(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)
"አማራ ክልል" እየተባለ የሚጠራው ሹም እና የህወሓት ጉዳይ አስፈፃሚ የሆነው ገዱ አንዳርጋቸው በዛሬው ዕለት ወደ አርማጭሆ ሙሴ ባምብ ከተማ አምርቶ የአካባቢውን ህዝብ ለማወያየት ሞክሮ ያለምንም ውጤት በውርደት ተመለሰ፡፡
====================================================
የህወሓቱ አሽከር ገዱ አንዳርጋቸው ዛሬ ጠዋት በከፍተኛ ወታደራዊ አጀብ ከባህር ዳር አርማጭሆ ሙሴ ባምብ ገብቶ የአካባቢውን ህዝብ በሦስት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ለማነጋገር ሞክሯል፡፡
በስብሰባው ላይ የተነሱት ሦስቱ የመወያያ አጀንዳዎች፦
1. በጎንደር የተከሰተው የእርስበርስ ግጭት
2. የወልቃይት ህዝብ የማንነት ጥያቄ እና
3. የኢትዮ-ሱዳን ድንበርን በሚመለከት ናቸው፡፡
ገዱ አንዳርጋቸውና ሌሎች የብአዴን ካድሬዎች በመሩት ስብሰባ ላይ የተገኘው የአርማጭሆ ህዝብ በጎንደር የተከሰተውን የእርስበርስ ግጭት ህወሓት እንደጠነሰሰው እና የእሱ ዲቃላ የሆነው ብአዴን እጁ እንዳለበት ገልጿል፡፡ ብአዴን የአህያ ባል ሆኖ ህወሓት ለተባለ የቀን ጅብ አሳልፎ ሰጥቶ የወልቃይትን ህዝብ እያስበላው እንደሚገኝም ህዝቡ ጨምሮ ተናገሯል፡፡
ድንበሩን በሚመለከት ደግሞ
"እናንተም ሆናችሁ ህወሓት የአገሪቱን ዳር ድንበር ማስከበር ስላልቻላችሁ፣ ህዝቡንም መምራት ስለተሳናችሁ ስልጣናችሁን ልቀቁ አርበኞች ግንቦት 7 ይምራን..." በማለት ድፍረት በተሞላበት ሁኔታ በአንድነት ጠይቋል፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ ለሱዳን ተቆርሳ የምትሰጥ አንድ ጋት መሬት እንኳን ብትኖር ህዝቡ ከውስጥም ከውጭም በአንድነት ለመዋጋት ቆርጦ እንደተነሳና ህወሓት ከባድ ዋጋ እንደሚከፍል ማስጠንቀቂያ ጭምር አስተላልፏል፤ ጀግናው የአርማጭሆ ህዝብ፡፡
በአጠቃላይ በአርማጭሆ ሙሴ ባምብ በህወሓት አሽከር ገዱ አንዳርካቸው እና በህዝቡ መካከል በዛሬው ዕለት የተካሄደው ውይይት ከፍተኛ ንትርክና እሰጥ አገባ እንዲሁም የከረረ ቁጣና ተቃውሞ የተሞላበት ሲሆን ከቀኑ 9፡30 ላይ ያለምንም ውጤት በአገዛዙ ውርደት የተላበሰ ሽንፈት ብቻ ተቋጭቷል፡፡
Wednesday, 23 December 2015
Breaking news
ይሄ ሁሉ ግፍ ሲደርስብን ....
እጅግ ያሳዝናል--- ቆይ ይሄ ሁሉ ግፍ ሲደርስብን ምን እስከምንሆን ነው የምንጠብቀው?
የአቃቂ ቃሊቲ ምእመናን ለሃምሳ አመታት ለጥምቀት በአልና ለሃይማኖታዊ ስርአት ስንገለገልበት የኖርነውን አባቶቻችን
በብዙ ተጋድሎ ከነ ቅድስናው ጠብቀው ያቆዩልን ጥንታዊ መንፈሳዊ ስፍራ በክፍለ ከተማው የተወሰኑ ባለስልጣናት
ከቤተክርስቲያን ተነጥቆ ህገ ወጥ ካርታና ፕላን አውጥተውበት በአሁን ሰአት በስፍራው ካፊቴሪያ እየሰሩበት ይገኛል፡፡
እጅግ አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ ቤተክርስቲያን ከካፊቴርያው ጋር በጋራ ጥምቀተ ባህሩን እንድትጠቀም ወስነውባታል፡፡
ህዝቡም አቤቱታውንና ጩኸቱን በተለያየ ሁኔታ እያሰማ ቢገኝም ባለስልጣናቱ የህዝቡን ጥያቄ ለማፈን የተለያዩ
ጫናዎችን እያደረጉ ይገኛል፡፡
ሰበር ዜና ህወዓት በጎንደር ህዝብ ላይ የጅምላ ግድያ..
