የምስራቅ አፍሪካዋ አገር ታንዛኒያ በተለያዩ ጊዜያት ወደ ግዛቷ በመግባት ወደ ደ/አፍሪካ ለመሸጋገር ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር ያደረገቻቸውን በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ስደትኞችን ወደ አገራቸው በ ሃይል ለመመልስ መዘጋጀቷን አሳወቀች። የታንዛኒያው የአገር ውስጥ ደህንንት ሹም የሆኑት ቻርልስ ኪታዋንጋን ዋቢ ያደረገው ዜና ሮይተርስ በማክሰኞ ጥር 26 /2016 እኤ አ እንደገለጸው በኢትዮጵያ የተከሰተውን መጠነ ሰፊ ረሃብን በመሸሽ ለተሳለ ኑሮ ሲሉ ለደላሎች ከ አንድ ሺህ እስከ ሁለት ሺህ ዶላር በመክፈል በታንዛኒያ እና በማላዊ በኩል ወደ ደ/አፍሪካ እና ወደ አውሮፓ ለማምራት አቅደው በአገሪቱ የጸጥታ ሃይሎች እጅ የወደቁ በርካታ ኢትዮጵያዊያኖች እና ሶማሊያዊያኖችን በሕግ አግባብነት በማሰሰ እና በእስራት በመቅጣት ወደ አገራቸው ለማባረር በከፍተኛ እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል። ታንዛኒያ በአትዮጵያዊያን ስደተኞች ላይ ጠጠር ያለ እርምጃ ስትውስድ የመጀመሪያዋ አይደለም። በቅርቡ ከ አርባ በላይ ኢትዮጵያዊያን ሰደተኞች በደላሎቻቸው “ወደ ደ/አፍሪካ እናሸጋግራችኋለን “ ተብለው ተሰፋ ከተሰጣቸው በሁዋላ በሁለት ባዶ ቤት ውስጥ ታጭቀው ሳሉ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መሆናቸው ታውቋል። ቀደም ባለው ጊዜም እኤ አ በሰኔ 29/ 2012 ቁጥራቸው 43 የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ሰደተኞች በእቃ መያዢያ/ኮንቴነር/ ውስጥ ተሸሽገው ከታንዛኒያ ወደ ደ/አፍሪካ ሲጓዙ በረሃብ ፣በውሃ ጥእም እና በአየር እጦት ታፍነው የመሞታቸው የበረካታዎችን ልብ የሰበረው ገጠመኝ አለማቀፋዊ መነጋገሪያ ሆኖ እንደነበር ይታወሳል። ጎረቤት ማላዊም አንደሁ ቁጥራቸው ከ 250 በላይ ኢትዮጵያዊያን ሰድተኞችን የጤንነቱ አያያዝ በጣም ዝቅተኛ በሆነ እና እጅግ ዘግናኝ በሆነ እስር ቤት ወስጥ በማጎር ወደ አገራቸው ለማባረር እንቅሰቃሴዎችን መጀመሯን ቀደም ሲል አሰታውቃለች። ከዚሁ ከህገውጥ የሰደተኞች ጉዳይ ጋር በተያያዘ ዜና ግብጽ ሰሞኑን አኢትዮጵያዊኣኖችን ጨምሮ የተለያዩ አገር ዜጎች የተካተቱትበት ከ 40 በላይ ሰደተኞችን በግብጹ ስነይ በረሃ በኩል ወደ እስራኤል ለመሻገር ሲጥሩ ያዝኳቸው በማለት ወደ መጡበት አገር ማባረሯን ካይሮ ፖስት ጋዜጣ ሰሞኑን ዘገቧል ሰውዲ አረቢያም እንዲሁ ሰሞኑን በአንድ በሕገውጥ አዘዋዋሪ የሶማሊያ ዜጋ አማካኝነት ደንበሯ ውስጥ ዘልቀው ሲጓዙ የነበሩ አራት ኢትዮጵያዊያን ሴቶች እና አንድ ጨቅላ ልጅ መያዛቸውን ሳውዲ ጋዜት የተባለ የአገሪው ጋዜጣ ዘገቧል። ጋዜጣው በሃተታው ላይ ተጠርጣሪው ግለሰብ በአገሪቱ የጸጥታ ሃይሎች ተይዞ አብረውት በመኪና ውስጥ ሰለነበሩት ገለሰቦቹ ማነነት ሲጠየቅ “ቤተሰቦቼ ናቸው” በማለት ህገውጥ መታወቂያ በማሳየት ለማታለል ቢሞክርም ሁሉም ተጠርጣሪዎች ከ ፖሊስ መዳፍ ከመወደቅ አላመለጡም ተብሏል።ሰውዲ አረቢያ ከ አንድ አመት በፊት በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያኖችን ከ አገሯ በገፍ ማባረሯ በሔራዊ ሃዘን እና ቁጣ መቀሰቀሱ አይዘነጋም። ታዲያ ይህ አይነቱ የረሃብ እና የመልካም አሰተዳደር እጦት ሰለባ የሆኑ የበርካታ ኢትዮጵያዊያን አሰከፊ የሰደት ጎዞ እና ያሰቡት ሳይሳካ ህይወታቸውን እሰከ ማጣት ጨምሮ ለተለያዩ ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሮአዊ ችግሮች የመዳረጋቸው እጣ ፈንታ መቼ ይቆም ይሆን? በሎ መጠየቁ እና ለችግሩ መንሴዎችም መፈትሄ ማፈላለጉ ግድ ይላል።
Saturday, 30 January 2016
ታንዛኒያ ረሃብን የሸሹ በርካታ ኢትዮጵያዊያንን “ከአገሬ ጠራርጌ አባርራልሁ” አለች ፣ግብጽ እና ሳውዲ አረቢያም ኢትዮጵያዊያኖችን ማዋከቡን ተያይዘውታል
የምስራቅ አፍሪካዋ አገር ታንዛኒያ በተለያዩ ጊዜያት ወደ ግዛቷ በመግባት ወደ ደ/አፍሪካ ለመሸጋገር ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር ያደረገቻቸውን በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ስደትኞችን ወደ አገራቸው በ ሃይል ለመመልስ መዘጋጀቷን አሳወቀች። የታንዛኒያው የአገር ውስጥ ደህንንት ሹም የሆኑት ቻርልስ ኪታዋንጋን ዋቢ ያደረገው ዜና ሮይተርስ በማክሰኞ ጥር 26 /2016 እኤ አ እንደገለጸው በኢትዮጵያ የተከሰተውን መጠነ ሰፊ ረሃብን በመሸሽ ለተሳለ ኑሮ ሲሉ ለደላሎች ከ አንድ ሺህ እስከ ሁለት ሺህ ዶላር በመክፈል በታንዛኒያ እና በማላዊ በኩል ወደ ደ/አፍሪካ እና ወደ አውሮፓ ለማምራት አቅደው በአገሪቱ የጸጥታ ሃይሎች እጅ የወደቁ በርካታ ኢትዮጵያዊያኖች እና ሶማሊያዊያኖችን በሕግ አግባብነት በማሰሰ እና በእስራት በመቅጣት ወደ አገራቸው ለማባረር በከፍተኛ እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል። ታንዛኒያ በአትዮጵያዊያን ስደተኞች ላይ ጠጠር ያለ እርምጃ ስትውስድ የመጀመሪያዋ አይደለም። በቅርቡ ከ አርባ በላይ ኢትዮጵያዊያን ሰደተኞች በደላሎቻቸው “ወደ ደ/አፍሪካ እናሸጋግራችኋለን “ ተብለው ተሰፋ ከተሰጣቸው በሁዋላ በሁለት ባዶ ቤት ውስጥ ታጭቀው ሳሉ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መሆናቸው ታውቋል። ቀደም ባለው ጊዜም እኤ አ በሰኔ 29/ 2012 ቁጥራቸው 43 የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ሰደተኞች በእቃ መያዢያ/ኮንቴነር/ ውስጥ ተሸሽገው ከታንዛኒያ ወደ ደ/አፍሪካ ሲጓዙ በረሃብ ፣በውሃ ጥእም እና በአየር እጦት ታፍነው የመሞታቸው የበረካታዎችን ልብ የሰበረው ገጠመኝ አለማቀፋዊ መነጋገሪያ ሆኖ እንደነበር ይታወሳል። ጎረቤት ማላዊም አንደሁ ቁጥራቸው ከ 250 በላይ ኢትዮጵያዊያን ሰድተኞችን የጤንነቱ አያያዝ በጣም ዝቅተኛ በሆነ እና እጅግ ዘግናኝ በሆነ እስር ቤት ወስጥ በማጎር ወደ አገራቸው ለማባረር እንቅሰቃሴዎችን መጀመሯን ቀደም ሲል አሰታውቃለች። ከዚሁ ከህገውጥ የሰደተኞች ጉዳይ ጋር በተያያዘ ዜና ግብጽ ሰሞኑን አኢትዮጵያዊኣኖችን ጨምሮ የተለያዩ አገር ዜጎች የተካተቱትበት ከ 40 በላይ ሰደተኞችን በግብጹ ስነይ በረሃ በኩል ወደ እስራኤል ለመሻገር ሲጥሩ ያዝኳቸው በማለት ወደ መጡበት አገር ማባረሯን ካይሮ ፖስት ጋዜጣ ሰሞኑን ዘገቧል ሰውዲ አረቢያም እንዲሁ ሰሞኑን በአንድ በሕገውጥ አዘዋዋሪ የሶማሊያ ዜጋ አማካኝነት ደንበሯ ውስጥ ዘልቀው ሲጓዙ የነበሩ አራት ኢትዮጵያዊያን ሴቶች እና አንድ ጨቅላ ልጅ መያዛቸውን ሳውዲ ጋዜት የተባለ የአገሪው ጋዜጣ ዘገቧል። ጋዜጣው በሃተታው ላይ ተጠርጣሪው ግለሰብ በአገሪቱ የጸጥታ ሃይሎች ተይዞ አብረውት በመኪና ውስጥ ሰለነበሩት ገለሰቦቹ ማነነት ሲጠየቅ “ቤተሰቦቼ ናቸው” በማለት ህገውጥ መታወቂያ በማሳየት ለማታለል ቢሞክርም ሁሉም ተጠርጣሪዎች ከ ፖሊስ መዳፍ ከመወደቅ አላመለጡም ተብሏል።