Wednesday, 6 January 2016

የአርበኞች ግንቦት 7 የትግል ጥሪ በራሪ ወረቀቶች በአርሲ ....

ኢሳት (ታህሳስ 27 ፥ 2008) የአርበኞች ግንቦት 7 የትግል ጥሪ በራሪ ወረቀቶች በአርሲ አሰላ ከተማ በርካታ ቀበሌዎች ትናንት ማክሰኞች በተሳካ ሁኔታ ለህዝብ መድረሳቸው ተገለጸ። በአካባቢው የሚኖሩ የአርበኞች ግንቦት ሰባት አስተባባሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት በከተማው ውስጥ በብዙ ስፍራዎች ከ1600 በላይ የሚሆኑ የትግል ጥሪ ወረቀቶች በከተማዋ ለሚኖረው ህዝብ እንዲደርስ ተደርጓል። ሕዝብ በሚያዘወትርባቸው በተለያዩ ግልጽ ቦታዎች የትግል የጥሪ ወረቀቶች ተለጥፈው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። የተበተነውን የትግል ጥሪ ወረቀት የመንግስት የጸጥታ ሃይላት ለመሰብሰብ ሙከራ ቢያደርጉም፣ አብዛኞቹ የጥሪ ወረቀቶች በነዋሪው እጅ በመግባታቸው የጸጥታ ሃይል ሰራተኞች ያሰቡት ያክል ወረቀት ለመሰብሰብ እንዳልቻሉ ታውቋል። አብዛኞቹ ወረቀቶች ሰው ሊያያቸው በሚችልባቸው የተለያዩ ቦታዎች የተቀመጡ ሲሆኑ፣ ፖሊሶች ወረቀቶችን ለመሰብሰብ ሲጥር እንደነበር እማኞች ለኢሳት ገልጸዋል። የመንግስት ጸጥታ ሃይሎች ለመሰብሰብ የቻሉት የትግል የጥሪ ወረቀት ከ50 እንደማይበልጥም ጉዳዩን በትኩረት ሲከታተሉ የነበሩ አስተባባሪዎች ከአሰላ ለኢሳት ተናግረዋል። ህብረትሰቡ የትግል ጥሪ ወረቀቱን በጉጉት እያነበበ እንደነበርም ለማወቅ ተችሏል። ከዚህ በፊት በአሰላ አካባቢ የትግል ጥሪ ወረቀት ተበትኖ ስለማያውቅ፣ ህዝቡ የትግል ጥሪ ሲደርሰው የግንቦት 7 አባላት በአካባቢው ይኖራሉ፣ ሊያደራጁንም ይችላሉ በሚል መንፈስ ደስተኛ መሆኑን የአካባቢውን ሰዎችን ያነጋገሩ አስተባባሪዎች ተናግረዋል። የህወሃት ኢህአዴግ የጸጥታ ሃይላትም፣ የደህንነትና የጸጥታ አካላት በምስጢር ይህን ያክል ወረቀት ሲበተን አለመድረሳችን  መዋረዳችንን ያመለክታል በማለት በቁጭት ሲናገሩ እንደነበር እማኞች ለኢሳት ገልጸዋል። የተበተነው ወረቀት ላይ የሰፈረው “የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ኦሮሞ፣ አማራ፣ ጉራጌ፣ ትግሬ ብለን ሳንከፋፈል በአንድነት እንነሳ፣ የታሰሩት ይፈቱ” የሚል መልዕክት እንደነበረው አስተባባሪዎቹ አስታውቀዋል። መልዕክቱም በአማርኛና በኦሮምኛ የተጻፈ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። በበራሪ ወረቀቱ ላይ የግንቦት ሰባት አርማ ያረፈበት እንደነበርም ታውቋል። የአርበኞች ግንቦት 7 ትን ለማስተዋወቅና በአገሪቱ በሁሉም ክፍሎች እንቅስቃሴ እንደሚያደርግ፣ በየአካባቢው የትግል ጥሪ ወረቀት መበተናቸውንና አባላት ማደራጀታቸውን እንደሚቀጥሉበት አስተባባሪዎቹ ለኢሳት ገልጸዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የትግል ጥሪ ያያዙ ወረቀቶች በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች እየተበተኑ ነው። የአርበኞች ግንቦት ሰባት አባላት በባህርዳት፣ አርባምንጭ፣ አዲስ አበባና፣ ወላይታ ሶዶ ከተሞች ባለፉት ጥቂት ወራት ተመሳሳይ መልዕክት ያላቸውን በራሪ ወረቀቶች ለህዝቡ ማድረሳቸው መዘገባችን የታወሳል።

