Thursday, 12 November 2015

(ከ አ.ታ ኦሮማይ)
"...አፄ ቴዎድሮስ የወቅቱ ልዕለ ኃያል ከነበረው የእንግሊዝ መንግስት ጋር መጣላታቸው ስህተት ነበር፤ ይህ ስህተታቸው ደግሞ ህይወታቸውን ለማጣታቸው ምክንያት ሆኗል፡፡
አፄ ምኒልክ ከአድዋ ድል በኋላ ኤርትራን ለጣልያን የሚለቅ ውል በመፈረም የኢትዮጵያ ሉአላዊ መሬትን አሳልፈው ሰጥተዋል፡፡
ከአፄ ቴዎድሮስ አጥፍቶ ጠፊነት ስልትም እንታቀብ፤ ከአፄ ምኒልክ በሉአላዊነት የመደራደር ልምድ ደግሞ እንማር..." መለስ ዜናዊ፡፡
ምንጊዜም ቢሆን አርበኝነትን መንቀፍ፣ ማንኳሰስና ማንቋሸሽ፤ ጀግኖች አርበኞችን ደግሞ ማጥላላት፣ ማዋረድና አፅማቸውን መስደብ በባንዳነትና በአገር ክህደት ተበክሎ ከበከተ፣ ከነተበና ከበሰበሰ ስነ-ልቦና የሚመነጭ እኩይና መሰርይ ባህሪ ነው፡፡
አዎ ባንዳዎች ዓላማቸው አገር በመሸጥ ሶልዲ መልቀም፤ ህዝብን አዋርዶ መከበርና መሾም እንጂ ለአገር ዳር ድንበር ለህዝብ ክብር መሞት አይደለም፡፡ ጥላቻን አንጂ ፍቅርን ሊሰብኩ አይችሉም፤ ክህደትን እንጂ ዕምነትን ፈፅሞ ሊያስፋፉ አይችሉም፤ የአርበኝነትን ታሪክ የማጠልሸትና የማጥፋት እንጂ የማበልፀግና ለትውልድ የማስተላለፍ ፍላጎትም ሆነ ዓላማ ጨርሶ የላቸውም፤ የክህደት እንጂ የአርበኝነት ታሪክ ያንቃቸዋል አይዋጥላቸውም፤ ጀግንነት ያቅራቸዋል፤ የአገር ፍቅር ያቅለሸልሻቸዋል፡፡ ይህ ሁሉ ቁም ነገር በእነሱ ውስጥ ፈፅሞ ስለሌለ ያስቀናቸዋልም፤ ከዘመን ዘመን እየደመቀና እየገነነ እየመጣ ባለው የጀግኖች አርበኞች እፁብ ድንቅ የሚያሰኝ ገድልና የማያረጅ ስብዕና ዓይናቸው ደርሶ ደም ይለብሳል፤ ነገር ግን መሆንን አይሹም፤ ቢሹም የባንዳነት ተፈጥሯቸው ስለማይፈቅድላቸው ጭራሽ አርበኛ መሆን አይችሉም፡፡ ለእነሱ አርበኝነት ማለት ባንዳነት ብቻ ነው፤ በተወለዱ በ40 ቀናቸው በይሁዳዊነት ፀበል የተጠመቁ በመሆናቸው፡፡
ባንዳዎች አገራቸው ሆዳቸው በመሆኑ የሚሞቱት ለከርሳቸው ብቻና ብቻ ነው፡፡ ባንዳዎች ንዋይን ከማፍቀር አልፈው ያመልኩታል፤ ስለሆነም ገንዘብ ለማግኘት የማያቀርቡት የመሰዋዕትነት አይነት የለም፡፡ የአገርን መሬት ይቆርሳሉ፤ ህዝብን አሳልፈው ይሰጣሉ፡፡
ባንዳዎች የህልውናቸው መሰረት፣ እስትንፋሳቸው ስልጣን በመሆኑ ህይወታቸውን የሚሰውት ለእሱና ለእሱ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህም ለአገር ሲል ህይወቱን የሰዋን ሊያደንቁና ሊወዱ አይችሉም፡፡