ሰውዲ አረቢያ ከ አንድ አመት በፊት በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያኖችን ከ አገሯ በገፍ ማባረሯ በሔራዊ ሃዘን እና ቁጣ መቀሰቀሱ አይዘነጋም። ታዲያ ይህ አይነቱ የረሃብ እና የመልካም አሰተዳደር እጦት ሰለባ የሆኑ የበርካታ ኢትዮጵያዊያን አሰከፊ የሰደት ጎዞ እና ያሰቡት ሳይሳካ ህይወታቸውን እሰከ ማጣት ጨምሮ ለተለያዩ ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሮአዊ ችግሮች የመዳረጋቸው እጣ ፈንታ መቼ ይቆም ይሆን? በሎ መጠየቁ እና ለችግሩ መንሴዎችም መፈትሄ ማፈላለጉ ግድ ይላል።
At least seven people were killed yesterday in Gambella town, south of Ethiopia, during an attempted prison break. Gambela
Clashes started around ten days ago after two individuals belonging to the two tribes quarreled over land. Dozens of Nuers were arrested following the clash that tensions spiraling out of control. After heavy gun fires that lasted for hours yesterday, calm has returned to the town today, the eye witness said. Several embassies and foreign organizations based in Ethiopia have issued travel warnings to their staffs following the clashes.
Thursday, 28 January 2016
አፍራሽ ግብረ ኃይል በማሰማራት ሕገወጥ ግንባታ በሚል ሱቆቹን ማፍረሱ ቀጥሏል።
ጥር ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ክልል ዋና ከተማ ሃዋሳ በተለምዶ አረብ ሰፈር አሮጌ ገበያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኙ የበረንዳ ዳሶችን ካንድ ቀን በፊት ብቻ ማሰጠንቀቂያ በመስጠት አፍራሽ ግብረ ኃይል በማሰማራት ሕገወጥ ግንባታ በሚል ሱቆቹን ማፍረሱ ቀጥሏል። ሕጋዊ የቫትና ቲኦቲ ግብር ከፋይ የሆኑት ነጋዴዎች ሁኔታውን በመቃወም ተቃውሟቸውን ቢገልፁም፣በአፀፋው የክልሉ ፖሊስ ሰላማዊ ሰልፈኞቹን በመደብደብ አካላዊ ጉዳት ከመፈፀሙ በተጨማሪ የተቃውሞው መሪ ያሉዋቸውን ነጋዴዎች ወደ ፖሊስ ጣቢያ ወስደው ስማቸውን መዝግበው ለቀዋቸዋል። የከተማውን ውበት ያበላሻል በሚል አጥጋቢ ባልሆነ ምክንያት ቀድሞ ተፈቅዶላቸው የሰሩዋቸው የንግድ ቦታዎች የፈረሱባቸው ከ200 በላይ የሚሆኑ ነጋዴዎች ከጸጥታ ሃይሎች ጋር ተጋጭተዋል። የአካባቢው ነዋሪዎችም ድጋፋቸውን ለነጋዴዎች ሰጥተዋል። ነጋዴዎቹ በብረትና በጣውላ የከለሉዋቸውን ቦታዎች በአፍራሽ ግብረ ኃይሉ በመፍረሱ እቃዎቻቸው በዝናብና በፀሃይ ጉዳት ደርሶባቸዋል። በዚህም ምክንያት እጅግ የከፋ ኪሳራና ጉዳት እንደደረሰባቸው ለማወቅ ተችሏል። በሃዋሳ ከተማ በቅርቡ በሬክተር ስኬል መለኪያ 4.5 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ መድረሱ ይታወቃል። በተለይ በከተማዋ ውስጥ ባሉት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ የመሬት መንቅጠቀጡ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን፣ በሃዋሳ ዩንቨርሲቲ ዋናው ግቢና ሪፈራል ግቢ ውስጥ ብዙ ተማሪዎች ተጎድተዋል። በንብረት ውድመት በኩልም የትምህርት ቤቶቹ ሕንጻ ግድግዳዎች ተሰነጣጥቀው መስታወቶቻቸውም ረግፈዋል። ዛሬ ተማሪዎቹ ለ15 ቀናት ትምህርታቸውን አቋረጠው ከግቢው ወጥተው ወደ ቤታቸው እንዲሄዱ የዩንቨርሲቲው አስተዳደር ማስታወቂያ በመለጠፍ ትምህርት መቋረጡን ገልጿል።
የሸቀጥ ዋጋ እየናረ ነው
ጥር ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ተከትሎ አጠቃላይ በአሃጉሩ የሸቀጥ ዋጋ እየናረ ነው። የአፍሪካ ሕብረት የኤኮኖሚ ጉዳይ ኃላፊ የሆኑት ዶክተር አንቶኒ ሞንታይ እንዳሉት የሸቀጦች ዋጋ መውረድ፣ የዶላር የወለድ መጠን በአሜሪካ መናር፣ አሳሳቢ ድርቅና የጎርፍ አደጋዎች በሃጉሪቱ ያለውን ምጣኔሃብታዊና ማኅበራዊ ችግሮች ይበልጥ አባብሰውታል ። ዶ/ር አንቶኒ "ችግሩ በመባባሱ ምክንያት የስራ አጡ ቁጥር እየጨመረ፣ የኑሮ ልዩነት እየሰፋ፣ ጤናማ ያልሆነ የንግድ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ፣ የዋጋ ግሽበት እያስከተለ ነው " ብለዋል ወደ ውጪ የሚላኩ የኤክስፖርት ምርቶች በማሽቆልቆላቸው ምክንያት ትርፍ ባለመኖሩ የሃጉሪቱ ገቢ ቀንስዋል። ድርጅቶችም ሰራተኞችን በመቀነሳቸው የስራ አጡ ቁጥር አሻቅቧል። የውጭ ምንዛሬ እጥረቱ በከፍተኛ ሁኔታ በማደጉ በሃጉሪቱ ኢንቨስትመንት ላይ አሉታዊ ጫና አሳድሯል። የኤሊኖ አየር መዛባትን ተከትሎ በተለያዩ የአፍሪካ አገራትይ ውስጥ በአገር ውስጥና ወደ ውጪ በሚላኩ የግብርና ምርቶች ላይ አስከፊ የሆነ ተፅዕኖ ፈጥሯል።በሃይድሮ ኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫዎች ረገድም በድርቁ ሰበብ ውሃ በወንዞችና በግድቦች ውስጥ ባለመኖሩ የኃይል አቅርቦቱ ተስተጋጉሏል።ይህም በማዕድን ማምረቻዎች፣ፋብሪካዎች በመስኖ እርሻዎችና በንጹህ ውሃ አቅርቦት ላይ የከፋ አደጋ እንዲደርስ ማድረጉን የአፍሪካ ሕብረት ተሰብሳቢዎች አስተውቀዋል።
በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በአሳሳቢ የርሃብ አደጋ ውስጥ
ጥር ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በአሳሳቢ የርሃብ አደጋ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን በሚቀጥሉት ወራት አደጋው በእጥፍ እንደሚጨምር ቅድመ ጥናቶች አረጋግጠዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና ግብረሰናይ የረድኤት ተቋማት በምስራቅ አፍሪካ ውስጥ ከተከሰተው የርሃብ አደጋዎች በኢትዮጵያ ያለው ርሃብ አድማሱን በማስፋቱ ከአጠቃላይ የአገሪቱ ሕዝብ ውስጥ አንድ አምስተኛ የሚሆነው ወይም ከ20 ሚሊዮን በላይ የሚሆነው ህዝብ በርሃብ አደጋ ውስጥ እንዳለና ሁኔታዎቹ እየከፉ መምጣታቸውን ድርጅቱ አስታውቋል። በአገሪቱ በተከሰተው የአየር መዛባት ሳቢያ ወቅቱን ጠብቆ ዝናብ ባለመዝነቡ በተከሰተው ድርቅ ሚሊዮኖች ለርሃብ ሲዳረጉ ሕጻናት ያልተመጣጠነ ምግብ በማጣታቸው ምክንያት የጤና መታወክ ደርሶባቸዋል። በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች በምግብ እጦት ምክንያት ልጆች ትምህርታቸውን ለማቋረጥ ተገደዋል። ዓለምአቀፍ የረድኤት ድርጅቶች አፋጣኝ እገዛ እንዲያደርጉና ርሃብተኞችን እንዲታደጉ የተባበሩት መንግስታት ጥሪውን አቅርቧል። በድርቁ ሳቢያ ከ100 ሽህ በላይ ኢትዮጵያዊያንና ሶማሊያዊያን ባሕር አቋርጠው ወደ የመን መግባታቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ቢሮ ገልጿል። በድርቁ ምክንያት ዕድሜያቸው ያልደረሱ ታዳጊዎች ካለ ዕድሜ ጋብቻ እንዲፈጽሙ በቤተሰባቸው እየተገደዱ መሆናቸውንም ድርጅቱ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ መንገስ በሕገወጥ መንገድ ወደ ጎንደር ሲጓዝ የነበሩ 45 ክላሽንኮፍ የጦር መሳሪያዎችን ደብረሊባኖስ ላይ ያዝኩ አለ
ዜናውን የዘገባው የሕወሓት መንግስት የሚቆጣጠረው ራድዮ ፋና ነው:: ራድዮ ፋና እንዳለው ወደ ጎንደር በሕገወጥ መንገድ በቶዮታ ፒካፕ መኪና ሲጓዝ የነበሩ 45 ክላሽንኮቭ የጦር መሳሪያዎችን ደብረሊባኖስ ወረዳ ላይ ፖሊስ ይዟል:: ራድዮ ፋና ጠመንጃዎቹ ከየት እንደመጡ? ከጠመንጃዎቹ ጀርባ እነማን እንዳሉበት አልነገረንም:: ግን ራድዮ ፋና ያለው ዜና እውነት ከሆነ በየከተማው ብዙ የጦር መሳሪያዎችን የደበቁ ሰዎች አሉ ማለት ነው::
Tuesday, 26 January 2016
የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ከካርታ ስራ ድርጅት ወጥቶ በደህንነት መስሪያ ቤት እንዲሰራ መደረጉ መሬት እንደፈለጉ ለመስጠት እንዲመች ነው ተባለ
በመረጃና ደህንነት ኤጀንሲ ( ኢንሳ) ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራ አንድ ከፍተኛ ባለሙያ ለኢሳት እንደገለጸው፣ የኢትዮጵያን የመሬት መረጃ የሚሰበስብ የኢትዮጵያ ካርታ ስራ ኤጀንሲ የተባለ መስሪያ ቤት ቢኖርም፣ መንግስት ፎቶ የማንሳቱ ስራ በኢንሳ ስራ ማድረጉ የተለያዩ አላማዎችን ለማስፈጸም ነው ይላል። የመረጃ ደህንነት ኤጀንሲ በአንድ ብሄር የተያዘ፣ ከመከላከያው ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለው እንዲሁም ለወያኔ ድርጀቶችና ደጋፊዎች መሬት በመስጠት ፣ የወያኔን የፖለቲካ ኢኮኖሚ ደግፈው እንዲይዙ ለማድረግ ነው ይላል። እስካሁን 46 የፎቶ መቆጣጠሪያ ምልክቶች ተስርተው ያለቁ ሲሆን፣ የአየር ላይ ፎቶ የማንሳቱ ስራ እየተሰራ እያለ ለ2 ሳምንታት በአየር ጸባይ ምክንያት እንዲሁም በአካባቢው እየተነሳ ባለው ህዝባዊ ተቃውሞ የተነሳ የአየር መቆጣጠሪያ ምልክት ለማቆም ባለመቻሉ እንዲቆም ከተደረገ በሁዋላ፣ ፎቶ የማንሳቱ ስራ እንደገና ተጀምሯል። በመጀመሪያው ዙር የሚካሄደው የፎቶ ማንሳት ስራ ከመተማ እስከ ቋራ ያለውን ወደ 365 ኪሜ እርዝመት ያለው መሬት የሚሸፍን ሲሆን ፣ በሂደትም በቤንሻንጉል ክልል አካባቢ ያለውን ፎቶ የማንሳቱ ስራ ይቀጥላል።
አሁን አንገብጋቢው ነገር ይላል ባለሙያው፣ በጎንደርና በሱዳን እንዲሁም በጎንደርና በምእራብ ትግራይ የሚሰሩ የአየር መቆጣጠሪያ ምልክቶች እንዳይሰሩ የአካባቢው ህዝብ በንቃት መጠበቅ እንዳለበት ባለሙያው ገልጿል
Mass arrest in Konso following peoples’ demand for self-administration
ESAT News (January 25, 2016)
Federal and regional forces are conducting mass arrests in Konso, southern Ethiopia following demand by the people of Konso to have their own zonal administration. Federal government and regional security forces were reportedly trying to force a large number of detainees to sign a piece of paper that says the demand for a self-administered zone was raised by “opposition political forces namely Patriotic Ginbot 7, but not the people of Konso.”
Konso is now under the control of federal forces; and businesses and schools have been closed for three weeks now, a source told ESAT on the phone.
The source said that regional special forces have gone to door to door in the middle of the night in Fasha, Duria and Kolme Kebeles to force people to sign the papers, but were to no avail as people refused to do so.
The federal government has reportedly sacked officials of the Woreda administration, including speaker of the council, for supporting the demand by the people of Konso.