http://ethsat.com/amharic/%e1%89%a0%e1%8a%a0%e1%88%b0%e1%88%8b-%e1%8a%a8%e1%89%b0%e1%88%9b-%e1%8b%a8%e1%8c%8d%e1%8a%95%e1%89%a6%e1%89%b5-%e1%88%b0%e1%89%a3%e1%89%b5-%e1%8b%a8%e1%89%b5%e1%8c%8d%e1%88%8d-%e1%8c%a5%e1%88%aa/

Tuesday, 5 January 2016

ዶክተር መረራ ጉዲና የኦፌኮ አመራሮች..

*ዶክተር መረራ ጉዲና የኦፌኮ አመራሮች ቢታሰሩም፣ በሕዝብ ላይ የሚደርሰው ድብደባ እና ግድያ ቢቀጥልም ሕዝባዊ ትግሉ ይቀጥላል ይላሉ። ለሁላችንም የምትሆን ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመመስረት ሁሉም በተባበረ ክንድ በቁርጠኝነት እንዲታገል ጠይቀዋል።
*የተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ በኦሮሚያ ለሚካሄደው የመብት ትግል ድጋፉን እንዲያደርግ ጥሪ ሲያቅርቡ ገዢው ሥርዓት ኢህአዴግ ግትርነቱ ለፓርቲው እና ለሀገሪቱ ስለማይጠቅም ሕዝቡን እንዲሰማ አሳስበዋል

*ባለፈው ሐሙስ ምሽት በዲላ ዩኒቨርስቲ ከተገደሉት ተማሪዎች አንዱ ጫንያለው አላየ ነው። የ19 ዓመቱ ጫንያለው የትውልድ ቦታው ደብረብርሀን ነው።
አባቱ "ልጄ የሁለተኛ ዓመት ኢንጂነሪንግ ተማሪ ነበር። ሕልሙ ተጨናገፈ" ብለዋል ለኢሳት

ተጨማሪ መረጃዎች አሉ::

የርስዎን ድምጽ ኢሳትን ያድምጡ!

http://ethsat.com/esat-radio-mon-04-jan-2016

Monday, 4 January 2016

ድርቁ እየተባባሰ....

