Saturday 9 April 2016

17 ዓመት ሙሉ መታኮስ ይኖራል ብላችሁ አትጠብቁ

ብዙ ሰዎች የጥይት ድምፅ ካልሰሙ ፣ ዛሬ በተደረገው ውጊያ ይሄን ያህል ሞተ ይሄን ያህል ቆሰለ የሚል ዜና ካልሰሙ እየተደረገ ያለው ትግል እውነት አይመስላቸውም። ወደዳችሁም ጠላችሁም ወያኔን በቁሙ የማፍረስ ስራ በሚገርም ሁኔታ እየተሰራ ነው። 2008 ከገባ በኋላ እንኳን በሀገሪቷ በአራቱም ማዕዘን አስገራሚ ህዝባዊ ንቅናቄን መፍጠር ተችሏል። ልክ እንደወያኔ 17 ዓመት ሙሉ መታኮስ ይኖራል ብላችሁ አትጠብቁ አሁን እየተሰራ ያለው ስራ ስርዓቱን በቁሙ የመግደል ስራ ነው። ስርዓቱ መሞቱ ከተረጋገጠ በኋላ የቀብሩ እለት ከባድ የተኩስ ልውውጥ ሊኖር ይችላል። ከዛ ባለፈ ረዥም ዓመታት የሚፈጅ የተኩስ ልውውጥና ብዙ ሕይወት የሚቀጠፍበት ነገር አትጠብቁ ምክንያቱም ትግሉ የሚመራው በተማሩ ሰዎች ስለሆነ።

Tuesday 5 April 2016

መክሸፍ ባሀል በመሆኑ ዛሬ ኢትዮጵያ በሁሉም ነገር ከአብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገሮች በታቺ ነች፣

የዛሬ ትውልድ የቀዳማዊ ሀይለ ስላሴን ዩኒቨርስቲ ታሪክ አያቅም፣በአስራ ዘጠኝ ሀምሳዎቹ በአፍሪካ ውስጥ የሚወዳደረው ዩኒቨርስቲ አልነበረም፣ በምእራብ አፍሪካ ከናይጀርያና ከጋና ፣በምስራቅ አፍሪካ ከኬንያ፣ከታዛንያና ከዩጋዳ ነፃ ትምሀርት እየተሰጣቸው ይማሩ ነበር፣ ሮበርት ኡጎ የሚባለው የቀዳማዊ ሃይለ ስላሲ ምሩቅ የኬንያ የውጭ ጉዳ ምኒስተር ነበር፣ጆርጅ ማጎምቤየሚባለው የታንዛንያ ወጣት በሁዋላ በብዙ ሀገሮች በኢትዮጵያም ጭምር አምባሳደር እየሆነ ሰርቷል፣ የኢትዮጵያ አየር ሀይልም፣ የኢትዮጵያ አየር መገድም ለብዙ የአፍሪካ አገሮች የዘመናዊ እውቀትና ጥበብ ምጮች ነበሩ።መክሸፍ ባሀል በመሆኑ ዛሬ ኢትዮጵያ በሁሉም ነገር ከአብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገሮች በታቺ ነች፣ ቁልቁል መውረድ ባሀል ሲሆንና ሀዝብ እሪ! ሳይል ሳይጮሀና ሳያለቅስ ገደል አፋፍ ላይ የደረሰ ይመስለኛል።
#ከአዳፍኔመፅሀፍገፅ22የተወሰደ።

Saturday 2 April 2016

የኢትዮጵያ የታሪክ ፈተናዎች እና የሚጋጩ ህልሞች- የኢሕዴግ ቆርጦ ቀጥል ፖለቲካ

የዶ/ር መራራ ጉዲና ምልከታ
በተቃዋሚ ጎራ፣ ብዙ ሳይንቀሳቀስ እያየሁ ያለሁት የኦሮሞና የአማራ ልሂቃን ፖለቲካ ነው። የሁለቱም ልሂቃን ፖለቲካ በዋናነት በሁለቱ ጫፎች ላይ ቆሞ ገመድ ከመጓተት ወደመሃል መጥቶ የጋራ ዴሞክራቲክ አጀንዳ መቅረጽ አላስቻለቸውም። ብዙዎቹ ሂሳብ የማወራረድ ፖለቲካን የዛሬ 30 እና 40 አመታት ብቻ ሳይሆን የዛሬ 130 እና 140 አመታት በፊት የነበረውም ጭምር የታሪክ ሂሳብ እንተሳሰብ የሚሉ ይመስሉኛል። የኦሮሞ ልሂቃን ዋናው ችግራቸው የጋራ የፖለቲካ አጀንዳ ለመቅረጽ ከመጣር ይልቅ ለብቻቸው የሚያደርጉትን ትግል የመንግስተ ሰማያት አስተማማኝ መንገድ አድርገው መምለካቸው ነው።
የአማራው ልሂቃን ዋናው በሽታቸው በዋናነት በአማራው ልሂቃን የተፈጠረችው ኢትዮጵያ በዋናነት እንደዛው ትቀጥል መቀጠለም ትችላለች የሚል ነው።
የሁለቱም ልሂቃን ያለፉት አርባ አመታት ጉዞ ሌኒን እንደሚለው "የሞኝ ሩጫ ፍጥነት አይጨምርም" አይነት ነው። በእኔ እምነት ሁለቱም ከታሰሩበት የታሪክ እስር ቤት ወጥተው በጋራ የዴሞክራቲክ አጀንዳ ላይ ተስማምተው በመሃል መንገድ ላይ ካልተገናኙ የኢትዮጵያ ፖለቲካ በአሁኑ ትውልድ ዘመን ፈቀቅ የሚል አይመስለኝም።
ዶ/ር መራራ ጉዲና
የኢትዮጵያ የታሪክ ፈተናዎች እና የሚጋጩ ህልሞች-የኢሕዴግ ቆርጦ ቀጥል ፖለቲካ