Thursday, 21 January 2016
ኦባንግ የኢህአዴግ ደጋፊ ስደተኞችን አስጠነቀቁ
ኦባንግ የኢህአዴግ ደጋፊ ስደተኞችን አስጠነቀቁ “በአስመሳይ ስደተኞች ላይ በቂ መረጃ አለ” “ክፉን በክፉ መመከት ባያስደስትም ወቅቱ ያስገድደናል” ሲሉ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር ኦባንግ ሜቶ በተለይ ለጎልጉል ተናገሩ። አገዛዙን ሸሽተው በተለያዩ አገራት ከለላ አግኝተው በስደት የሚኖሩም ሆኑ ጉዳያቸው እየታየ ያሉ ወገኖች አካሄዳቸውን እንዲያስተካክሉ አስጠንቅቀዋል።
የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናትና ህግ አውጪዎች፣ የጀርመን የኢሚግሬሽን ሃላፊዎችና ከፍተኛ የፖለቲካ ሰዎች፣ ከኖርዌይ የኢሚግሬሽን ጉዳይ ሃላፊዎችና ተዛማጅ ሃላፊነት ካላቸው የህግ ክፍሎች፣ በካናዳ በተለያዩ ደረጃ ካሉ ባለስልጣናትና ወትዋቾች (አክቲቪስቶች)፣ በስዊድን አንዲሁም በእንግሊዝ በተመሳሳይ ግንኙነት ፈጥረው እየሰሩ መሆኑንን ያመለከቱት አቶ ኦባንግ “አገራቱ የስደት ፈቃድ ካገኙ በኋላ ለስደት ዳረገን ከሚሉት መንግሥት ጋር በቅርብ እየሰሩ ስላሉ አስመሳይ ስደተኞች አስገራሚ መረጃዎች መሰብሰባቸውን አውቃለሁ” ብለዋል።
አቶ መለስ በሞቱ በወር ጊዜ ውስጥ ብቻ በካናዳ ቫንኮቨር 27 አንድ አይነት ቋንቋ ብቻ የሚናገሩ ወጣቶች ጥገኛነት መጠየቃቸውን ጉዳዩን በጥብቅ እየመረመሩት ካሉ ክፍሎች ማረጋገጣቸውንና የምርመራውን ውጤት በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙ ያመለከቱት አቶ ኦባንግ፣ “ወጣቶቹ ካናዳ የገቡት ለእያንዳንዳቸው 75 ሺህ ዶላር በማውጣት ነው። ይህን ገንዘብ ማን ሰጣቸው? እንዴት አገኙት? እንዴት ከአንድ አካባቢ (ክልል) ብቻ ሊሆኑ ቻሉ? የሚሉት ጉዳዮች ምርመራውን በያዙት ወገኖች ላይ ግራሞት የፈጠረ ትልቅ ጉዳይ ነው” በማለት የጉዳዩን አሳሳቢነት ከገንዘብ ማሸሽ ጋር በማያያዝ አመላክተዋል። ለምሳሌ አንድ ጉዳይ አነሱ እንጂ በመላው ካናዳ በተመሳሳይ የምርመራ ስራ እየተሰራ መሆኑንን ተናግረዋል።
የካናዳው አንድ ማሳያ ሲሆን በአሜሪካ ግዙፍ ቪላዎችን እየገዙ ያሉት ክፍሎች ጉዳይ ከገንዘብ ማሸሽ ጋር ተያይዞ እየተመረመረ እንደሆነ አቶ ኦባንግ አስረድተዋል። ጥገኝነት ካገኙ በኋላ “ሊገለን ሲል አመለጥነው” ያሉትን ኢህአዴግን የሚደግፉ ክፍሎች ላይም ለሚመለከታቸው ባለስልጣናትና ተቋማት ከሚቀርበው መረጃ በተጨማሪ ከፍትህ ወዳድ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ጋር ድርጅታቸው በጥምረት እየሰራ መሆኑን አቶ ኦባንግ አልሸሸጉም፡፡
በጀርመን ኑረንበርግ በኢሚግሬሽን ጉዳዮች ዙሪያ የሚሰሩ ባለስልጣናት በተመሳሳይ የምርመራ ስራ እያከናወኑ እንደሆነ ያመለከቱት አቶ ኦባንግ፣ በግል በጉዳዩ ዙሪያ መነጋገራቸውን አስታውቀዋል። የጥገኝነት ፈቃድ ካገኙ በኋላ ዲያስፖራውን በመከታተልና አገር ቤት የሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ለችግር እንዲዳረጉ የሚያደርጉትን ክፍሎች ማንነት ነቅሰው እንደሚያውቋቸው ባለሥልጣናቱ በግንኙነታቸው ወቅት እንዳረጋገጡላቸው አመልክተዋል።
“ኢህአዴግ ለጊዜው የጠመንጃ ሃይል አለው። የገንዘብ አቅም አለው። ወዳጆችም አሉት። እኛ ደግሞ በየአቅጣጫው ፍትህ ወዳድ አጋሮች አሉን። ከነሱ ጋር እየሰራን ነው” በማለት አስረግጠው የተናገሩት ኦባንግ በማንኛውም መስፈርት ስደት ላይ ያሉ ወገኖችን መከታተልና መሰለል ተቀባይነት የለውም ብለዋል።
“አሜሪካ፣ ካናዳ፣ ኖርዌይ፣ እንግሊዝ፣ ስዊድንና ጀርመን አገር ባለስልጣናቱ ከበቂ በላይ መረጃ አግኝተዋል። እኛም እየሰራንበት ያለ ተከታታይ ስራ አለ። በየአቅጣጫው የሚደረገው ትግል በቅርቡ ፍሬው መታየት ይጀምራል” የሚሉት ኦባንግ ርምጃው መወሰድ ሲጀምር ከስድስት እስከ አስራ ሁለት ዓመት እስር እንደሚያስከትል፣ ከዚያም የከፋ አደጋ እንዳለው ጠቁመዋል።
በትምህርትና በተለያዩ ስልጠናዎች ወደ ተለያዩ ዓለማት የሚሰማሩ የአገዛዙ አገልጋዮችም ቢሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸው የሚያሳስቡት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር “አገዛዙ መድቧቸው በየኤምባሲው ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች፣ የስለላ ሰዎች፣ ከፍተኛ ባለስልጣናት ምስላቸውንና ማንነታቸውን ባደባባይ አይገልጹም። በኤምባሲዎች ድረ ገጽ ላይ እንኳ ስለማንነታቸው በቂ መረጃ ለመስጠት ድፍረት የላቸውም። የስርዓቱ ባህሪና የወንጀለኛነቱ መጠን ራሳቸውን እንዲገልጹ አይፈቅድላቸውም” በማለት በተራ መደለያና ጥቅማ ጥቅም ደረታቸውን እየሰጡ ያሉ ወገኖች አካሄዳቸውን በመመርመርና የሚያስከብራቸውን ተግባር እንዲፈጽሙ ጥሪ አስተላልፈዋል።
“ምክር በመለገስ ሰፊ ጊዜ የወሰድነው ክፉን በክፉ የመመለስ እምነት፣ ክፉ እንድናደርግ የሚገፋን ድርጅታዊ አቋም ስለሌለንና የሚጠሉንን ጭምር ነጻ የሚያወጣ ግዙፍ ራዕይ ስላለን ነው” የሚል ጥልቅ አስተያየት የሰነዘሩት አቶ ኦባንግ፣ በአገራቸው መኖር ያልቻሉ ወገኖች ተሰደውም ሰላም ሲያጡ መመልከት ግን የማይቻልበት ደረጃ መድረሱን አመልክተዋል። ከዚህም በተጨማሪ እሳቸው በግል፣ ድርጅታቸው በመርህ የሚታገሉለት የሰዎች መብት መከበር ብሩህ አጀንዳ በዝምታ እንዲቀመጡ እንደማይፈቅድላቸው ተናግረዋል።
ከኖርዌይ የኢሚግሬሽን ባለስልጣናት ጋር በተገናኙባቸው ወቅቶች ይህንኑ ጉዳይ አስመልክቶ በግልጽ እንደነገሯቸው ያመለከቱት ኦባንግ ሜቶ፣ አሁን ስሙንና ዝርዝር ጉዳዩን ለመናገር ፈቃደኛ ካልሆኑት ክፍል ጋር በጋራ እየሰሩ መሆኑንን ጠቁመዋል። አኢጋን ያቋቋመው የግልጽነትና የተጠያቂነት ግብረ ሃይል አንዱና ትልቁ ስራው እንዲህ ያሉ ጉዳዮችን መርምሮና አጣርቶ ለሚመለከታቸው በማቅረብ ፍትህን መጠየቅ መሆኑንን ያመለከቱት አቶ ኦባንግ “ዝርዝሩን መናገር ቢከብድም ብዙ ስራ እየሰራንበት ያለው የስደተኞች ጉዳይ የሌሎችንም ተሳትፎና ትብብር ይጠይቃል” ብለዋል።
“በስሜት መታገል አያዋጣም” የሚል የትግል ማስተካከያ ሃሳብ ፈንጠቅ ያደረጉት አቶ ኦባንግ የስደት ማመልከቻቸው ተቀባይነት አግኝቶ የመኖሪያ ፈቃድ ካገኙ በኋላ አገር ቤት በመመላለስ፣ ህግ በመተላለፍ ለአገዛዙ የሚሰሩ በሙሉ “ብልጥና አዋቂ ነን፣ ባለጊዜዎች ነን” በሚል አስተሳሰብ የሚንቀሰቀሱ አንደማያዋጣቸው ሲያሳስቡ “ለእንደዚህ አይነቶች ሁሉም ዓይነት መንገድ አይሰራላቸውም። ግለሰቦችንና ባለስልጣናትን ሳይሆን አሰራርን በማጭበርበር ይጠየቃሉ። አገራቱ እንደ ኢትዮጵያ ሳይሆን ስራ ላይ የሚውል ህግ አላቸውና ይተገብሩባቸዋል። አሰራራቸው ሲጭበረበር ዝም የማይሉት ለማንም ሲሉ ሳይሆን ለራሳቸው ሲሉ ነው። አሰራር / ሲስተም/ ሲበረዝ የሚያስከትለውን አደጋ ስለሚረዱ የሚታገሱ ካልሆነ በቀር በዝምታ አያልፉም። በኖርዌይም ሊሆን የታሰበው ይህ ነው። አሁንም ዝርዝር መረጃ ለመስጠት እቸገራለሁ” በማለት ነው። አቶ መለስ ህይወታቸው ባለፈ ወቅት በስደት ካምፕ የሚኖሩ ጭምር ለቅሶ መቀመጣቸው በኖርዌይ ሚዲያዎች አስገራሚ ተብሎ መዘገቡ፣ በህዝቡና በፖለቲከኞች ዘንድ መነጋገሪያ አጀንዳ እንደነበር አይዘነጋም።