ሰበር ዜና ህወዓት በጎንደር ህዝብ ላይ የጅምላ ግድያ ለመፈፀም የትግራይ ተዋጊ ሚሊሻወችን እና አጋዚወችን ማሰለፉ ተሰማ።
ላለፉት ሳምንታት የተለያዮ የሁለቱ ክልሎች ባለስልጣናት እና የህወዓት ትግራይ የሚመራው የፌደራል ባለስልጣናት የወልቃይት ህዝብ እየሰበሰበ ሲያናግር ቢቆይም የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ እኛ አማራ እንጂ ትግራውያን አይደለንም በሚል ሰጣ ገባ ባለስልጣናት ያደረጉት ስብሰባወች ሁሉ ውጤት አልባ ሆነዋል። በዚህ ምክንያት የትግራይ መስተዳደር የወልቃይት ጠገዴ መሬት የትግራይ መሬት ነው በሚል ለአንዴ እና መጨረሻ ያለውን እልባት ለመስጠት የጦርነት ዘመቻ ማወጁን መረጃወች አመልክተዋል።
የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ መላው የአማርውን ህዝብ ከጎናችን ሁኑ ሲሉ በተወካዮቻችው ለሰሜን ሸዋ፣ ወሎ ፣ጎንደር እና ጎጃም ህዝቦች በርካታ ወረቀቶችን በመበተን ጥሪ ማድረጋቸው ተሰምቷል
Sunday, 20 December 2015
ዘአቃቂ ቃሊቲ ጥምቀተ ባህር
ሰበር ዜና
*
ዘአቃቂ ቃሊቲ ጥምቀተ ባህር
*
ስማቸው ለጊዜው የማይገለጽ የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ በጸጥታ ሃይሎች ከመኖሪያ ቤታቸው ተወስደው ባልታወቀ ስፍራ ለረጅም ሰአት እንዲቆዩ ከተደረገ በዋላ ማምሻ ላይ መለቀቃቸው ተሰማ፡፡ የአቃቂ ቃሊቲ ጥምቀተ ባህር ይዞታን ለማስከበር በተዋቀረው ኮሚቴ ውስጥ ሲሳተፉ የነበሩ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከሚገኙ ዘጠኙ አድባራት መካከል የአንዱ ደብር አለቃ የሆኑት ለጊዜው ስማቸው የማይገለጽ አባት በጠዋት ከቤታቸው በደህንነቶች ከተወሰዱ በዋላ ባልታወቀ ስፍራ ቀኑን ሙሉ እንዲቆዩ ተደርገው የተለያዩ ጥያቄዎች ሲቀርብላቸው ከዋለ በዋላ ዛቻና ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው ማምሻ ላይ ወደ መኖሪያቸው መመለሳቸውን የመረጃ ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡
የቤተክርስቲያን ይዞታ ተነጥቆ በድብቅም ካርታና ፕላን ወጥቶበት እየተገነባ ያለውን የእምነትን ቅድስናና የሃይማኖትን ክብር የሚያዋርድ ካፍቴሪያና የመዝናኛ ፕሮጀክትን ህዝቡና ቤተክርስቲያን በማውገዝና በመቃወም ጥንታዊውን መንፈሳዊ ይዞታ ለማስከበር በተዋቀረው ኮሚቴ ውስጥ አባል ሆነው የተጣለባቸውን ሰማያዊ አደራ በጽናት ሲወጡ የቆዩ አባቶችን በስልክ የተለያዩ ዛቻዎችና ማስጠንቀቂያዎች ሲደርሳቸው ቆይቶ አሁን የተወሰደው ርምጃ አባቶችን በማስፈራራትና በማስጨነቅ ህብረተሰቡ ግንባታውን እንዲቀበል እንዲያደርጉ ታሳቢ የሆነ መሆኑን ምንጮች ይጠቁማሉ፡፡
"ከስፍራው ጋር የተያይዞ ለሚፈጠረው የትኛውም ችግር ተጠያቂ ናችሁ፡፡ ልማቱን እየተቃወማችሁ ነው፡፡" የሚል የክስና የማስፈራሪያ ዛቻ አባቶች ላይ እያቀረቡ ያሉት አካላት አባቶችን በማስጨነቅና በማስፈራራት እንዲሁም በመከፋፈል የቀረበውን ፍትሃዊ ጥያቄ ለማስቆም ከፍተኛ ጫና እያደረጉ መሆኑን ምንጮች ይጠቁማሉ፡፡ እየደረሰባቸው ያለውን ከፍተኛ ጫናና የማስጨነቅ ተግባር የደብር አለቆች ስለ ቤተክርስቲያን ሲሉ ለመናገር ፈቃደኛ ባይሆኑም ከተገለጸውም በላይ የተለያዩ መከራዎችን በጸጋ እየተቀበሉ እንዳለ ሁኔታውን በቅርበት የሚከታተሉ አካላት ይገልጻሉ፡፡
አንዳንድ ምንጮች እንደሚጠቁሙት ከሆነ አባቶችን በማስፈራራትና በማለያየት የጥምቀት በአል በየ አጥቢያው እንዲከበር ለማድረግ አደገኛ ተግባር እየተፈጸመ እንደሚገኝ ይገልጻሉ፡፡ ከመቼውም ጊዜ በላይ ህዝቡ በጸሎት እንዲተጋና ከአባቶች ጎን እንዲቆምም ያሳስባሉ፡፡
ቤተክርስቲያን ይዞታዋን ለማስከበር በግልጽና ህጋዊ በሆነ መንገድ ጥያቄዋን እያቀረበች በምትገኝበት ወቅት ከኮሚቴ አባላት መካከል የይሁዳን ስራ የሚሰራን ሰው በማዘጋጀትና የስብሰባዎቹን ሂደት በሞባይል መቅረጸ ድምጽ ቀርጾ የሚያቀብልን ሰው መላክ ለምን አስፈለገ? ብለው የሚጠይቁት ታዛቢዎች የትኛውም አካል ቤተክርስቲያን በምታደርጋቸው ስብሰባዎች ላይ መሳተፍ እየቻለ ቤተክርስቲያን እንደ ወንጀለኛ ተቆጥራ በውስጧ ሆነው የእጇን በረከት እየበሉ ነገር ግን ሰማያዊውን ህይወት ዘንግተው ወሬ የማቀበል ርካሽ ተግባር ላይ የተሰማሩ ምናምንቴ ሰዎችን መጠቀም ለምን አስፈለገ ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡ በዘመነ ስጋዌም በአምላካችን ለታላቅ ክብርና ስልጣን ከተመረጡት መካከል በሃዋርያት ጉባኤ መካከል የነበረው ይሁዳ አምላኩ ከሰጠው ታላቅ ክብርና ስጦታ ይልቅ ሰላሳ ብር በልጦበት አምላኩን ለመሸጥና የሃዋርያትን ጉባኤ ለመበትን በጀርባ ከአይሁድ ጋር ይደራደር እንደነበር እንዲሁ ዛሬም በቤተክርስቲያን ጉያ ተሸሽገው ቤተክርስቲያንን ለመሸጥ የሚያደቡ የሲኦል እጩዎች በመካከላችን መኖራቸውን የተስተዋለበት አጋጣሚ መኖሩን ታዛቢዎች ይገልጻሉ፡፡
*
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የቤተክርስቲያንን ጥያቄ ለበላይ የመንግስት አካላት በማቅረብና ይዞታውን ለማስከበር ከሁሉም ደብራት ከተዋቀሩት የኮሚቴ አባላት መካከል በቀዳሚነት ሃላፊነታቸውን እየተወጡ ካሉት መሃል አራት የኮሚቴው አባላት በቅርቡ እንዲታሰሩ መወሰኑን የሚጠቁሙ መረጃዎች ከታማኝ ምንጮች ተሰምቷል፡፡ ህግና ስርአት ባለበት ሀገር በጠራራ ፀሃይ በዘመናት ተከብሮ በቆየው ሃይማኖታዊ ይዞታ ላይ በመግባት በህገ መንግስቱ የተረጋገጠውን ህዝብ በሀገሩ በነጻነት ሃይማኖቱን የማራመድ መብቱን በመጣስ ህገወጥ ተግባር የፈጸሙ የክፍለ ከተማው ባለ ስልጣናት በህግ ሳይጠየቁ በነጻነት እየኖሩ "ጥንታዊው መንፈሳዊ የቤተክርስቲያን ይዞታ ባልተገባ መንገድ ተወስዷል፤ በስፍራውም እየተከናወነ ያለው ፕሮጀክት የሃይማኖትን ክብርና የእምነትን ቅድስና የሚያዋርድ ያልተገባ ስራ ነው፡፡" ብለው በግልፅ በስነ ሥርአት ጥያቄ ያቀረቡ ንጹሃንን ለማሰር መነሳት የበለጠ በህዝቡና በአስተዳደሩ መካከል መተማመንን የሚያጠፋና ህብረተሰቡንም የሚያስከፋ ጉዳዩን በሰከነ አግባብ በማየት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ውሳኔ ላለመወሰን የተያዘውን አቋም የሚያሳይ ነው፡፡
የሰላምና የፍቅር ቤት የሆነችው ቤተክርስቲያን አቤቱታዋንና ጥያቄዋን በሥርአትና በአግባብ ሃላፊነት በተሞላበትም መንገድ እያቀረበች ቢሆንም በክፍለ ከተማው እየተፈጸመ ያለው ተግባርም ሃላፊነት የጎደለው ለችግሩም ዘላቂ መፍትሄ የማያስገኝ በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት በህግና በአግባብ ለቤተክርስቲያኒቱ ጥያቄ ፍትሀዊ ምላሽን እንዲሰጡ ዛሬም ቤተክርስቲያን ተማጽኖዋን ታቀርባለች፡፡
*
ተጨማሪ ሰበር ዜና ስለደረሰን ከቆይታ በዋላ ይዘን እንመለሳለን፡፡
*
ቸር ወሬ ያሰማን!
