Thursday 16 April 2015

እስከመቼ በማዘን እና በቁጭት እንኖራለን???

ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ሰሞኑን የጀመረው የውጪ ዜጎችን ኢላማ ያደረገው ጥቃት ተባብሶ መቀጠሉ ተነገረ፡፡ የበርካታ ሀገራት ዜጎች በስለት እታረዱ፣ በእሳት እየተቃጠሉ፣ ንብረታቸው እየተዘረፈና እየወደመ እንዲሁም እየተገደሉ እንደሚገኝ በርካታ የአለም ሚዲያዎች ዜናውን በመቀባበል ላይ ይገኛሉ
ኬንያ ውስጥ ኢትዮጵያኖች በጅምላ እየታሰሩ ነው። ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ኢትዮጵያኖች እየተደበደቡ ፤ በድንጋይ እየተፈነከቱ ፤ በዐይን እንኳን ለማየት በሚሰቀጠጥ ሁኔታ ጎማ ታስሮባቸው ቤንዚል ተርከፍክፎባቸው በእሳት እየተቃጠሉ ነው። የመን ውስጥም እንዲሁ ያለምንም ርህራሄ ኢትዮጵያኖች በግፍ እየተጨፈጨፉ ነው። አምና በሳውዲዎች ላይ "እነዚ እርኩስ አረቦች" እያልን ፀጉር ስንነጭ ፤ ዛሬም "እነዚህ አውሬ ጥቁሮች" እያልን ብናማርር ነገ የወገኖቻችንን እጣ ፈንታ ከዚህ የከፋ ሊሆን ይችላል እንጂ በ"RIP" እና ሌሎች ላይ የስድብ ናዳ በማውረድ ለውጥ አይመጣም።
.
ለዚህ ሁሉ ስደት ፣ ውርደት ፣ ግድያና ሰቆቃ የዳረገን የህወሃት አገዛዝ መሆኑን መገንዘብ አቅቶናል?! ህንድ ፣ ጅቡቲ ፣ ሱዳን እና ሱማልያ ሳይቀሩ ፥ ከነዚህ ሀገራት የራሳቸውን ዜጎች ሲያስወጡ ፤ የኛን ወገኖች ሊያድን ፍላጉቱም አቅሙም ያለው መንግስት የሚባል አካል አለመኖሩ አያንገበግበንም!?
እስከመቼ በማዘን እና በቁጭት እንኖራለን ?? እውነት በወገኖቻችን ጭፍጨፋ ያዘንን ከሆነ ቢያንስ የተደራጁ ሀይሎችን እንርዳ ፣ እናጠናክር ፤ ውርደት ይበቃል እንበል!!



No comments:

Post a Comment