ድርቁ እየተባባሰ በመጣባቸው አካባቢዎች የትምህርት ሰራው እየተጎዳ መምጣቱ ተነገረ፡፡
በሰሜን ጎንደር ዞን በሚገኙ ሰባት ወረዳዎች በተከሰተው ድርቅ ፣ የሚያስተምሩ መምህራን በየጊዜው ስራቸውን በመልቀቃቸው የትምህርቱ ስራ አደጋ ላይ መሆኑን የዞኑ ትምህርት ከፍተኛ ባለስልጣናት በጎንደር ከተማ በሰጡት መግለጫ ተናገሩ፡፡ በዞኑ ባሉት 280 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ከ120 ሽህ በላይ ህጻናት ተማሪዎች ትምህርታቸውን ለማቆም በቋፍ ላይ መሆናቸወን የተናገሩት የዞኑ አመራሮች በተለይ በወገራ፣ምስራቅ በለሳና ጃናሞራ ወረዳዎች በሁለት ሳምንት ብቻ 265 መምህራን መልቀቃቸውን ሲናገሩ ተሰምተዋል፡፡ በጃናሞራ ወረዳ አሁን አሁን የመበተን አዝማሚያ እየታየ መሆኑን የዞኑ የትምህርት ከፍተኛ ኃላፊዎች ገልጸው፤ሰፊ የደርቅ አደጋ በታየባቸው 120 ቀበሌዎች የትምህርቱ ሂደት አደጋ ላይ መውደቁን ተናግረዋል፡፡ በዞኑ ያለውን የትምህርት ሂደት ለማስቀጠል የመምህራን መልቀቅ መሰረታዊ ችግር መሆኑን የሚናገሩት አመራሮች አሁንም የተሰጠ አስቸኳይ መፍትሄ ባለመኖሩ ችግሩ እየተባባሰ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡ ድርቁ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ከድህነቱ ጋር ተያይዞ ከባድ የጽህፈት መሳሪያ እጥረት ችግር መኖሩ አንዱ የመማር ማስተማሩን ሂደት አደጋ ላይ የሚጥል ችግር መሆኑን አክለው የሚናገሩት የትምህርት አመራሮች፣ አንድ ደብተር ለአራትና አምስት ተማሪዎች የሚጠቀሙበትን ሁኔታ በአካል በመገኘት መመልከታቸውን ተናግረዋል፡፡ ድርቁ በተከሰተባቸው ሰባቱም ወረዳዎች ለህጻናቱ አስቸኳይ አልሚ ምግብ ካልቀረበላቸው የሞት አደጋ ሊከሰት እንደሚችል ስጋቱ እንዳደረባቸው የሚገልጹት ኃላፊ ከረሃቡ ጋር በተጨማሪ የውሃ እጥረቱም ለተማሪዎች ፈታኝ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በአንድም ይሁን በሌላ ችግር የመቅረትን ሁኔታ እያባባሰው ያለው የተከሰተው የውሃ ችግር መሆኑን የሚገልጹት ኃላፊ አንድ ጀሪካን ውሃ ለማምጣት ህጻናቱ የስድስት ሰዓት መንገድ የሚጓዙ በመሆኑ የቀሪ ተማሪዎች ብዛት ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ መምጣቱ በትምህርቱ ላይ ያንዣበበ ትልቅ አደጋ መሆኑን ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡

Saturday, 2 January 2016

መርጦ_ለማርያም

#መርጦ_ለማርያም
ህወሀት አሁንም አፈናውን ኣባብሶ ቀጥሎበታል!!!
በጎጃም መርጦለማርያም ከተማ ነዋሪ የነበረውን መምህር አሰጋ አሰፋ በ12/04/2008 ዓ.ም በህወሃት ደህንነቶች ታፍኖ ተወስዳል፡፡ መምህር አሰጋ ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ የቅንጅት ጠንካራ አባል የነበረና አሁንም የመኢአድ የወረዳው አስተባባሪ ሲሆን ፍጹም የሀገር ፍቅር ያለው በአካባቢው ማህበረሰብም የተከበረና ለገዥው ዘረኛ መንግስት ያልተንበረከከ የቁርጥ ቀን ልጅ ነበር፡፡ የመምህር አሰጋ ቤት ለ3 ሰዓታት የፈጀ ፍተሻ የተደረገበት ሲሆን በዚሁ ወቅት አፋኞች ሲጠይቁት እኔ ህጋዊ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል ነኝ ኢህአዴግን በህይወት እያለሁ አይደለም ሞቸ እንኳ አጽሜ እናንተን የፋለማል በማለት ነበር በድፍረት የተናገረው፡፡
ታፍኖ ከተወሰደበት ቀን ጀምሮ የት እና በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ እስከ ዛሬ 23/04/2008ዓ.ም ድረስ ቤተሰቡም ሆኑ ጓደኞቹ እንደማያቁና በጭንቀት ውስጥ ናቸው፡፡ ሕዝብን በማስተባበርና በማደራጀት ተጽዕኖ ይፈጥራሉ የሚላቸውን የህዝብ ሊጆች ሁሉ በማሳደድ ላይ ይገኛል፡፡በዚህ ወረዳና በአካባቢው ታፍነው የሚወሰዱ ዜጎች ቁጥር እጅግ እየጨመረና ህብረተሰቡም በዚህ ጉዳይ ላይ ተቃውሞ እንዳያቀርብ በተለያዩ የመንግስት ተላላኪዎችና ሆዳሞች እየተሰለለ መሆኑን በማወቁ በልቡ የአመጽ እሳት እየነደደበት ቀን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡
ድል ለተገፉና ትፍትህን ለተራቡ፣ ሞት ለአፋኙ ስርዓት አራማጆች፣ ነጻነት ለኢትዮጵያ!!

