Wednesday, 13 January 2016

ዶክተር ታደሰ ብሩ ቀጣይ አጀንዳዎች ምንድናቸው?

የንቅናቂያችን ከፍተኛ አመራር ዶክተር ታደሰ ብሩ ቀጣይ አጀንዳዎች ምንድናቸው?

በመጀመሪያ

(1) “ማስተር ፕላኑ ሙሉ በሙሉ እንዲቆም ተወሰነ” ማለት ምን ማለት እንደሆነ [እስከነጭራሹ ተሰረዘ ወይስ ለጊዜው ወደኃላ ተገፋ]፣
(2) አዲስ አበባን እና ኦሮሚያን የሚመለከት ጉዳይ (የፌደራል ጉዳይ) እንዴት ኦህዴድ ብቻውን ሊወስን እንደቻለ፣ እና
(3) በመንግሥት እቅድ ላይ ፓርቲ እንዴት ውሳኔ ሊሰጥ እንደቻለ [ስለመንግሥትና ፓርቲ ዝምድና “ሆድ ሲያውቅ ..” ቢሆንም] መብራራት ይኖርበታል።

እነዚህን ነገሮች በልባችን አስቀምጠን፤ የተገኘውን ድል እያደነቅንና እያከበርን ወደ ቀጣይ አጀንዳዎች እንሂድ።

1ኛ) የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ እንዳረጋገጠው ሕዝብ ፕላኑን መቃወሙ መብቱ ነው። መብታቸውን ሲያስከብሩ ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖቻችን ጀግኖች ሰማዕታት መሆናቸው እውቅና ይሰጠው፤ ለቤተሰቦቻቸውም ካሳ ይከፈል። በዚህ ትግል የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖቻችን ተገቢው ክብር ይሰጣቸው፤ ካሳ ይከፈላቸው። የታሰሩት ሁሉ ይፈቱ፣ ይቅርታ ይጠየቁ፤ ካሳ ይከፈላቸው።

2ኛ) መብቱን ለመጠየቅ በወጣ ሕዝብ ላይ ጦር ያዘመቱ፤ የተኩስ ትዕዛዝ የሰጡ እና የተኮሱ በአስቸኳይ ህግ ፊት ይቅረቡ። ”ማስተር ፕላኑን” በሕዝብ ላይ ለመጫን የወሰኑ፤ በውድም በግድም ተፈፃሚ ይሆናል ብለው ሲደነፉ የነበሩ ባለሥልጣናት ከሥልጣን ይወገዱ፤ ላደረሱት ጥፋት በህግ ይጠየቁ። አሁን ያለው የዳኝነት ሥርዓት ተዓማኒነት የሌለው በመሆኑ ይህንን ጉዳይ የሚያስፈጽም ገለልተኛ አካል ይቋም።

3ኛ)በመላ አገሪቱ የተስፋፋው የመሬት ቅርምት ይቁም፤ ከሱዳን ጋር እየተደረገ ያለው የድብብቆሽ ስምምነት ይፋ ይሁን።

No comments:

Post a Comment