ባንዳዎች የክብር መገለጫቸው የአገር ክህደት፣ የህዝብ ጥላቻና፣ የመንፈስ ርኩሰትና ውርደት ታሪክ በመሆኑ መሰዋዕትነትና ፍቅርን አክብሮ ለመቀበል የሚያስችል ምንም አይነት መሻት በውስጣቸው ፈፅሞ የለም፡፡
ባንዳዎች ዋነኛ ተግባራቸው የአርበኝነትን ታሪክ ከዝክረ መዝገብ መፋቅ ብቻ ሳይሆን የባንዳነት ጥቁር ጥላሸት መቀባትም ጭምር ነው፡፡ በተለይም ደግሞ እንደ እነ አፄ ምኒልክ አይነት የጥቁር ህዝብ ነፃነት ቀንዲሎች ቦግ ብለው በርተው በባንዳነት ዋሻ ውስጥ ተቀብሮ በድቅድቅ ጨለማ የተዋጠውን ማንነታቸውን አጋልጠው እርቃናቸውን ስለሚያስቀሩት አይመቿቸውም፡፡
አዎ መለስ ዜናዊ በተወለደ በአርባኛው ቀን በይሁዳዊነት ፀበል ተጠምቆ በህዝብ የጥላቻ ስነ-ልቦና ተኮትኩቶ አገር ተሸጦ የተለቀመ ሶልዲ እየበላ ያደገ አድጎም በህዝብ ውርደት ነግሶ ኖሮ በኢትዮጵያችን ላይ ታላቅ ክህደትን ፈፅሞ የሙጥኝ ብሎ ለስልጣኑ የሞተ እልምያለ የባንዳ ልጅ ባንዳ ነው፡፡
ባንዳ የባንዳ ልጅ ምንጊዜም ጠፊ ነው
እሱን እንደ አርበኞች አልፋና ኦሜጋ ያደረገው ማን ነው፤
ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን በ30 ዲናር ሸጠው- በመዳፎቻቸው ሙሉ ክህደትን የዘገኑ
ቀፎውን በዘረኝነት ዘንግ በመሸንቆር ንቦችን የበተኑ
በክህደት ተጠምቀው በውሸት የፀኑ፤
ከርስ ከህሊና የበለጠባቸው
መንደር ከአገር ጎልቶ ሚታያቸው
በደም የሰከሩ ግፍ ያሻገታቸው
ከምላስ በስተቀር ምንም የሌላቸው
ከድንቁርና አፈር በዘር ውሃ አቡክቶ ጋግሮ ያወጣቸው
በስብሰው የገሙ የቁም ሬሳዎች ዞምቢዎች ናቸው፤
ብቸኛው አማራጭ ብቸኛው መፍትሄ ከኢትዮጵያ- ጠራርጎ ቆፍሮ መቅበር ነው
መቃብራቸው ላይ "የገፋሽ ይገፋ" በማለት መፃፍ ነው፡፡
ዛሬ ላይ አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ እያፋፋመው የሚገኘው የአርበኝነት ትግል ባንዳነትን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት የሚደረግ ነው፡፡
ከስንዴው ማሳ ላይ እንክርዳዶች በቅለው
ከስንዴው ጋራ በስህተት ታጭደው ተወቅተው
ታፍሰው ተሰፍረው ጎተራ ውስጥ ገብተው
ከዚያም ተፈጭተው ከስንዴው ጋር ልመው
ዳቦ ይሆናሉ ሊጥ ሆነው ተጋግረው
ዳቦውም አይጣፍጥ ይመራል ስንቀምሰው
ግን እንክርዳዶቹ ከዳቦው ውስጥ ሆነው
"ቅመም ነን" ይላሉ የበለጥን ከዳቦው
የትናንትናውን ማንነታቸውን ፈፅመው ዘንግተው፡፡
አርበኝነት ባንዳነትን ያሸንፋል!

Saturday, 31 October 2015

የአርበኞች ግንቦት 7 ስብስቦችን በመላ አገሪቱ እናደራጅ

የአርበኞች ግንቦት 7 ስብስቦችን በመላ አገሪቱ እናደራጅ!
