Thursday, 20 April 2017

በጎንደር የቦንብ ፍንዳታ ተከሰተ

በጎንደር የቦንብ ፍንዳታ ተከሰተ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተደጋጋሚ የቦንብ ፍንዳታን ባስተናገደችው ጎንደር ማክሰኞ ምሽት 2 ሰአት አካባቢ ታክሲ ማዞሪያ በጌምድር ሆቴል አካባቢ ቦንብ መፈንዳቱን የአይን እማኞች ተናግረዋል። በፍንዳታው በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት አለመድረሱን የሚገለጹት እማኞች በፍንዳታው ወቅት ከፍተኛ ድምጽ ከመሰማቱ ጋር ተያይዞ በአካባቢ መደናገጥ ተፈጥሮ ነበር ብለዋል። የመከላከያ እና የፌደራል ፖሊስ አባላት ከ15 ደቂቃ በሁዋላ ወደ አካባቢው በመምጣት መንገዶችን በመዝጋት መንገድ ላይ ያገኙዋቸውን ሰዎች ይዘው አስረዋል። ለጥቃቱ እስካሁን ሃላፊነቱን የወሰደ አካል የለም።

No comments:

Post a Comment