የትግራይ ድንበር እስከ ተከዜ ወንዝ ነዉ ብለዉ ያምናሉ የተባሉ....

ሰበር መረጃ . . ወያኔ በአርማጭሆ ዙሪያ የቤት ለቤት አሰሳ ሊያካሂድ መሆኑ ተሰማ!!
በወታደራዊ እምነቱ እየተመናመነ ዉስጥ ለዉስቱ እየተበላላ የመጣዉና የመጨረሻዉ ገደል ጫፍ ላይ የሚገኘዉ የወያኔ ስርአተ ቀብርን በማስፈጸሙ ስራ ላይ እየተጉ የመጡት የነጻነት ሐይሎችን ይረዳሉ፣ ያግዛሉ፣ መረጃ ይሰጣሉ እራሳቸዉን የዉስጥ አርበኞች ብለዉ እያደራጁ ነዉ ከጀርባቸዉ አርበኞች ግንቦት 7 አለ የተባሉ የ24ተኛ ክ/ጦር አመራሮች እየታደኑ ይገኛሉ።
የራሱ ጅራፍ እራሱን እየገረፈዉ የሚገኘዉ የትግራይ ነጻ አዉጭ ቡድን ከፍተኛ አመራሮች እየሸሹ ወደ ጎረቤት ሐገር ገብተዋል።
የዉስጥ አርበኞችን አድናለዉ ያለዉ የወያኔ ወታደራዊ ደህንነቱ የራሱን ቀንደኛ ሐይሎች በመብላቱ በመላዉ ሐገሪቱ እየተስፋፉ የሚገኙት የዉስጥ አርበኞች ደስታቸዉን ሲገልጹ ሰንብተዋል ! ! ! በመሆኑም ከዚህ ጋር በተያያዘ ለወያኔ አይታዘዙም፣ በወልቃይት ትግሬነት አይስማሙም፣ የትግራይ ድንበር እስከ ተከዜ ወንዝ ነዉ ብለዉ ያምናሉ የተባሉ የአርማጭሆ ገበሬዎችን ትጥቅ ለማስፈታት የቤት ለቤት አሰሳ እንዲደረግ የወያኔ ሹማምንቶች ተስማምተዋል በመሆኑም መላዉ የጎንደር ህዝብ ትጥቅህን እንድትጠብቅ በጥብቅ እናሳስባለን ትጥቅህ ክብርን የምታረጋግጥበት የመጀመሪያዉ ሐይል ነዉ ትጥቅ አስፈቺዎች ላይ እየወሰድክ ያለህዉን እርምጃ አጠናክረህ ቀጥል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
( ጉድሽ ወያኔ )

Friday 1 April 2016

ይች ሀገር የኢትዮጵያዊው ናት ወይስ እንደምናያት የባዕዳኖች ናት ።

ንብረትነታቸው የኢትዮጵያ የመንገዶች ባለስልጣን የሆኑና ዋጋቸው ከ65 ሚልዬን ብር በላይ 88 የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ለጥገና ተብለው ወጥተው ከመስሪያ ቤቱ ወደትግራይ ተወስደው እንደወጡ ቀሩ ። መመለሱ ይድከማቸው ፣ ይደብራቸው ወይም መጋዘን ውስጥ ተነው ይጥፉ የታወቀ ነገር የለም ፣ ሁኖም ግን የመንገድ ባለ ሥልጣን የተባለው ማሽኖቹን ከወሰደው አካል መጠየቅ ባይችልም ከኢትዮጵያ ሕዝብ ንብረትነት እንዲሰረዙ የፌዳራል መንግሥት ከሚባለው የጠየቀ መሆኑ ተገልጿል ። እንደተባለው ወይም እንደተለመደው እንደ 10,000ቶን ቡና ለወደፊቱ እንዳይደገም ከተደገመም ለወደፊቱ እጅ እንቆርጣለን ተብሎ ይሆን አይታወቅም ። የኢትዮጵያ የሕዝብ ሀብት እንዲህ እንደዋዛ ያለምን ተቆጭ በተራ ዘራፊ እንዲህ ይወሰዳል ፣ ይች ሀገር የኢትዮጵያዊው ናት ወይስ እንደምናያት የባዕዳኖች ናት ።
ዜጋ የሚዋከብባት ዜጎች ከትውልድ መንደራቸው የሚባረሩባት ባዕዳን እንደፈለጉ የሚሆኑባት በግድ መሬት ውሰዱልን ወይም እንስጣችሁ ሱዳኖች የሚለመኑባት ሀገር