የኢትዮጵያ ወጣቶች የህወሓት አገዛዝ በአገራችን ላይ የሚያደርሰውን በደል የሚገልጹ እና ከዚህ በደል መገላገያ መንገድ የሚያመላክቱ ፓስተሮች በግድግዳዎችና ምሰሶች ላይ እየለጠፉ፤ በራሪ ወረቀቶችን እየበተኑ እና የግድግዳ ላይ ጽሁፎችን እየፃፉ ነው። ባለፈው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ በተለያየ መጠን ቢሆንም በአገሪቱ አብዛኛዎቹ ትላልቅ ከተሞች ውስጥ ይህ የቅስቀሳ ዘዴ ተግባራዊ ሆኗል። ይህ ተግባራዊ ሥራ የአርበኞች ግንቦት 7 አባላትና ደጋፊዎች በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች ያሉ መሆኑ ተጨባጭ ማሳያ ሆኗል።
አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች የሚገኙ ወጣቶች እያደረጉት ያለውን እንቅስቃሴ ያደንቃል፤ ተግባሮቻቸው ባነሰ ኪሳራ የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በጠንካራ ሥነ ሥርዓት በተዋቀሩ የአርበኞች ግንቦት 7 ስብስቦች እንዲመሩ ያበረታታል። ከተግባራዊ ሥራዎች ጎን ለጎን የድርጅት አቅም ግንባታ መሠራት ያለበት አቢይ ጉዳይ መሆኑን አርበኞች ግንቦት 7 በአጽንዖት ያስገነዝባል። በዚህም መሠረት ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ አባላትና ደጋፊዎችች ለድርጅትና ለአባላት ጥንካሬ ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጡ አበክሮ ያሳስባል።
ነፃነት ናፋቂ ወጣቶች የሚያደርጉት የሕዝባዊ እምቢተኝነት መገለጫ ተግባራት ዓይነታቸው እየተቀያየረ እንዲቀጥል በእቅድ መመራትና በድርጅት መታገዝ አለባቸው። የመረጥነው ሁለገብ የትግል ስትራቴጂ እምንፈልገው ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ላይ እንዲያደርሰን የኢትዮጵያ ሕዝብ በሁለቱም የትግል ስልቶች አኳያ መደራጀት ይኖርበታል።
በዚህም መሠረት ለሕዝባዊ አመጽ ጠንካራ የአርበኛ ሠራዊት ማደራጀት እንደሚያስፈልግ ሁሉ ለሕዝባዊ እምቢተኝነትም ጠንካራ ድርጅት በኢትዮጵያ ከተሞችና ገጠሮች፤ በሥራና በመኖሪያ አካባቢዎች ማደራጀት ይገባል። ስለሆነም በከፍተኛ ምስጢር የተደራጁ እና በከፍተኛ ብቃት የሚመሩ የአርበኛ ግንቦት 7 ክበባት በየቦታው፣ በብዛት እና በጥንቃቄ መደራጀት ይኖርባቸዋል። ድርጅት ድርጅት የሚሆነው ደግሞ በሥነ ሥርዓት ሲዋቀርና በብቃት ሲመራ ነው። ስለሆነም ነፃነት ናፋቂ የሆነ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በሥነ ሥርዓት በተዋቀሩ ትናንሽ ስብስቦች ራሱን እንዲያደራጅ፤ የፓለቲካ፣ የታሪክ እና የጠቅላላ እውቀት ግንዛቤውን ለማዳበር እንዲሁን መሠረታዊ የደህንነት ጥበቃ ክህሎቶችን እንዲያጎለብት ጥረት እንዲያደርግ ተደጋጋሚ ማሳሰቢያ መስጠት አስፈልጓል።