Friday, 1 January 2016

በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር በየአመቱ ከፍተኛ ገንዘብ የምታወጣው ኢትዮጵያ ... 26 ቢሊዮን

ኢሳት (ታህሳስ 23 ፣ 2008) በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር በየአመቱ ከፍተኛ ገንዘብ የምታወጣው ኢትዮጵያ ከህገ-ወጥ ንግድ ተቋማት ጋር በተያያዘ በየአመቱ ሁለት ቢሊዮን ዶላር እያጣች እንደሆነ አንድ አለም አቀፍ የፋይናንስ ደህንነት ተቋም ይፋ አደረገ። እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ2004-2013 26 ቢሊዮን ዶላር አካባቢ በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ያጣችው ኢትዮጵያ ከዚሁ ገንዘብ መካከል 19.7 ቢሊዮን ዶላር ከህገወጥ ንግድ ጋር የተያያዘ መሆኑን ግሎባል ፋይናንሻል ኢንተለጀንስ አስታውቋል። ሃገሪቷ ከህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ጋር በተገናኘ እያጣች ያለችው ገንዘብ ከሃገሪቱ አመታዊ አጠቃላይ ምርት ውስጥ ከ5-10 በመቶ የሚሆነውን እንደሚሸፍንና መጠኑም ከአህጉሪቱ ሰፊ መሆኑን ተቋሙ ገልጿል። ኢትዮጵያ በተጨማሪ ቻይና፣ ሩሲያ፣ ሜክሲኮ፣ ህንድ እና ማሌዥያ ከፍተና ገንዘብን በህገወጥ ዝውውር ከሚያጡ ሃገራት መካከል ዋንኞቹ መሆናቸውን የፋይናንስ ተቋሙ አመልክቷል። ኢትዮጵያ ካላት አነስተኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴና የውጭ ንግድ ገቢ አኳያም በየአመቱ እያጣች ያለው ገንዘብ እጅግ ከፍተኛ መሆኑን የድርጅቱን ሪፖርት ዋቢ በማድረግ ዘ-ሲቲዝን የተሰኘ ጋዜጣ አርብ እለት ዘግቧል። የአለም ባንክን ጨምሮ የብሪታኒያ መንግስትና ሌሎች አለም አቀፍ ተቋማት ኢትዮጵያ የምታጣውን ገንዘብ እንዲቀንስ ለማድረግ የስልጠናና የምክር ድጋፍን እየሰጡ ኣንደሚገኝም ታዉቋል። በህገወጥ መንገድ ከሃገር የሚወጣው ገንዘብ በላኪና በአስመጪዎች እንዲሁም በሌሎች የገንዘብ ዝውውሮች መሆኑን የፋይናንስ የደህንነት ተቋሙ መረጃ አመልክቷል። ሀገሪቱ እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ2004 እስከ 2013 ድረስ ከሃገሯ የወጣው ወደ 26 ቢሊዮን ዶላርም በአፍሪካ ደረጃ ከፍተኛው ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን ትግሉ ከ10 ዓመት በኋላም እልባት አለማግኘቱ ተገልጿል። የመንግስት ባለስልጣናትም በበኩላቸው የህገወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመቆጣጠር የተለያዩ እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው ሲሉ ምላሽ መስጠት ዘሲቲዝን ጋዜጣ በዘገባው አስነብቧል።