በርካታ አሳዛኝና ህሊናን የሚፈታተኑ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሆነ ያወሱት ኦባንግ ሜቶ፣ ህጻናትን በጉዲፈቻ ስም በመቸብቸብ፣ ሴት እህቶቻችንን አረብ አገራት ያለ ዋስትና በመላክ ከፍተኛ ገበያ እየሰሩ ያሉት የህወሃት ሰዎች እንደሆኑ በበርካታ ማስረጃዎች መረጋገጡን ያስታውሳሉ። አያይዘውም አገራቸውን ለቀው ለስደት የሚወጡትን ወደ ኬኒያ፣ ታንዛኒያና ደቡብ አፍሪካ ብሎም በጅቡቲና በሶማሌ በኩል ገንዘብ እያስከፈሉ የሚያሻግሩት አሁንም እነሱ ናቸው ሲሉ አስቀድመው ስለ ጠየቁት ትብብር ማሳሰቢያቸውን ያጠናክራሉ።
“በማስተዋል እንስራ” የሚሉት ኦባንግ በየአቅጣጫው መረጃ ላይ የተኙና፣ በምን አገባኝ ስሜት ዝምታን የመረጡ ወገኖች ያላቸውን መረጃ በመስጠት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ከተለያዩ አካላት ጋር እየሰራ ያለውን ስራ እንዲያግዙ አሳስበዋል። ይህንን ማድረግ አቶ ኦባንግንና እርሳቸው የሚመሩትን ድርጅት መርዳት ሳይሆን ራስንና አገርን መርዳት እንደሆነም አጽንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።
ከተቋቋመ 135ዓመታትን ያስቆጠረው የአሜሪካ ሕግ ባለሙያዎች ማኅበር (ABA) እየተባለ በሚጠራውና 400 ሺህ በላይ አባላት ባሉት የህግ ባለሙያዎች ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ከሁለት ሳምንት በፊት ንግግር እንዲያደርጉ በተጋበዙበት ወቅት አቶ ኦባንግ ሜቶ በርካታ ጉዳዮችን በማንሳት ድጋፍ ጠይቀው አዎንታዊ ምላሽ እንዳገኙ ጠቅሰዋል፡፡ በርካታ የህግ ባለሙያዎች በተገኙበት ስብሰባ ላይ በኢትዮጵያ ያለውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ፣ ኢህአዴግ ህግን ከለላ በማድረግ በዜጎች ላይ የሚፈጽመውን ወንጀል፣ ለእንደዚህ ዓይነት ተግባሩ ማስፈጸሚያም የጸረ ሽብርተኝነትን፣ የመያዶችን፣ ወዘተ ህጎች በማውጣት ዜጎችን ለእስር፣ ለስደት፣ ለስቃይ መዳረጉን፣ የፍትህ አካላቱን ህግን በሚያከብሩና ፍትህ በሚያስፈጽሙ ሳይሆን ራሱ በመሠረተው ተቋም እያመረተ ለፖለቲካ መጠቀሚያ እያደረገ መሆኑን፣ ከዚህ አልፎ ደግሞ በስደተኛነት ስም ደጋፊዎቹን ወደ ውጪ በመላክ በሃሰት የኢህአዴግ ሰለባ በማስመሰል በየምዕራቡ ዓለም የመኖሪያ ፈቃድ እንዲያገኙ በማስደረግ መልሶ ስደተኛውን እዲሰልሉና ለሥርዓቱ እንዲሰሩ እያደረገ መሆኑን፣ ወዘተ በስፋት አብራርተዋል፡፡ የባለሙያዎቹ ማኅበር ጉዳዩን በጥልቀት እንደሚያየውና ያለውን ከፍተኛ የሰው ኃይል በመጠቀም ከአኢጋን ጋር እንደሚሰራ ከሌሎች ማኀበራት ጋር በመሆንም በተለይ በምዕራቡ ዓለም የተሰገሰጉትን አስመሳይ ስደተኞች ወደ ፍትህ የማምጣቱ ጉዳይ ቅድሚያ የሚሰጠው መሆኑን ለአቶ ኦባንግና ለድርጅታቸው አረጋግጠዋል፡፡
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈቱ ጥሪዎን እንዲያቀርብ
ኢሳት (ጥር 12 ፥ 2008) የብሪታኒያ መንግስት ከቀናት በኋላ በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የአፍሪካ ህብረት ልዩ የመሪዎች ጉባዔን በመጠቀም አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈቱ ጥሪዎን እንዲያቀርብ ሪፕሪቭ የተሰኘ የብሪታኒያ የሰብዓዊ መብት ተቋም ሃሙስ አሳሰበ። በዚሁ ልዩ የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ የብሪታኒያውን የውጭ ጉዳይ ቢሮ ሚኒስትር የሆኑት ጀምስ ዱድሪጅ ወደ አዲስ አበበ ይጓዛሉ ተብሎ ይጠበቃል። ሃላፊው ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉዞ ተከትሎም የሃገሪቱ የሰብዓዊ መብት ተቋም ለጀምስ ዱድሪጅ የጹሁፍ መልዕክትን ያቀረበ ሲሆን በመልዕክቱም ሚኒስቱ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ ዋነኛ አጀንዳ እንዲያደርጉት ጠይቋል። “ወደ አዲስ አበባው የአፍሪካ ልዩ የመሪዎች ጉባዔ የሚወከሉት የብሪታኒያ ባለስልጣናት ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈታ ብርቱ ግፊት ማድረግ ይኖርባቸዋል” ሲሉ የተቋሙ የሞት ቅጣትን የሚከታተለው ክፍል ሃላፊ ማያ ፎአ አስታውቀዋል። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፈው ከተሰጡበት ጊዜ ጀምሮ የጤናቸው ሁኔታ እጅግ እያሽቆለቆለ መምጣቱ አሳስቦት እንደሚገኝም የብሪታኒያው የሰብዓዊ መብት ድርጅት ባወጣው መገለጫ አመልክቷል። በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የአእምሮ ጤንነት አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱ በሌሎች አካላት ጭምር መረጋገጡና በመግለፅ ላይ መሆኑንም ሪፕሪቭ ተቋም አክሎ አስታውቋል። ከቀናት በኋላ በአዲስ አበባ የሚጀመረው የዘንድሮው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ አጀንዳውን በሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ የሚካሄድ ሲሆን የብሪታኒያ መንግስት ይህንኑ አጀንዳ በመጠቀም ለኢትዮጵያ መንግስት የሰብዓዊ መብት ጥያቄው እንድያቀርብ ድርጅቱ ጠይቋል። በርካታ አለም አቀፍ ድርጅቶች የብሪታኒያ መንግስት አንዳርጋቸው ለማስፈታት የተለሳለሰ አቋምን ይዟል ሲሉ ተቃውሞ ሲያቀርቡ መቆየታቸው ይታወሳል።
የአውሮፓ ህብረት ጠንካራ የተባለውን ውሳኔ በኢትዮጵያ ላይ አሳለፈ
TPLF is on the verge of death
ጥር ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 7ቱ ዋና ዋና የአውሮፓ ህብረት የፖለቲካ ድርጅቶች ኢትዮጵያን በተመለከተ የቀረበውን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ አጽድቀዋል። አነስተኛ ቁጥር ያላቸው የቀኝ አክራሪዎች ብቻ ውሳኔውን ተቃውመውታል። ለህጉ መጽደቅ ከፍተኛ ትግል ሲያካሂዱ የሰነበቱት የህብረቱ የፓርላማ አባል ሚስ አና ጎሜዝ በውሳኔው መደሰታቸውን ተናግረዋል። “በጣም ጠቃሚ የሆነ ሰነድ ነው፣ በተለይ ዋና ዋና የሚባሉት የፖለቲካ ድርጅቶች የውሳኔው ሰነድ ሳይለወጥ እንዲቀጥል ማድረጋቸው ትልቅ ነገር ነው” ሲሉ አክለዋል።