የተደራጀ ስብስብ ለሚንቀሳቀስበት አካባቢ ተስማሚ የሆኑ የቅስቀሳ ዘዴዎችን ለበላይ አመራር አሳውቆ ሲፈቀድ ተግባራዊ ማድረግ ይችላል። የተደራጀ ስብስብ ለአካባቢው ባህልና ስነልቦና ተስማሚ የሆነ መንገድ ተጠቅሞ የሕዝብን የልብ ትርታ ማዳመጥ፤ ለጥያቄዎቹም መፍትሄ መሻት ይችላል። የተደራጀ ስብስብ የጠላትን እንቅስቃሴ እየሰለለ መረጃ ለነፃነት ኃይሎች እንዲደርስ የተመቻቸ ሁኔታ መፍጠር ይችላል። የተደራጀ ስብስብ ሕዝብ በሥርዓቱ ላይ እንዲያምጽ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤ ሆኖም ግን አቅም ሳይጎለበትም አመጽ ተነስቶ በነፃነት ታጋዮች ላይ አላስፈላጊ መስዋዕትነት እንዳይከፈል ይከላከላል። ሁኔታዎች የተመቻቹ መሆናቸው የበላይ አመራር ሲያምንበት ደግሞ አመጽ በመቀስቀስ ትግሉ ግቡን ሳይመታ እንዳይበርድ ፀንቶ ይቆማል። የተደራጀ ስብስብ ከአርበኞች ግንቦት 7 የሚሰጠውን ድርጅታዊ መመሪያ ተከትሎ ተግባራቱን ይከውናል፤ “ተነስ!” ሲባል ለመነሳት ራሱን ዝግጁ ያደርጋል።
ስለሆነም በከፍተኛ ሥነሥርዓት የታነፁ፣ በብቃት የሚመሩ፣ ከአርበኞች ግንቦት 7 አመራር ጋር የጠበቀ ግኑኝነት ያላቸው በርካታ ስብስቦችን በመላ አገሪቱ ውስጥ እናደራጅ።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

የህወሓት አገዛዝ የቀድሞው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ)
የህወሓት አገዛዝ የቀድሞው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት የነበሩትን እየለቀመ ከመከላከያ ኃይሉ እያባረራቸው መሆኑ ታወቀ፡፡
====================================================
ህወሓት በ1983 ዓ.ም መላ አገሪቱን በነፍጥ እንደተቆጣጠረ በሁለት ያለፉ የኢትዮጵያ መንግስታት ከፍተኛ የህዝብ ሀብት፣ ዕውቀትና ጉልበት ፈሶበት ለዘመናት በስንት ልፋትና ጥረት የተገነባውን የአገር መከላከያ ሰራዊት ባደረበት ጭፍን ጥላቻና ቂም ብቻ ተመስርቶ "የደርግ ነው" በሚል ሰበብ ባንድ ጀምበር ንዶ ማፈራረሱን አገር ያወቀው ፀሃይ የሞቀው ሀቅ ነው፡፡ 
ከበረሃ የመጡ ድኩማን ታጋዮቹን ለሙያው የሚመጥን ምንም አይነት ዘመናዊ ዕውቀት ሳይኖራቸው የጀነራልነት ማዕረግ በማሸከም በአየር ኃይሉና በምድር ኃይሉ ውስጥ በሚገኙ የአዛዥነት ቦታዎች ላይ እነሱን ብቻ አስቀምጦ ስልጣኑን ለመጠበቅ ብቻ እንዲተጉለት በማድረግ የአገራችንን ብሄራዊ ደህንነት አደጋ ላይ ጥሎት ይገኛል፡፡
ህወሓት የተባለው ዘረኛ ቡድን ውስጡ በቂምና በጥላቻ ብቻ ተሞልቶ ያፈራረሰውን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት አደጋ ባንዣበበበት ጊዜ ጥሪ በማድረግ መልሶ ለመሰብሰብ የሞከረ ሲሆን ከጦርነቱ በኋላ ደግሞ አብዛኞቹን ከተጠቀመባቸው በኋላ እንደገና አባሯቸዋል፡፡
አሁን ደግሞ አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ እያፋፋመው ከሚገኘው የአርበኝነት ትግል ጋር በተያያዘ ከትግራይ ተወላጅ የህወሓት ተጋዮች ውጭ በሆኑ ወታደራዊ አዛዦች ላይ ዕምነት በማጣቱ የመከላከያ ኃይሉን የማጥራት የወቅቱ አንገብጋቢ ውሳኔውን የቀድሞ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላትን በማባረር ተግባራዊ ማድረግ ጀምሯል፡፡
ቂምና በቀሉ መቸም የማይበርድለት ህወሓት በተደጋጋሚ የደም ቁማር ሲቆምርባቸው ከኖሩት የተባረሩ የቀድሞው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት አብዛኞቹ የአርበኝነት ትግሉን በመቀላቀል ላይ ናቸው፡፡