Prof. Berhanu Nega Eritrean press's Person of the year 2015

ኤርትራን ፕሬስ የተባለ ድረገጽ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን የዓመቱ ምርጥ ሰው አድርጎ መረጠ
በሳምንት ከ600, 000 በላይ አንባቢዎች እንዳሉት የሚገልጸው ኤርትራን ፕሬስ የተሰኘው የመረጃ መረብ የ2015 ዓ.ም ፕሮፌሰር ብርርሃኑ ነጋን የዓመቱ ምርጥ ሰው አድርጎ መረጠ::
ከጁላይ 2015 ጀምሮ የኢሕ አዴግን መንግስት ለመጣል ኤርትራ ጠቅልለው መግባታቸውን የገለጸው ድረገጹ እንዲህ ያለውን ውሳኔ በመወሰናቸውና ትግሉን ለመምራት ያላቸውን ብቃት በመተንተን የዓመቱ ምርጥ ሰው ብሏቸዋል::
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ2007 ዘ-ሐበሻ አንባቢዎች የዓመቱ ምርጥ ሰው ተብለው መመረጣቸው የሚታወስ ሲሆን በወቅቱ ስለርሳቸው የሚከተለውን ጽፈን ነበር::
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በ1958 ዓ.ም ደብረዘይት አካባቢ የተወለዱ ሲሆን ምንም እንኳ የተወለዱት ከሃብታም ቤተሰብ ቢሆንም አስተዳደጋቸው ግን ራሳቸውን ችለው እንዲያድጉ እየተማሩ ነው:: ይህንን ፕሮፌሰር ብርሃኑ በሃገር ቤት ለሚታተም ጋዜጣ በ1997 ዓ.ም ሲናገሩ “አባቴ ነጋ ቦንገርን ልጅ እያለሁ ሲኒማ ራስ ጥሩ የህንድ ፊልም ወጥቶ ለማየት ሳንቲም ስጠኝ ስለው ራስህ ሰርተህ ስታገኝ ትገባለህ ይለኝ ነበር” (ቃል በቃል የተወሰደ አይደለም) ይላሉ:: አባታቸው አቶ ነጋ ቦንገር ሲያሳድጓቸው በማሞላቀቅ ሳይሆን ራሳቸውን መቻል እንዳለባቸው በማስተማር ነበር:: ይህም ለፕሮፌሰሩ ስኬት ጠቅሟቸዋል::
ፕሮፌሰሩ ወደ ሳሪስ አካባቢ ግሎባል የሚባል ደረጃውን የጠበቀ ሆቴል ከፍተው የነበረ ቢሆንም በሽብርተኛነት በኢትዮጵያ መንግስት ከተከሰሱ በኋላ ይህ ሆቴል ተወርሷል::
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ወደ ትግሉ ዓለም የገቡት ገና የ17 ዓመት ወጣት በነበሩበት ወቅት ነው:: ያን ጊዜ ከኢህ አፓ ጋር በሚሰሩበት ወቅት ብዙ ምስጢሮች ባይነገራቸውም መኪና ይነዱ ስለነበር የኢሕአፓ አመራሮችን ከቦታ ቦታ በመውሰድ አገልግሎት ይሰጡ እንደነበር አብረዋቸው ይታገሉ የነበሩ ሰዎች ለዘ-ሐበሻ ይናገራሉ:: እንዲሁም ፕሮፌሰር ብርሃኑ በወቅቱ በኢህአፓ አመራሮች እርምጃ ሊወሰድባቸው ሲል በሱዳን በኩል አምልጠው እንደጠፉ ከታሪካቸው ያሰባሰብነው መረጃ ያመለክታል::
በሱዳን በኩል አድርገው አሜሪካ ከገቡም በኋላ ትምህርታቸው ላይ በማተኮር በከፍተኛ ማዕረግ የተመረቁ ሲሆን ኢህአዴግ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ ኢትዮጵያ ጠቅልለው በመግባት ሃገራቸውን ማገልገል ጀምረዋል:: ፕሮፌሰር በቅድሚያ ኢሕ አዴግን ለመለወጥ አዳዲስ ሃሳቦችን ቢያቀርቡም ኢህ አዴግ ግን የሚለወጥ ድርጅት ሊሆን አልቻለም:: በዚህም ተስፋ ሳይቆርጡ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች ማህበርን በመመስረት ብዙ አስተዋጽኦ አበርክተዋል::
