“እኔና ዳንኤል ሺበሺ ባለቤት አልባ የግፍ እስረኞች ሆነናል። ታስረንም በምንገኝበት ቦሌ ፖሊስ መምሪያ ‘የእናንተ ጉዳይ ከአቅሜ በላይ ነው፤ እናንተን መክሰስም ይሁን መፍታት አልችልም’ በማለቱ ወደ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ እንደምንሔድ ዛሬ ጠዋት ተነገረን። በተባልነውም መሠረት በጠዋት እቃችንን ሸክፈን (ይዘን) ወደ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ሔድን - ከመርማሪዎቻችን ጋር።
ማዕከላዊ እኛን አልቀበልም አለ። ወዲያውም ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን (3ተኛ) ተላክን። ይህም ኮሚሽን "አልቀበልም፤ አልችልም" የሚል ምላሽ ሰጠ።
በመጨረሻም ልደታ ፍርድ ቤት የሚገኘው የዐቃቤ ሕግ ቢሮ ጉዳያችንን እንዲያየው መዝገባችንን የያዙት መርማሪ ፖሊሶች ማስረጃ የሚሏቸውን ሰነዶች (ስልኮቻችንን ጭምር) ሰጥተው ተመልሰን ወደ ቦሌ ፖሊስ መምሪያ መጣን።
“አምስት ወራት በግፍ መታሠራችን ሳያንስ፣ ለተጠራጠርንበት ጉዳይ እስካሁን መፍትሔ የሚሰጠን አካል በመጥፋቱ በሀገራችንም በጣም አዝነናል። ግን ለተሻለች ሀገር ግንባታ ዛሬም ሆነ ነገ ጠንክሬ እንደምታገል ልቤ በፅኑ ያምናል።
“ኃይልን በሚሰጠኝ በፈጣሪ ሁሉን እችላለሁ።" ~ ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ፡፡ ምንጭ በፍቃዱ ሀይሉ ከ ዞን 9
No comments:
Post a Comment