸውም ቦታ ለማሳረፍ ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ፡፡
ሰሞኑን ወያኔ እየፈፀመው ከሚገኘው ከፕሮፖጋንዳ ፍጆታነት የማያልፍ የአየር ላይ ተዋጊ አውሮፕላን ትርኢት፣ የእግረኛና የሜካናይዝድ ውጊያ ልምምድና ከቦታ ቦታ የሠራዊት ጉዞ አንፃ የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ወታደራዊ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር አሰፋ ማሩ
“ወያኔ ካለው በላይ የሚያሳይና ከሚያውቀው በላይ የሚናገር ግብዝ መንግስት መሆኑ ምንጊዜም ቢሆን መዘንጋት የለበትም፡፡” ብለዋል፡፡
ኮማንደር አሰፋ አያይዘውም
“ወያኔ ሁለቱም እግሮቹ ከጉልበቱ ላይ እሱ የህዝቡን አንገት ለመቅላት ከዘር ሰገባ በመዘዘው ስለታም ሰይፍ ተቆርጠው ቁመቱ እጅግ በጣም ድንክ ሆኗል፡፡ ሰው ሰራሽ እግሮች ቀጥሎ ወደ ላይ በመንጠራራት ነው ያደገ ለመምሰል እየሞከረ የሚገኘው፡፡
በህዝቡ ፊት የሚያደርጋቸው ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች የምናብ ፈጠራ ፍሬዎች እንጂ የጦር ሜዳ ዓለም ነፀብራቆች አይደሉም፡፡ አንድ ገበሬ ገና ለገና ንብ ይገባልኛል ብሎ ተስፋ በማድረግ ብቻ በእበት ለቅልቆ በሰም ጭስ በማጠን ትልቅ ዛፍ ላይ በሰቀለው ባዶ ቀፎ የሚመሰለው ህወሓት ያሁን ጊዜ እንቅስቃሴዎቹ ሁሉ በራስ ካለመተማመንና ከፍርሃት የመነጩ ናቸው፡፡ ዛፍ ላይ የተሰቀለ ባዶ ቀፎ ንብ ሳይኖረው ማር በውስጡ ሊከማችበት አይችልም፡፡ መምሰልና መሆን ልዩነታቸው የትየለሌ ነው፡፡ ደግሞም እዩኝ እዩኝ ያለ ቆይቶ ደብቁኝ ደብቁኝ ማለቱ ሳይታልም የተፈታ ነው፡፡” በማለት ገልፀዋል፡፡
ኮማንደሩ እንዳሉትም ወያኔ በእንድ መልክ በወታደራዊ አቅሙ የተባ መስሎ ለህዝቡ ለመታየት ይጣጣራል፤ በሌላ መልኩ ደግሞ እንደ ሸንኮራ መጥጦ ከተፋቸው የቀድሞ ሠራዊት አባላት እግር ስር ሳይቀር እየወደቀ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም የህወሓት ጀነራሎች በየመንደሩ እየዞሩ የገበሬ ታጣቂዎችን ዘበመሰብሰብ
“ጦርነት ዓይኑን አፍጥጦ መጥቶብናል፤ ሠራዊታችን እየፈረሰ ወደ ኤርትራ በመኮብለልና የታጠቁ ቡድኖችን በመቀላቀል መዋጋት እንደማይፈልግ አቋሙን እየገለፀልን ነው፡፡ እባካችሁን ባይሆን እናንተ እርዱን አስፈላጊውን ድጋፍ እናደርግላችኋለን፡፡” እያሉ በመማፀን ላይ እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል፡፡
የአርበኞ ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ወታደራዊ አዣዥ ከማንደር አሰፋ ማሩ
“አርበኞች ግንቦት 7 ህዝቡ እንዲያደርግ የሚፈልገውንና የሚጠበቅበትን ማንኛውንም ተግባር ሁሉ በአስፈላጊው ጊዜና ቦታ ለመፈፀም ዝግጁ ነው፡፡” ካሉ በኋላ
“ህዝቡ ደግሞ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ የተጫነውን የባርነት ቀንበር አልሸከምም ብሎ እምቢተኛ መሆንና የትጥቅ ትግሉን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ከመደገፍ ባለፈ በባለቤትነት ማስኬዱን በተጠናቀረ ሁኔታ መቀጠል አለበት፡፡” ሲሉ የኢትዮጵያን ህዝብ አሳስበዋል፡፡
በማህበራዊ ድረ-ገፆች አማካኝነት ነፃነት በተራቡ ወጣቶች ቀስቃሽ ነት የተጀመረው ዝርዝር ሳንቲሞችን በመሰብሰብ ለወያኔ መንግስት ፍፁም አምባገነናዊ አገዛዝ እምቢተኛነትን የመግለፅ ሂደቱ አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡
በልዩ ልዩ የኢትዮጵያ ከተሞች የሚኖሩ እምቢተኛ የህብረተሰብ ክፍሎች በትንሹ የ3 መቶና የ4መቶ ብር ሳንቲሞች በየጓዳው እያከማቹ ተቃውሟቸውን በመግለፅ ላይ ይገኛሉ፡፡ አንድ ብር በ0.75 ሳንቲም መመንዘር የጀመረባቸው ከተሞች እንዳሉም ታውቋል፡፡

No comments:

Post a Comment