ከምርጫ 2007 በፊት ፕሮፌሰር ብርሃኑ እና ፕሮፌሰር መስፍን በብሄራዊ ሎተሪ አዳራሽ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በመሰብሰብ ስለ ነፃነትና መብት ምንነት በሰፊው በሕዝባዊ ስብሰባ ይሰብኩ ነበር:: በርካታ ተከታዮችን እያፈሩ መምጣታቸው ያስፈራው መንግስት ሁለቱንም ታዋቂ ፖለቲከኞች ሕገመንግስቱን በኃይል ለመናድ በሚል አስሮ ሲያንገላታቸው ቆይቷል::
ምርጫ 1997 እየቀረበ ሲመጣ በየወሩ በሂልተን ሆቴል ኢትዮጵያ በ2020 በሚል ምሁራን እየተሰባሰቡ ኢትዮጵያ በ2020 ዓ.ም ምን መሆን እንዳለባት እንዲመካከሩ ያደርጉ የነበሩት ፕሮፌሰር ብርሃኑ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር በነበሩበት ወቅት ደመወዛቸውን ለችግረኛ ተማሪዎች ያከፋፍሉ እንደነበር ይነገራል::
ፕሮፌሰሩ ቀስተዳመና የተሰኘ ፓርቲ አቋቁመው ከኢድሊ ጋር በመተባበር ታላላቆቹን መኢአድና ኢዴፓ-መድህንን አንድ በማድረግ ቅንጅት ፓርቲ እንዲፈጠርና በምርጫ 97 ኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ ለውጥ እንዲፈጠር ጥረው ነበር:: በዚህም የአዲስ አበባ ከንቲባ ሆነው በሕዝብ ተመርጠው የነበረ ቢሆንም መንግስት በሃይል ያመጣሁትን ስልጣን በስኪብርቶ አለቅም በሚል የፖለቲካውን ምህዳር ዘግቶታል::
በዚህ ምርጫ ሰብሰብም ፕሮፌሰር ብርሃኑ እስር ቤት ተወርውረው ነበር:: ከ እስር ቤት ከወጡ በኋላም ሰላማዊ ትግል ብቻውን ለውጥ አያመጣም በሚል ወደ ሁለገብ ትግል በመሸጋገር ግንቦት 7ን መሰረቱ:: ግንቦት ሰባት በአሁኑ ሰዓት ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር እየተዋሃደ ትግሉ ወደ አንድ አቅጣጫ እንዲሸጋገር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ሰርተዋል::

Protests in Oromia Region Returns to its Routine

ኢሳት ልዩ ዜና
በኦሮሚያ ክልል ህዝባዊ እምቢተኝነቱ ዳግም አገርሽቷል። በተለያዩ አከባቢዎች ግጭቶች ተፈጥረዋል። የተኩስ ልውውጥ ተደርጓል። ቦምብ ተወርውሮ ፈንድቷል። የሰው ህይወት ጠፍቷል። ብዙዎች ክፉኛ ቆስለዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ ወደ እስር ቤት ገብተዋል። ምዕራብ ወለጋ፡ ምዕራብ ሸዋ፡ ምስራቅ ሀረርጌ፡ አርሲ፡ ሌሎችም ሁለተኛውን ዙር ህዝባዊ ንቅናቄ ጀምረውታል። አቶ በቀለ ነጋአ በቁም እስር ላይ ናቸው።

https://www.facebook.com/ESATtv/videos/1074090439289704/