Friday, 4 April 2014

 No worries about Eritrean oppositions if Eritrea forms, says  Ethiopian government  


April 2, 2014
Getachew Reda, who was the Director General of the Public Diplomacy and Communications Directorate of the Ministry of Foreign Affairs before his current appointment as the Press and Publicity State Minister at the Office of the Prime Minister, said the Ethiopian government does not have any problem if the Ethiopian government changes its positions and comes to peaceful deal with us as the Eritrean opposition are under our armpits and we have no worries.
He said if the Eritrean regime wants to form with us, we will have no chip on our shoulder against them. Getachew said armed Eritrean opposition forces are not taking actions because the Eritrean Defence Force is heavily entrenched around the borders.
Getachew said the reports that Ethiopia teaches 20,000 Eritrean refugees is an exaggeration, the number is not more than 1800. These students could not be a security risk as they have started their studies after proper vetting, he added.
The Minister said the hopeless Ethiopian youth is more risky to security than the Eritrean refugees and tracking these youth will clear the security risk, he said.
Although the Ethiopian people have not prospered, we have created a zeal for prosperity which has succeeded in diverting its attention, Getachew said.
Asked about the Djibouti port, Getachew said “as the families of the Djibouti’s leaders share the rent money we pay for the port, we have no fear that Djibouti will deny us access to the port.”

Tuesday, 1 April 2014

20 march 2014
                                                  
ከአዲስ አበባ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ!
ኢህአዴግ አገር የመምራት ብቃት እንደሌለው አዲስ አበባ ማሳያ ናት!!
ሌሎች አገሮች ለዋና ከተሞቻቸው ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የየአገሮቻቸው ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ማሳያ በማድረግ አለም አቀፍ ተቋማትንና ጎብኝዎችን በመጋበዝ የከተሞቻቸውን ነዋሪዎች ተጠቃሚ ያደርጋሉ፡፡