የተላለፈው ውሳኔ ምን ያክል ጠንካራ ነው የተባሉት አና ጎሜዝ፣ በኦሮሞ እና በሌሎችም ኢትዮጵያውያን ላይ የተፈጸመውን ግድያ ያወግዛል፣ እስክንድር ነጋን የመሰሉ ጋዜጠኞች፣ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ ሌሎች ፖለቲከኞችም እንዲፈቱ ይጠይቀዋል ብለዋል። ባለፉት 10 አመታት በኢትዮጵያ ላይ ከተላለፉት ውሳኔዎች ውስጥ የአሁኑ ጠንካራ መሆኑን የገለጹት ሚስ አና ጎሜዝ በተለይ ዋና ዋና የሚባሉት 7ቱ የፖለቲካ ድርጅቶች እንዳለ መቀበላቸው ትልቅ ውጤት ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የህብረቱ ባለስልጣናትንና አዲስ አበባ የሚገኙ የህብረቱን ተወካዮች ለማግባባት ቢሞክርም፣ የህብረቱ የፓርላማ አባላት ግን አንቀበልም በማለት ማጽደቃቸውን አክለዋል
ከዚህ በሁዋላ የአውሮፓ መንግስታት ፣ በ7ቱ ዋና ዋና የፖለቲካ ፓርቲዎች የተደገፈውን የፓርላማ አባላቱን ውሳኔ ሊያጣጥሉት አይተው እንዳላዩ ሊያልፉት አይችሉም” ያሉት አና ጎሜዝ ፣ ይህን ካደረጉ በራሳቸው የፖለቲካ ህይወት ላይ ተጽእኖ እንደሚያመጣባቸው አስረድተዋል
ህብረቱ በቅርቡ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በኢትዮጵያውያን ላይ የፈጸሙትን ግድያና የሰብአዊ መብት ጥሰት በጽኑ አውግዟል። የ140 ሰዎች ግልጽ፣ ተአማኒ እና ገለልተኛ በሆነ አካል እንዲመረመር ጠይቋል። ጋዜጠኞችና የሰብአዊ መብት ድርጅቶች በነጻ እንዲንቀሳቀሱ ሁኔታዎች እንዲመቻቹም አሳስቧል።ለኢትዮጵያ የሚሰጠው እርዳታ የሰብአዊ መብት ጥሰቱን እንዳያባብሰው፣ ቁጥጥር ሊደረግ ይገባል ብሎአል።
በሌላ በኩል ደግሞ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ኤክስፐርቶች የጸጥታ ሃይሎች በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚወስዱትን እርምጃ እንዲያቆም ጠይቀዋል። “የተገደለውና የታሰረው ህዝብ ቁጥር መንግስት ህዝቡን እንደ አጋር ሳይሆን እንደእንቅፋት እንደሚያየው” የሚያመለክተው ነው ያሉት ኤስፐርቶች፣ ምንም እንኳ መንግስት እቅዱን መተውን ቢናገርም ግድያው ፣ ማሰሩና ከልክ በላይ ሃይል መጠቀሙ አሁንም አሳስቦናል ብለዋል።
የታሰሩት በሙሉ በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንዲሁም ድርጊቱን የፈጸሙት የጸጥታ ሃይሎች በገለልተኛ ወገን ተጣርቶ ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል።
Wednesday, 20 January 2016
የጎረቤት ጅቡቲ መንግስት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ዕቃዎች ላይ በዘመናዊ ማሽን ፍተሻን ...
ኢሳት (ጥር 11 ፥ 2008) የጎረቤት ጅቡቲ መንግስት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ዕቃዎች ላይ በዘመናዊ ማሽን ፍተሻን በማካሄድ በአንድ ኮንቴንይነር እስከ 35 ዶላር ለማስከፈል የያዘውን እቅድ በሁለቱ ሃገራት መካከል አለመግባባት መፍጠሩ ተገለጠ። ጅቡቲ የወሰደችውን አቋም ተከትሎም በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተቋቋመ ቡድን ከሃገሪቱ ጋር ድርድር እያካሄደ እንደሚገኝ ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። ጅቡቲ አዲሱን መመሪያዋን ከተያዘው ወር ጀምሮ ተግባራዊ ለማድረግ እቅድን ይዛ የነበረ ሲሆን እርምጃው በኢትዮጵያ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ አካላት ገልጸዋል። በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተቋቋመው ቡድን ድርድሩን ከሳምንታት በፊት ቢጀምርም እስካሁን ድረስ የተደረሰ ስምምነት አለመኖሩም ታውቋል። ወደብ አልባ የሆነችን ኢትዮጵያ አብዛኛው የውጭ ንግዷንና የገቢ ምርቶቿን በጎረቤት ጅቡቲ በኩል የምታካሄድ ሲሆን በአመት ወደ 1.4 ቢሊዮን ዶላ አካባቢ ገንዘብ ለአገልግሎት እንደምታወጣም ይነገራል። ሁለቱ ሃገራት ትስስራቸውን ያጠናክራል የተባለ በርካታ ስምምነቶችን መፈራረማቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ለጅቡቲ በነጻ የውሃ አቅርቦትን ለማድረግ ስምምነት ማድረጓም መዘገቡ ይታወሳል። ጅቡቲ በበኩሏ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ከወደብ አገልግሎት ጋር የተገናኙ ማሻሻያዎችን ተግባራዊ እንደምታደርግ ስትገልጽ ቆይታለች። ይሁንና ሃገሪቱ እንዲህ ያለ ክፍያን ተግባራዊ ለማድረግ እቅድ ማያዟ በሁለቱ ሃገራት መካከል አለመግባባት መፍጠሩ ተገልጿል።
Friday, 15 January 2016
Thursday, 14 January 2016
Dr. Gregory Stanton, President of Genocide Watch
"The Tigrean regime is attempting to colonize the rest of Ethiopia. One of the big worries we have, I say this with real sincerity, because this is an effectively Tigrean takeover of the whole country, do you know who will eventually pay for this? The Tigreans. The Tigreans will become hated in the country. I lived in Rwanda and in Burundi. I saw what happened when an elite basically took control of the country. In both of those countries, the Tutsi elite basically ran the countries. And so they were very much resented by the Hutus. What was the result? Genocide. I am worried not just for the ordinary people who are Oromo or Amharas or Ogadani or others, I am worried for the Tigreans. Tigreans could become victims of genocides themselves if others turn against them and try to kill them. The name of our organization is Genocide Watch. We are very worried about these kind of forces because they are natural human forces. You can see them develop." Dr. Gregory Stanton, President of Genocide Watch
Wednesday, 13 January 2016
ዶክተር ታደሰ ብሩ ቀጣይ አጀንዳዎች ምንድናቸው?
የንቅናቂያችን ከፍተኛ አመራር ዶክተር ታደሰ ብሩ ቀጣይ አጀንዳዎች ምንድናቸው?