Tuesday, 27 October 2015

የምንከፍለዉ የህይወት መስዋእትነት በእጃችን እንደሆነ የአለም ህዝብ እንዲያቅልን እንፈልጋለን፡፡" ይላሉ።

ጥቅምት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በድቡብና ጋምቤላ የድንበር ከተማ በሆነቸው ቴፒ ራሳቸውን ያደራጁ ወጣቶች በመልካም አስተዳደርና ህዝቡን አፍኖ በመግዛት ለስቃይ ዳርገውታል ባሉዋቸው የመንግስት ታጣቂዎች እና ሹማምንት ላይ የሚያደርሱትን የሃይል ጥቃት መቆጣጠር እየተሳነው የመጣው መንግስት ካለፈው አርብ ጀምሮ፣ በተለያዩ የከተማው አካባቢዎች ጥቃቱን በማስፋት ነዋሪዎች ሲያሰቃይ ሰንብቷል። የመንግስት ታጣቂዎች፣ የነዋሪዎችን መኖሪያ ቤቶች ሰብረው በመግባት፣ ህጻን፣ አዛውንት፣ ሴት ወንድ ሳይሉ ያገኙትን የደበደቡ ሲሆን፣ አንዳንድ ወጣቶችንም ይዘው አስረዋል። " ሽፍቶችን የሚረዳው ማን ነው፣ አውጡ?" በማለት ጥቃት ሲፈጽሙ የቆዩት ታጣቂዎች፣ የሚፈልጉትን ለማግኘት ባለመቻላቸው፣ በጅምላ ወጣቱን እያዋከቡት መሆኑን ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል። ጥቃቱን ተከትሎ የቴፒ ወጣቶች መግለጫ አውጥተው ለኢሳት ልከዋል። መግለጫው " የቴፒ ወጣቶች ቡድን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ላለፉት 24 አመታት መንግስት የጫነበትን የዘረኝነት ቀንበር ለማስወገድ ሁሉም በተናጠል ሲታገል ቆይቷል" ካለ በሁዋላ፣ ሆኖም የሰላማዊ መንገድን አሻፈረኝ ያለው መንግስት ህዝቡን ሲገድል፣ ሲያስር፣ ሲፈናቅል በመቆየቱ፣ ካለፈው አመት ጀምሮ በደልና ጭቆና አንገሸገሻቸው ወጣቶች ዱር ቤቴ ብለው የህይወት መስዋትነት ለመክፈል ተገደዋል።" ሲል ያብራራል። "የመንግስት ወታደሮች በህዝቡ ላይ እያካሄዱ ያለውን ድብደባና እንግልት እንዲያቆሙ ፣ ወታደሩ የህዝብ ልጅ መሆኑን መዘንጋት እንደሌለበትና ነገ በታሪክ ተጠያቂ እንደሚሆኑ " ወጣቶቹ በመግለጫው በማሳሰብ፣ "መንግስት በህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ ለማስቆም ካልቻለና ለሚነሱት ጥያቄዎች መልስ መስጠት ከተሳነው፣ የመንግስት ወታደሮች የሚወስዱትን ጥቃት በመፍራት ትግላችንን አናቆምም" ብለዋል። መግለጫቸውን ሲያሳርጉም " ምንም እንኩዋን ጦርነትን የሚያወርስ ጦረኛ መንግስት ቢኖረንም አሁንም ቢሆን የቴፒ ወጣቶች ቡድን ሰላማዊ በሆነ መንገድ የቴፒ ህዝብ የሰላም ችግር እንዲቀረፍ ይጠይቃል፡፡ ነገር ግን ይህ ሳይሆን ቢቀር የምንከፍለዉ የህይወት መስዋእትነት በእጃችን እንደሆነ የአለም ህዝብ እንዲያቅልን እንፈልጋለን፡፡" ይላሉ።
ጥቅምት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በድቡብና ጋምቤላ የድንበር ከተማ በሆነቸው ቴፒ ራሳቸውን ያደራጁ ወጣቶች በመልካም አስተዳደርና ህዝቡን አፍኖ በመግዛት ለስቃይ ዳርገውታል ባሉዋቸው የመንግስት ታጣቂዎች እና ሹማምንት ላይ የሚያደርሱትን የሃይል ጥቃት መቆጣጠር እየተሳነው የመጣው መንግስት ካለፈው አርብ ጀምሮ፣ በተለያዩ የከተማው አካባቢዎች ጥቃቱን በማስፋት ነዋሪዎች ሲያሰቃይ ሰንብቷል። የመንግስት ታጣቂዎች፣ የነዋሪዎችን መኖሪያ ቤቶች ሰብረው በመግባት፣ ህጻን፣ አዛውንት፣ ሴት ወንድ ሳይሉ ያገኙትን የደበደቡ ሲሆን፣ አንዳንድ ወጣቶችንም ይዘው አስረዋል። " ሽፍቶችን የሚረዳው ማን ነው፣ አውጡ?" በማለት ጥቃት ሲፈጽሙ የቆዩት ታጣቂዎች፣ የሚፈልጉትን ለማግኘት ባለመቻላቸው፣ በጅምላ ወጣቱን እያዋከቡት መሆኑን ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል። ጥቃቱን ተከትሎ የቴፒ ወጣቶች መግለጫ አውጥተው ለኢሳት ልከዋል። መግለጫው " የቴፒ ወጣቶች ቡድን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ላለፉት 24 አመታት መንግስት የጫነበትን የዘረኝነት ቀንበር ለማስወገድ ሁሉም በተናጠል ሲታገል ቆይቷል" ካለ በሁዋላ፣ ሆኖም የሰላማዊ መንገድን አሻፈረኝ ያለው መንግስት ህዝቡን ሲገድል፣ ሲያስር፣ ሲፈናቅል በመቆየቱ፣ ካለፈው አመት ጀምሮ በደልና ጭቆና አንገሸገሻቸው ወጣቶች ዱር ቤቴ ብለው የህይወት መስዋትነት ለመክፈል ተገደዋል።" ሲል ያብራራል። "የመንግስት ወታደሮች በህዝቡ ላይ እያካሄዱ ያለውን ድብደባና እንግልት እንዲያቆሙ ፣ ወታደሩ የህዝብ ልጅ መሆኑን መዘንጋት እንደሌለበትና ነገ በታሪክ ተጠያቂ እንደሚሆኑ " ወጣቶቹ በመግለጫው በማሳሰብ፣ "መንግስት በህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ ለማስቆም ካልቻለና ለሚነሱት ጥያቄዎች መልስ መስጠት ከተሳነው፣ የመንግስት ወታደሮች የሚወስዱትን ጥቃት በመፍራት ትግላችንን አናቆምም" ብለዋል። መግለጫቸውን ሲያሳርጉም " ምንም እንኩዋን ጦርነትን የሚያወርስ ጦረኛ መንግስት ቢኖረንም አሁንም ቢሆን የቴፒ ወጣቶች ቡድን ሰላማዊ በሆነ መንገድ የቴፒ ህዝብ የሰላም ችግር እንዲቀረፍ ይጠይቃል፡፡ ነገር ግን ይህ ሳይሆን ቢቀር የምንከፍለዉ የህይወት መስዋእትነት በእጃችን እንደሆነ የአለም ህዝብ እንዲያቅልን እንፈልጋለን፡፡" ይላሉ።

ረሃብና ድህነት ታሪክ ሆኗል የሚባለውም ተረት ነው

ጥቅምት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦሮሞ ፌደራሊስት ሊቀመንበር እና የመድረክ የአመራር አባል የሆኑት ዶ/ር መረራ ጉዲና ይህን ምላሽ የሰጡት ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች የቀረበውን የውይይት ግብዣ ተቃዋሚዎች ውድቅ ማድረጋቸውን ለፓርላማ አባላት መናገራቸውን ተከትሎ ነው። መንግስት በጠራው የአምስት ኣመታት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውይይት ላይ ያልተሳተፉ እንደመድረክ፣ ሰማያዊ እና መኢአድ ያሉ ፓርቲዎች ያቀረቡት ምክንያተ ውሃ ያማያነሳ ነው ያሉት አቶ ሃይለማርያም ፣ ፓርቲዎቹ ያልተሳተፉት በሕጋዊ መንገድ የተመረጠ መንግስት አይደለም በማለት መሆኑን ጠቅሰው ወደፊት ከየትኛው መንግስት ጋር እንደሚወያዩ እናያለን ሲሉ ዝተዋል፡፡ ዶ/ር መረራ ሲናገሩ፣ "በቅድሚያ አንነጋገርም አላልንም፣ ቅድሚያ መሰረታዊ በሆኑት የአገሪቱ ጉዳዮች ላይ ለምሳሌ ነጻ ምርጫን ፣ ነጻ ሚዲያን፣ በነጻነት መንቀሳቀስንንና በመሳሰሉት መሰረታዊ መብቶች ጉዳይ እንነጋገር " ነው ያለው ካሉ በሁዋላ፣ እነሱ በሚሉት ጉዳይ ላይ ለመነጋገርም ፣ በር ዘግቶ ሳይሆን፣ በነጻ ሜዳ፣ ለህዝብ በቀጥታ በሚተላለፍ መልኩ መሆን አለበት በማለት