እንዳለመታደል ሆኖ ግን በብዙዎች የአፍሪካ አገራት የአህጉሪቱ መዲና ተደርጋ የምትጠቀሰው አዲስ አበበባችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደ ኋላ አየተጎተተች ለኑሮ ምቹ ከሆኑ ከተሞች ምድብ መቀላቀለ ተስኗት ለነዋሪዎቿ የማትመች የፈተና ምድር ሆናለች፡፡
ኢህአዴግ ራሱን ልማታዊ መንግሥት በማድረግ ከሰየመበት ቅጽበት አንስቶ በልማት ሰበብ ዜጎች ከመኖሪያቸውና ቤተሰቦቻቸውን ከሚያስተዳድሩበት የንግድ ቦታ እንዲፈናቀሉ ተደርገዋል፡፡ በከተማይቱ እንዲነሱ የተደረጉት የንግድ ሱቆች በአብዛኛው በኪራይ ቤቶችና በቀበሌ ስም የተመዘገቡ በመሆናቸውም በሱቆቹ በመነገድ ይተዳደሩ የነበሩ ቤተሰቦች ባዶ አጃቸውን እንዲቀሩ ተደርገዋል፡፡
በአዲስ አበባ እየተካሄደ ያለውን የመንገድ ዝርጋታ የተነሳ የተጠና ሥራ ባለመሰራቱ ከፍተኛ የህዝብ ገንዘብ የወጣባቸው መንገዶች ለምረቃ በበቁ በጥቂት ቀናት ልዩነት እንዲፈርሱ ተደርገዋል፡፡ የከተማው ነዋሪ ለሚጠቀምባቸው የመጓጓዣ አውታሮች ተለዋጭ መንገድ ባመዘጋጀቱም ለተጨማሪ ወጪ ተዳርጓል፡፡ ትራንስፖርት ማግኘት በሁሉም አካባቢዎች አስቸጋሪ በመሆኑ የከተማይቱ የሥራ እንቃስቃሴ ተዳክሟል፡፡ መንግሥት ‹‹የምትታለብ ላም›› በማለት የሚጠራው የኢትዮ ቴሌ ኮም አገልግሎት የለም የሚባልበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ጭምር በኢትዮጵ ቴሌኮም የተንቀራፈፈ አገልግሎተ የተነሳ ባንኮችና የተለያዩ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ለደምበኞቻቸው ተገቢውን ግልጋሎተ ማበርከት አልቻሉም፡፡
የከተማይቱ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ችግር የተወሰኑ ሠራተኞች ችግር እንደሆነ ተጠቁሞ ሠራተኞች ለስንብት ቢዳረጉም የኤሌክትሪክ መቆራረጥና ለረጅም ግዜ መጥፋት የከተማይቱ ኢንዱስትሪዎች ፤ንግድ ተቋማትንና ነዋሪውን እያማረረና ህይወቱን እያመሰቃቀለ ከመሄድ ውጭ ምንም አይነት ለውጥ አልታየበትም፡፡ በከተማይቱ ውሃ ማግኘት እንደ ትልቅ እድል መቆጠር ጀምሯል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ የከተማይቱ 75% ነዋሪ ውሃ እንደሚያገኝ ቢናገሩም መሬት ላይ ያለው እውነታ ግን በተቃራኒው ሆኗል፡፡ ጊዜያቸውን በትምሀርት ገበታቸው ላይ በመገኘት ማሳለፍ ይገባቸው የነበሩ ተማሪዎች ውሃ ለመቅዳት ረዥም መንገድ ለመጓዝ በመገደዳቸው የትምህርት ጊዜአቸው እየተበደለ ይገኛል፡፡
በአጠቃላይ ከተማይቱን በማስተዳደር ላይ የሚገኘው ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ የከተማይቱ ነዋሪ ለሚገፋው አስቸጋሪ ህይወት ተጠያቂ ነው፡፡ ድርጅቱ አገሪቱን የመምራት ብቃት እንደሌለውም የወቅቱ የአዲስ አበባ ሁኔታ አይነተኛ ማሳያ ነው፡፡
የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ የአዲስ አበባ ምክር ቤት የከተማይቱ ነዋሪ እየገፋው የሚገኘውን ፈታኝ ህይወት በማጥናት ህዝቡን በተለይም የከተማውን እና የዙሪያ አካባቢዋን ነዋሪ በማደራጀት በቅርቡ ‹‹የእሪታ ቀን›› በማለት ሰይሞ በ1ወር ጊዜ ውስጥ ሠላማዊ ሠልፍ ለማድረግ የወሰንን መሆኑን እየገለፅን የአዲስ አበባና አካባቢዋ ነዋሪዎች ሰላማዊ ሰልፉ በሚደረግበት ቀን በነቂስ በመውጣት በስርዓቱ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ለመግለፅ እንዲዘጋጁ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