በመጀመሪያ
(1) “ማስተር ፕላኑ ሙሉ በሙሉ እንዲቆም ተወሰነ” ማለት ምን ማለት እንደሆነ [እስከነጭራሹ ተሰረዘ ወይስ ለጊዜው ወደኃላ ተገፋ]፣
(2) አዲስ አበባን እና ኦሮሚያን የሚመለከት ጉዳይ (የፌደራል ጉዳይ) እንዴት ኦህዴድ ብቻውን ሊወስን እንደቻለ፣ እና
(3) በመንግሥት እቅድ ላይ ፓርቲ እንዴት ውሳኔ ሊሰጥ እንደቻለ [ስለመንግሥትና ፓርቲ ዝምድና “ሆድ ሲያውቅ ..” ቢሆንም] መብራራት ይኖርበታል።
እነዚህን ነገሮች በልባችን አስቀምጠን፤ የተገኘውን ድል እያደነቅንና እያከበርን ወደ ቀጣይ አጀንዳዎች እንሂድ።
1ኛ) የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ እንዳረጋገጠው ሕዝብ ፕላኑን መቃወሙ መብቱ ነው። መብታቸውን ሲያስከብሩ ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖቻችን ጀግኖች ሰማዕታት መሆናቸው እውቅና ይሰጠው፤ ለቤተሰቦቻቸውም ካሳ ይከፈል። በዚህ ትግል የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖቻችን ተገቢው ክብር ይሰጣቸው፤ ካሳ ይከፈላቸው። የታሰሩት ሁሉ ይፈቱ፣ ይቅርታ ይጠየቁ፤ ካሳ ይከፈላቸው።
2ኛ) መብቱን ለመጠየቅ በወጣ ሕዝብ ላይ ጦር ያዘመቱ፤ የተኩስ ትዕዛዝ የሰጡ እና የተኮሱ በአስቸኳይ ህግ ፊት ይቅረቡ። ”ማስተር ፕላኑን” በሕዝብ ላይ ለመጫን የወሰኑ፤ በውድም በግድም ተፈፃሚ ይሆናል ብለው ሲደነፉ የነበሩ ባለሥልጣናት ከሥልጣን ይወገዱ፤ ላደረሱት ጥፋት በህግ ይጠየቁ። አሁን ያለው የዳኝነት ሥርዓት ተዓማኒነት የሌለው በመሆኑ ይህንን ጉዳይ የሚያስፈጽም ገለልተኛ አካል ይቋም።
3ኛ)በመላ አገሪቱ የተስፋፋው የመሬት ቅርምት ይቁም፤ ከሱዳን ጋር እየተደረገ ያለው የድብብቆሽ ስምምነት ይፋ ይሁን።
ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪዎች አቶ አባይ ጸሃዬን “የመሬት ከበርቴው” ...
አቶ አባይ ጸሀዬ በዘመዶቻቸው ስም በርካታ መሬቶች መውስዳቸው፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ ባስቀመጡት ሃላፊ አማካይነት በመሬት ንግድ ከፍተኛ ጥቅም ማግኘታቸው፣ ህጋዊ ሰነድና ካርታ ያለው ቁልፍ ቦታ ከባለቤቱ ተነጥቆ ለእርሳቸው ዘመድ መሰጠቱ ሲረጋገጥ ምርመራው እንዲቆም መታዘዙ ታወቀ። በየክልሉ ተመሳሳይ ንቅዘት አለ። በህዝብና በቦሌ ክፍለ ከተማ ሰራተኞች፣ እንዲሁም ለአብነት የተጠቀሱት ንብረታቸው የተወሰደባቸው ሴት ወ/ሮ ጉዳያቸውን የትኛውም ቦታ ሲወስዱ መጀመሪያ ቀጠሮ እንደሚሰጣቸው፣ በቀጠሮዋቸው ቀን ሲሄዱ ምን ምላሽ እንደማያገኙ ጠቅሰው ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት የተጀመረው የምርመራ ስራ ይህንን ይመስላል። ቀደም ሲል ተጠሪነቱ ለአቶ መለስ የነበረው ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪዎች አቶ አባይ ጸሃዬን “የመሬት ከበርቴው” የሚል ስም ሰጥተዋቸዋል። ስያሜውም የተሰጣቸው በቦሌ ክፍለ ከተማ መሬት ሲነግዱ ስለነበር ነው። የኮሚሽኑ የፌደራል የጎልጉል ምንጭ እንዳመለከቱት አቶ አባይ ጸሀዬ መሬት ሲነግዱ እንደ ነበር የታወቀው በክፍለ ከተማው በተካሄደ ምርመራ ነው። በክፍለ ከተማው በጠራራ ጸሃይ የግለሰቦችን መሬት ሳይቀር እየቸበቸበ እንደሚገኝ ኮሚሽኑ በደረሰው ተደጋጋሚ ጥቆማ መሰረት የሚመለከተው መምሪያ መነሻ ጥናት ያዘጋጅና ምርመራው እንዲጀምር ይታዘዛል። በዚሁ መሰረት የኮሚሽኑ መርማሪዎች ስራቸውን ይጀምራሉ። የኮሚሽኑ ባለሙያዎች ምርመራ እንደጀመሩ መሬት በህገወጥ መንገድ ሲቸበቸብ እንደነበር ይረዱና ከመሬት ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ያሽጋሉ። የመሬት ልኬትም ሆነ ከመሬት ጋር የተያያዘ ስራ እንዳይሰራ ያግዳሉ። በተጨማሪም መሬት እየለኩ ሲሰጡ የነበሩ መሃንዲሶች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጎ ምርመራው በጥብቅ እንዲካሄድ ይደረጋል። ክፍለ ከተማው ክልሉን ወደ ገጠር ቀበሌዎች እያሰፋ መሬት ይከልላል። መሬታቸው የተወሰደባቸው ደካማዎችን ቦሌ ክፍለ ከተማ ካሳ ለመውሰድ ሲንከራተቱ ማየት የተለመደ ነው። አራት ዓመት፣ አምስት ዓመት ከዚያም በላይ ካሳ ሳያገኙ የሚመላለሱ ደካሞች አሁን ድረስ አሉ። ባለንብረት ለንብረቱ ካሳ የሚከፍለው አጥቶ ይንከራተታል፤ መሬት የመንግስት እንደሆነ ያወጀው መንግስት በከፍተኛ ባለስልጣኖቹ አማካይነት መሬት አየር በአየር ይቸበችባል። ይህ የአሰራሩ ግድፈት ሲሆን ለአብነት የተጠቆመው ጉዳይ አስከፊነትና የወንጀሉ ርህራሄ አልባነት እዚህ ላይ ጎልቶ ይታያል። አሳዛኝ የተባለው የምርመራ ውጤት ታሪክ የሚጀምርው እዚህ ላይ ነው። መሃንዲሶች በሙሉ ታስረው ተመረመሩ። ምርመራው በሙሉ ወደ አንድ ሰው ቢያመላክትም ያንን ሰው ደፍሮ የሚናገር ጠፋ። ይህን ጊዜ “ለምን” የሚል ጥያቄ ተነሳ። የመሬት አስተዳደር ሃላፊውና የክፍለከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ ጉዳዩ የማይመለከታቸው ተደርጎ መወሰዱ፤ መሬት በህገወጥ ስለመቸብቸቡ በቂ መረጃና ማስረጃ በቀረበበት ሁኔታ፣ መሬታቸውን በግፍ ተነጥቀው ለሌላ ሰው የተሰጠባቸው እንዳሉ ተረጋግጦ ሳለ ካርታ ላይ የሚፈርሙትና ለመሃንዲሶች ትዕዛዝ የሚያስተላልፉት የመሬት አስተዳደር እንዲታሰሩና እንዲመረመሩ አለመደረጉ በጓሮ ኮሚሽኑ የሚታማበት ጉዳይ ሆነ። “ጥርስ የሌለው አንበሳና የመለስ አሽከር” የሚለው የኮሚሽኑ ስም በስፋት ተነሳ!! “ለፀረሙስና ኮሚሽን ሌላ ጸረ ሙስና ኮሚሽን” በሚል የክፍለ ከተማው ሰራተኛ የሆኑ ደብዳቤ በመጻፍ ወቀሳ ሰንዝረው ምርመራው በወጉ እንዲከናወን ጥቆማና አስተያየታቸውን ላኩ። አንዳንድ ስማቸውንና ማንነታቸውን የደበቁ ሰዎች ጉዳዩን ለግል ሚዲያና ለመንግስት መገናኛዎች እንደሚያቀብሉ ዛቱ። ማንም ምን ቢል የሚሰማም የሚደነግጥም ጠፋ። ምርመራ ከተደረገባቸው ጉዳዮች መካከል ለአብነት የተቀመጠው ዛሬ ህንጻ በብድር ተገነብቶበት ከፍተኛ ኪራይ የሚሰበሰብበት ከመገናኛ ወደ ገርጂ በሚወስደው አዲሱ ጎዳና ዳር ላይ ያለ አንድ ቦታ ጉዳይ ሲጎተት ሚስጥሩን ገለጠው። የመረጃው ምንጭ እንዳስረዱት ምርመራውን የያዘው ባልደረባቸው እንደነገራቸው ምስጢሩ ሲገለጽ ማመን አቅቶት ነበር። ለክፍለከተማው የመሬት አስተዳደር ሃላፊ ቅርብ ተጠሪ የሆነው መሃንዲስ ምርመራ ሲካሄድበት “እንግዲያውስ እውነቱ ይህ ነው” በማለት አብራራ። በግፍ የተወሰደው ከላይ የተገለጸው ቦታ የተሰጠው ለአቶ አባይ ጸሃዬ ዘመድ መሆኑን ይፋ አደረገ። መሬቱ የቀድሞው ባለቤቶች ለመሆኑ የሚገልጽ በቂ ማስረጃ እንዳለው ቢታወቅም አለቃው አዲስ የባለቤትነት ማስረጃ ቀደም ሲል እንደነበር ተደርጎ እንዲያዘጋጅ ባዘዘው መሰረት የሰው ንብረት አሳልፎ መስጠቱን አስታወቀ። ይህን ጊዜ ምርመራው ባስቸኳይ ወደ ሌላ መርማሪ እንዲዛወር ተደረገ። የቦሌ ክፍለ ከተማ የመሬት አስተዳደር ሃላፊ አቶ መሠረት የአቶ አባይ ጸሃዬ የቅርብ የስጋ ዘመድ ሲሆኑ፣ በእርሳቸው ትዕዛዝና አጽዳቂነት በክፍለ ከተማው በርካታ ቁልፍ ቦታዎች ለዘመድ አዝማድ በሽርክና፣ ለባለ ገንዘብ በሽያጭ እንዲዘዋወሩ መደረጉ በምርመራ እንደታወቀ አስቸኳይ መመሪያ ተላለፈ። መመሪያው እስረኛው መሃንዲስ ባስቸኳይ እንዲለቀቅ፣ ምርመራውም እንዲቋረጥ የሚል ነበር። ከፍተኛ የሙስና ወንጀልና የስነምግበር ጉድለት መከሰቱን፣ በግፍ ንብረታቸውን ተቀምተው ባዶ እጃቸውን የቀሩ እንዳሉና፣ በማስፋፊያ ስም ቁልፍ ቦታዎች ከህግ ውጪ መተላለፋቸውን ይፋ ለማድረግ ሰፊ ጊዜ ወስዶ የተሰራው ስራ ሙሉ በሙሉ ይፋ ሳይሆን ተዳፈነ። የተልከሰከሰ የስራ ሪፖርት እንዲቀርብ ተደርጎ ፋይሉ ተዘጋ። ከእስር የተፈታው መሃንዲስም ደብዛ ጠፋ። የአገር ደህንነት ከበርካታ ተመሳሳይ ወንጀሎች ጋር ጉዳዩን እንደያዘው የጎልጉል ዘጋቢ አረጋግጧል። የድርጊቱ ዋና ተዋናይ የአቶ አባይ ዘመድ እንኳንስ ሊታሰሩ በእድገት የከንቲባ ኩማ ደመቅሳ አማካሪ ሆነው አዲስ አበባ አስተዳደር ተመደቡ። ዋና ስራ አሰፈጻሚው የፌደራል ስራና ከተማ ልማት ሚኒስትር ውስጥ ከፍተኛ ሹመት ተሰጣቸው። በአሁኑ ወቅት የከንቲባው አማካሪ የሆኑት የአባይ ጸሃዬ ዘመድ መሬትን አስመልክተው ኪራይ ሰብሳቢነት ስለመስፋፋቱ ክፍለ ከተሞችን ሰብስበው ይሰብካሉ። ስለ ሙስና አደገኛነት በየመድረኩ እንዲያስተምሩ ተደረገ። ድርጊቱ በርካቶችን አስቆጣ። በርካታ የወቀሳ ደብዳቤ ለኮሚሽኑ ጎረፈለት። በአካል ቀርበው ምስክርነት የሰጡና ኮሚሽኑ ሊመሰርት አቅዶት ለነበረው ክስ ምስክር ለመሆን የተስማሙ ደነገጡ። ጉዳዩ እንዲዳፈን ስለተደረገበት ምክንያት ሲያስረዱ “በየትኛውም ደረጃ ያሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ በደህንነት ውስጥ ያሉ ባለስልጣናትና መካከለኛ ደረጃ ሃላፊዎች በግልጽ ሙስና ውስጥ መዘፈቃቸው በመረጃ ቢቀርብም ኮሚሽኑ እርምጃ የማይወስደው ሙስና አንዱ የስርዓቱ እድሜ ማራዘሚያ መንገድ በመሆኑ ነው” ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል። “ኢህአዴግን እያገለገሉ ያሉ ባለስልጣኖች ህወሃትን በሚገባ መከራከር የማይችሉትና በታዛዥነት እያጎበደዱ ለመኖር የሚገደዱት የገቡበትን የሙስና ማጥ ስለሚያውቁት ከተቃወምን እንታሰራለን” በሚል ፍርሃቻ መሆኑን የኮሚሽኑ ባልደረባ ለጎልጉል የአዲስ አበባ ምንጭ ተናግረዋል። ባለሙያው አያይዘውም “በአገሪቱ የተንሰራፋው ሙስና አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል፤ ከላይ እስከታች ተበለሻሽቷል” ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል። “ባለሥልጣናትን በሙስና ማበስበስ” የስርዓቱ ዋንኛ የማኮሰሻና የማዋረጃ ስልት እንደሆነ የተለያዩ ማስረጃዎችን በማጣቀስ “አቶ መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ” በሚል ርዕስ ባቀረብነው ቃለ ምልልስ ማስነበባችን ይታወሳል። ኢህአዴግ ለትምህርት ውጪ አገር የላከቸውና ስማቸውን ለጊዜው መግለጽ ያልፈለጉት ተናጋሪ “ስርዓቱ በስብሷል” ባይ ናቸው። “ባለኝ መረጃ መሰረት የኔ ስጋት እነዚህ ያለቀረጥ የሚነግዱ፣ ገንዘብ የሚያቀባብሉ፣ የገንዘብ ዝውውር ላይ የተሰማሩ፣ ድርጅት ያላቸው፣ በቅጽበት ተመንጥቀው ባለሚሊዮኖች የሆኑ፣ የባንክ ብቸኛ ተጠቃሚዎች፣ ሸቃጮችና አወራራጆች ከትንሽ እስከ ትልቅ ስራውን የሚሰሩት ከባለስልጣናት ጋር ነው። ከመከላከያ አመራሮች ጋር ነው። ከደህንነትና ከዋናው የስልጣን እርከን ጋር በመመሳጠርም ነው” በማለት ቃለ ምልልስ አድራጊው በውል የሚያውቁትን ተናግረዋል። አያይዘውም “ስርዓት ሲበሰብስ ልዩ ምልክቱ ትናንሽ መንግስታት ማቆጥቆጣቸው ነው። በኢህአዴግ መበስበስ አቶ መለስን ጨምሮ በርካቶች ይስማማሉ። ኢህአዴግ መዓዛውን አልቀየረም የሚሉት በአገሪቱ ድፍን ቆዳ ላይ የራሳቸውን መንግስት የተከሉ ተጠቃሚዎች ብቻ ናቸው። እነሱ ክሬሙን እየላሱ ስለሆነ የመበስበስ አደጋ አይታያቸውም። ስለመበስበስ ለማሰብም ጊዜ የላቸውም። የበሰበሰው ነገር ሲናድ የሚበላው ግን አስቀድሞ እነሱን ነው። ምክንያቱም አቶ መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ በጣም ትልቅ ነው” በማለት ፍርሃቻቸውን ይገልጻሉ። የፌዴራል መንግስት የስነ ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን በአገሪቱ የተንሰራፋውን ሙስና በገለልተኛ ወገን አስጠንቶ ያገኘውና ይፋ የተደረገው ውጤት አስደንጋጭ መሆኑ ይታወሳል። በዚሁ ጥናት መሰረት ፖሊስ፣ ፍርድ ቤቶች፣ አጠቃላይ የፍትህ ተቋማትና ራሱ ጸረ ሙስና ኮሚሽን ቀዳሚ ሙስና የተንሰራፋባቸው ተቋማት መሆናቸውን ማረጋገጡ፣ ተቋማቱም በጥናቱ ቅር መሰኘታቸውን በመግለጻቸው በዝርዝር ይቀርባል የተባለው ጥናት እስካሁን ይፋ ሊሆን አለመቻሉም ታውቋል፡፡ የፊታችን አርብ ቃለ መሃላ የሚፈጽሙት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ እንደ አቶ መለስ የጸረ ሙስና ኮሚሽን ተጠሪነቱ ለእርቸው ስለሆነ አዲስ በሚያቋቁሙት ካቢኔ ውስጥ መካተት የሌለባቸውን የነቀዙ ባለስልጣናት ለመለየት ፋይላቸውን ከኮሚሽኑ መውሰድ እንደሚችሉ ተጠቁሟል።
(በጎልጉል ሪፖርተር)