በጽሁፍ መግለጻቸውን ተናግረዋል። መድረኩን ተጠቅማችሁ ለምን ሃሳባችሁን ለማስተላለፍ አልቻላችሁም በሚል ለተጠየቁት ዶ/ር መረራ፣ የኢህአዴግ ፖሊሲ ስልጣን ወይም ሞት በመሆኑ፣ የልጅ ስራ መጫወቱ ትርጉም የለውም ብለዋል። አገሪቱ አደጋ ውስጥ ናት ያሉት ዶ/ር መረራ ዲሞክራሲው የፖለቲካ ቅርቃር ውስጥ መግባቱን፣ አገሪቱ ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ እያመራች መሆኑዋንና የሚባለው ዲሞክራሲ፣ ሰላምና መረጋጋት አለመኖሩን እንዲሁም ረሃብና ድህነት ታሪክ ሆኗል የሚባለውም ተረት ነው በማለት ገልጸዋል። በሌላ ዜና ደግሞ ጠ/ሚኒስትሩ የብድር አወሳሰዳችን የተለየ በመሆኑ ለጫና አልተዳረግንም ብለዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በፓርላማ ተገኝተው ከምክርቤቱ አባላት የብድር ዕዳ ክምችት አለ ስለመባሉ የተጠየቁ ሲሆን መንግስታቸውን የብድር አወሳሰድ ከሌሎች የአፍሪካ አገራት ጋር በማነጻጸር እኛ የተሻልን ስለሆነ ለዕዳ ጫና አልተዳረግንም ብለዋል፡፡ ሌሎች የአፍሪካ አገሮች ለዕለት ተዕለት ሥራ ማስኬጃና ደመወዝ ክፍያ ብድር ይወስዳሉ፣ እኛ ግን ለትርፍ የሚሰሩ ተቋማት ማለትም እንደቴሌ፣ አሌክትሪክ፣ ስኳር፣ ባቡር ወዘተ ስንል ብድር እንወስዳለን፣ ኩባንያዎቹ ሰርተው ብድራቸውን የሚከፍሉ በመሆኑ ያን ያህል ስጋት እንደሌለው በመግለጽ ለማጣጣል ሞክረዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የተወሰደው የኢትዮጽያ የኤክስፖርት ዘርፍ አፈጻጸም ባለፉት ሶስት ኣመታት የተዳከመ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ይህ ክስተት በዕዳ ጫና አለካክ ላይ የራሱ ተጽዕኖ እንዳለው አምነዋል፡፡ ለልማት ስራዎች ብድር የምንወስደው የመክፈል አቅም ስላለን ነው የሚሉት አቶ ሃይለማርም መክፈል እስከቻልን ድረስ ብንወስድ ችግር የለውም ዓይነት መልዕክት ለማስተላለፍ መድረኩን ተጠቅመውበታል፡፡ የኣለም ባንክ በቅርቡ ኢትዮጽያ ከፍተኛ ዕዳ ጫና ካለባቸው የአፍሪካ አገራት አንዱዋ መሆንዋን በመጥቀስ መንግስት ጥንቃቄ እንዲደርግ መምከሩ የሚታወስ ነው፡፡
http://ethsat.com/

‪#‎RIP‬ ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ እሸቴ

‪#‎RIP‬ ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ እሸቴ ከጎንደር ከተማ እምብርት ፒያሳ ጀምሮ እጁን ሊይዙ የተከታተሉትን ፖሊሶች ቀበሌ 6 ቂርቆስ አካባቢ እስኪደርስ "አትቅረቡኝ! ብትመለሱ ይሻላችኋል እያለ የለመናቸው ሲሆን ነገር ግን ፖሊሶቹ ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ባለመቻላቸው ቆራጥ እና የማያዳግም እርምጃ ወስዷል፡፡ ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ እሸቴ በያዘው ኮልት ሽጉጥ አንዲት ጥይት ብቻ እስክትቀረው እጁን ሊይዙ ከተከታተሉት ፖሊሶች ስድስቱን እያለመ ከረፈረፋቸው በኋላ በመጨረሻዋ ጥይት ራሱን ገድሏል፡፡ ታጋይ ዘመነ ከኤርትራ ለኢሳት ከተናገረው የተውሰደ.
http://ethsat.com/esat-radio-mon-26-oct-2015/