ኢህአዲግ/ወያኔ ሕዝብ ለማፋጀት የገነባውን ‘የመርዝ ብልቃጥ’ በያዝነው ሳምንት በሃያ ሚልዮን ብር ወጪ ይመርቃል


ምርቃቱ የሩዋንዳው የዘር ማጥፋት ግጭት ከተጀመረበት 20ኛ ዓመት ጋር ገጥሟል።ባጋጣሚ ወይስ ታስቦበት?


መጋቢት 22/2006 ዓም
ኢትዮጵያን እየመራ የሚገኘው ኢህአዲግ/ወያኔ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከቀን ወደ ቀን እርስ በርሱ እንዳይተማመን፣እንዲነቃቀፍ፣እንዲጠራጠር ከእዚህ ባለፈ ደግሞ ግጭት እንዲፈጠር እያደረገ 22 ዓመታትን ዘለቀ።ህዝቡ እለት ከእለት በገዢው መንግስት የሚወጠኑለትን የእርስ በርስ ማጋጫ ተንኮሎች እየተመለከተ ልቦናው በእጅጉ እየደማ ነው።
አንድ ወራሪ የውጭ ጠላት ሊሰራ የሚችለውን ያህል ህዝብን ከሕዝብ ጋር የማጋጨት ሥራ ኢህአዲግ/ወያኔ በትክክል ሰርቶበታል። የሃገሪቱን ፌድራል አስተዳደር በየትኛውም ዓለም ያልታየ ቋንቋን መሰረት ያደረገ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ደገሰላት።ፌድራላዊ አስተዳደር በዘመናዊው ዓለም አንዱ እና አማራጭ የአስተዳደር ዘይቤ ይሁን እንጂ በየትኛውም ሀገር መሰረት የሚያደርገው የመልክዓ ምድርን አቀማመጥ እና ታሪካዊ አሰፋፈርን ነው። እርግጥ ነው ጣልያን ሀገራችንን በወረረ ዘመን አሁን ወያኔ የሚጠቀምበትን የክልል አስተዳደር የመሰለ ቋንቋን መሰረት ያደረገ የአስተዳደር መዋቅር ዘርግቶ ነበር።
አንዳንዶች የአሁኑ ቋንቋን መሰረት ያደረገ አስተዳደር የብሔር ብሄረሰቦችን መብት ከማስከበር አንፃር የሚመስላቸው የዋሃን አይጠፉም።ግን ፈፅሞ አላማው ይህ ላለመሆኑ ብዙ ማስረጃ መጥቀስ ይቻላል።እርግጥ ነው የህዝብ ባህል ማለትም ቋንቋው፣አለባበሱ፣ታሪኩ ወዘተ ሊጠበቅለት እና ከለላ ማግኘት አለበት።ይህ ከለላ በማግኘት መብት  ስም ወንጀል ሲሰራ፣ቁርሾ በባትሪ እየተፈለገ ሲራገብ እና ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት ሲውል ነው ወንጀሉ።
ኢህአዲግ/ወያኔ ሕዝብ እርስ በርሱ በጎሳ ሲጋጭ መፍትሄ ለመፈለግ ከመነሳት ይልቅ ጉዳዩን ሲያባብስ እና ቤንዚን ስያርከፈክፍ ማየት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ዕለት ከዕለት የሚመለከተው ድራማ ሆኗል። ለእዚህም ብዙ አብነቶችን መጥቀስ ይቻላል። ለእዚህ ፅሁፍ ግን ሁለት ምሳሌዎችን እንጥቀስ -
1/  በዩንቨርስቲዎች ውስጥ ወጣቶች ‘አንተ የእገሌ ነህ አንተ የእንቶኔ ነህ’ ተባብለው ፀብ ሲነሳ ጉዳዩ የመጪው ትውልድ እና የአሁኑ ትውልድ አደገኛ አቅጣጫ ነው ብሎ የችግሩን ስር ለመፍታት ከመጣር እና የጉዳዩን አስከፊነት  በመገናኛ ብዙሃን ከመግለፅ እና ከማስተማር ይልቅ ፖሊስ ይልቁን ከአንድኛው ወገን ቆሞ ሌላውን ሲያስር እና ሲቀጣ መመልከት ዘግናኝ ተግባር ነው።
2/ ሕዝብ ለዘመናት ከኖረበት የእርሻ ቦታ ”የእገሌ ዘር ነህ” ተብሎ በክልል መስተዳድሮች ጭምር ሲባረር ለጉዳዩ እንደ መንግስትነት ለመዳኘት ሳይሆን የሚሞከረው እንደ ቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ አባባል ”ቀድመው ባልተወለዱበት ሀገር መስፈር የለባቸውም” እንደ አቶ አለምነህ የብአዴን ቢሮ ምክትል ኃላፊ ደግሞ ”የትዕቢት ልጋግ” ነው የሚሉ መልሶችን መስማት እራስ ያማል።መሪዎቻችን እንዲህ እያሉ ከጉርዳፈርዳ እስከ አሶሳ፣ከአሶሳ እስከ ሐረር፣ ከሐረር እስከ ጅጅጋ፣ ከጅጅጋ እስከ ቦረና ጉጂ፣ ድረስ በብዙ አስር ሺህ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን በኢህአዲግ/ወያኔ የጎሳ ፖለቲካ ተሰደዱ፣ተገደሉ።ይህ ሁሉ ሲሆን ግን መንግስት ጉዳዩን እንደ ትልቅ ችግር ሳይሆን እንደ አንድ የማስተዳደርያ ዘዴ እንደቆጠረው በ እርግጠኝነት መረዳት ይቻላል።