*
"ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተክርስቲያን!"
Saturday, 19 December 2015
መከላከያ እየተፈረካከሰ ነው
==================
በዚ ሁለት ቀን ብቻ በርካታ ወታደሮች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው በዛላምበሳ ግንባር ወደኤርትራ ገቡ
ከነዚ በርካታ ወታደሮች መኮንኖችም እንደሚገኙበት
ለማወቅ ተችሏል። በሁለት ቀን ብቻ እጅግ በርካታ ወታደሮች ስርኣቱን በመቃወም ወደኤርትራ ሲገቡ ከመቸውም በላይ ስርኣቱ ምን ያህል ውድቀቱ እንደተቃረበ እንደሚያሳይ ለመገመት ይቻላል።
Hermon Cohen
Tuesday, 8 December 2015
ኢህአዴግ በአሸባሪነት የሚፈርጃቸው የአርበኞች ግንቦት7
ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ በአሸባሪነት የሚፈርጃቸው የአርበኞች ግንቦት7 ሊቀመንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ወደ አገር ቤት ተመልሰው ግንቦት ወር ተካሂዶ በነበረው ምርጫ እንዲሳተፉ፣ በእርሳቸው በኩል መልክት እንዲያስተላልፉ ተነግሮአቸው እንደነበር የአውሮፓ ህብረት የፓርላማ አባል እና የኢትዮጵያ የምርጫ 97 የህብረቱ የምርጫ ታዛቢ ልኡካን መሪ ሚስ አና ጎሜዝ ተናግረዋል። ሚስ አና ጎሜዝ ይህን የተናገሩት ባለፈው ሳምንት ተዘጋጅቶ በነበረው ስብሰባ ላይ ነው። መንግስት በአንድ በኩል ፕ/ር ብርሃኑን ሽብረተኛ ይላቸዋል፤ በሌላ በኩል ደግሞ ወደ አገር ተመልሶ በምርጫው እንዲሳተፍ መልእክት እንዳስተላልፍላቸው ጠይቀውኝ ነበር፣ ያሉት አና ጎሜዝ፣ መልእከቱን ማድረሳቸውንና ፕሮፌሰሩ መሰረታዊ የሚባሉት ጥያቄዎች ከተሟሉ በምርጫው ለመሳተፍ ዝግጁ መሆናቸውን መልስ እንደሰጧቸው ተናግረዋል። ይሁን እንጅ አሉ ባለስልጣኑዋ፣ መመለስ አለባቸው የተባሉት መሰረታዊ ጥያቄዎች ባለመመለሳቸው ኢህዴግ ምርጫውን 100 በመቶ አሸንፍኩ በማለት አስደምሞናል ብለዋል። ሚስ አና የሽምግልና ጥያቄው የቀረበላቸው እርሳቸው የአፍሪካና ካረቢያን አገራት የፓርላማ አባላት ስብሰባ ለመካፈል ወደ አዲስ አበባ ባቀኑበት ወቅት ነው። ኢሳት በወቅቱ ዘገባውን ያቀረበ ቢሆንም፣ ጥያቄው በአንድ የአውሮፓ ዲፕሎማት መቅረቡን ከመግለጽ ውጭ የዲፕሎማቷን ስም አልጠቀሰም ነበር።
http://ethsat.com/…