በያዝነው ሳምንት  በሃያ ሚልዮን ብር ወጪ የሚመረቀው የመርዝ ብልቃጥ 


በአርሲ ዞን በሂቶሳ ወረዳ ከሃያ ሚልዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያሰራውን  ”አኖሌ ሐውልት” እና ሙዝዬም
የእርስ በርስ ግጭቶች ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲሻገሩ የሚጥረው ኢህአዲግ/ ወያኔ ለእርስ በርስ ጦርነቶች እየመረጠ ሃውልት ሲሰራ ከርሞ በእዚህ ሳምንት ደግሞ ለየት ያለ የጥፋት ድግስ የሚሆን ከመቶ አመታት በፊት ለመፈፀሙ ምንም አይነት የታሪክ ማስረጃ የሌለው በዳግማዊ ምኒልክ ዘመን በአርሲ ዞን በሂቶሳ ወረዳ ተፈፅሟል ያለውን የታሪክ ምሁራን ያላረጋገጡትን የፈጠራ ታሪክ ከሃያ ሚልዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያሰራውን  ”አኖሌ ሐውልት” እና ሙዝዬም  በእዚህ በያዝነው ሳምንት እንደሚመረቅ ኢቲቪ ዛሬ መጋቢት 22/2006 ዓም የዜና እወጃው ላይ አስታወቀ።የፈጠራው ታሪክ ከመቶ ዓመታት በፊት የአፄ ምኒልክ ሰራዊት የኦሮሞ ሴቶችን ጡት ቆርጦ ነበር እና ማስታወሻነቱ ለተቆረጡት ጡት እና እጅ ይሁን” ይላል የሃውልቱ የመሰራት ምክንያትን ኦህዴድ /ኢህአዲግ/ወያኔ ሲናገር። አሳዛኝ የደረስንበት የዝቅጠት ዘመን።በየትኛውም ሀገር ውስጥ በቀደሙ መሪዎች ያውም ከመቶ አመታት በላይ ለሆነው ታሪክ ቀርቶ የቅርቦቹም ቢሆን ለተሰሩ ተገቢ ያልሆኑ ድርጊቶች ለመጪው ትውልድ የሚያቆይ የእልቂት ድግስ ከፋች ሃውልት አይሰራም። የሚጠጣ ውሃ፣ የምበላው ምግብ ለሌለው ሕዝብከ 20 ሚልዮን ብር በላይ አውጥቶ መበተን ምን የሚሉት ፈልጥ ነው?
አንድ መንግስት ሕዝብ ከህዝብ ጋር አብሮ የሚኖርበትን ዘዴ ሲቀይስ ልዩነትን እያጎላ ሳይሆን አንድነትን እያሳየ እና እያጎላ ሕዝብ በፍቅር እና በስምምነት እንዲኖር ይጥራል እንጂ እንዴት ከአሁኑ ትውልድ አልፎ ለመጪው ትውልድ ቂም ለማውረስ ተግቶ ይሰራል? ይህ ተግባር ማንን ይጠቅማል? ለመሆኑ ያለፉ ነገስታት በወቅቱ በነበረው የቅጣት መንገዳቸው ሁሉ የቀጡትን የቅጣት አይነት እየዘረዘርን ሃውልት ብንሰራ የቱን ከየቱ እንመርጣለን?
የሃውልቱ ምርቃት እንደ ትልቅ የሀገር ልማት ዛሬ ኢቲቪ ቀድሞ ዛሬ ይናገረው እንጂ ወቅቱ የሩዋንዳው እልቂት የተጀመረበት 20ኛ አመት ጋር ገጥሟል።በሚያዝያ 7/1994 ዓም  እስከ ሐምሌ/1994 ዓም እ ኤ አቆጣጠር የቆየው በቱትሲዎች እና በሁቶዎች መካከል የተደረገው እልቂት ከአምስት መቶ ሺህ በላይ ሕዝብ ሕይወት ቀጥፏል።የሩዋንዳው እልቂት በአንድ ሌሊት ድንገት የደረሰ ጉዳይ አይደለም።በሂደት አልፎ አልፎ በተነሱ ቁርሾዎች ጥርቅም ሳብያ መሆኑን መዘንጋት አይገባም።የዛሬ የባለ ሃያ ሚልዮን ሃውልት ገንቢዎችም ሆኑ አስገንቢዎች መዘንጋት የሌለባቸው  በሰሩት ሥራ ሁሉ የሚጠየቁበት ቀን እንደሚመጣ መጠራጠር አይገባም።የመርዝ ብልቃጡም ይሰበራል የፍርድ ቀኑም ይቆረጣል።                  source: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/14055