Friday, 21 April 2017

አዲስ አበባ (ዝግ )ስብስባ

ህወሀት ወያኔ
ከውስጥ ታጋይ አርበኛ የተላከ መረጃ በአቶ ደብረጼዮን የሚመራው ቡድን ከወትሮው በተለየ አስቸኳይ ስብስባ ተቀምጧል መንስኤው አቶ ኋይለማሪያም ደሳለኝ ለውጭ ጋዜጠኞች ሊሰጡት በነበርው መግለጫ ባልታወቀ ሁኔታ በደብረጼዮ ትዛዝ መቋረጡን ተከትሎ፡አንደኛ ይሂን ሚስጥር ለኢሳት እንዲት ደረሰው? በሚል የተነሳ ጭቅጭቅ፡ከምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩም አቶ ደመቀ መኮነን? ጠቅላይ ሚንስትሩም አቶ ኋይለማሪያም ደሳለኝ በተገኝበት በአጠቃላይ የኢህደግ ሚንስትሮችበተገኙበት ግምገማ አቶ  ደብርጼዮ ጠቅላይ ሚንስትሩ ለውጭ ሚዲያ ሊያቀርቡት የነበረው እኛ ሣንወያይበት ሊቀርብ በፍጹም አይችልም እኔንም ሆነ በረከት ስምዐን ሳንነጋገርበት እንዲት መግለጫው እነደሚሰ ጥበትጥንቃቂ በተሞላበት መንገድ መሰጠት ያለበት በአሁኑ በሀገር ውስጥ ብዙ ችግር አለብን የውጭ ድፕሎማሲያችን ብዙ ነገሮችን ተፅኖ እያሳደረብን በአለንበት ወቅት ምንም ዓይነት መግለጫ አይሰጥም ሲሉ በተቃራኔው ሊሎቹ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ስለሆነ   መግለጫ መስጠት ተገቢነው ብለዋል፡ እነደብረጼዮ ግን ቁጣ በተሞላበት መንገድ ይሂን የሚመለከተው የትግራይ ልጆች የሞቱለት አላማ እኛው ነን እናተን ያስቀመጥናቹህ እኛው ነን አርፋቹህ ተቀመጡ አሉ ምክትል ጠቅላይ ምንስትሩ አቶ ደመቀ መኮነን እንዲህ ብለዋል የኢህደግ ህገ መንግስት በሚለው  መቀጠል አለብን ሁላችንም ለህገ መንግስቱ የሚገባን ሰርተናል፡ አቶ ኋይለማሪያምም ከመናገር ተቆጥበዋል ዝምታን መርጠዋል የፈሩም ይመስላል ከፊታቸው የፍራቻ መልዕክት ይታያል፡አቶ አባይ ጻሃየ በመለስ ቦታ ያስቀመጥነህ እኛው መቀመጥ አልጠፋንም ነበር የውጩን ጫና ለመቀንስ እንጅ ህገ መንግስቱን ያፅደቅነውም ሆነ የመሰርትነው  በድማችን አሉ።
ይሂን ተከትሎ ነው ነባር የህወሀት ታጋዮች ሣይቀር ያሳተፈ አቶ ስብሃት ነጋ፡ አቶ ፅጌ አብርሃ፡ አቶ አርከበ ቆብዮ፡ዶ/  ቴዎድሮስ አድህኖምም አቶ አዲሱ ለገሠ፡ እንዲሁም ከአሚሪካንና ከሎንዶን ከውጭ ካሉት ደጋፊዎችን ያካተተ ዝግ confres ስብስባ እየተካሂደ ነው።
ድል ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ።
ሞት ለባንዳዎች

Thursday, 20 April 2017

በጎንደር የቦንብ ፍንዳታ ተከሰተ

በጎንደር የቦንብ ፍንዳታ ተከሰተ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተደጋጋሚ የቦንብ ፍንዳታን ባስተናገደችው ጎንደር ማክሰኞ ምሽት 2 ሰአት አካባቢ ታክሲ ማዞሪያ በጌምድር ሆቴል አካባቢ ቦንብ መፈንዳቱን የአይን እማኞች ተናግረዋል። በፍንዳታው በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት አለመድረሱን የሚገለጹት እማኞች በፍንዳታው ወቅት ከፍተኛ ድምጽ ከመሰማቱ ጋር ተያይዞ በአካባቢ መደናገጥ ተፈጥሮ ነበር ብለዋል። የመከላከያ እና የፌደራል ፖሊስ አባላት ከ15 ደቂቃ በሁዋላ ወደ አካባቢው በመምጣት መንገዶችን በመዝጋት መንገድ ላይ ያገኙዋቸውን ሰዎች ይዘው አስረዋል። ለጥቃቱ እስካሁን ሃላፊነቱን የወሰደ አካል የለም።

ስለታፈኑት ፖሊሶች የአካባቢውን ባለስልጣናት ለማናገር ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም

አርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ሚያዚያ 8 ቀን 2009 ዓም በትክል ድንጋይ እና በወገራ መሃል ልዩ ስሙ ጭጋሳ ቀበሌ ላይ ሳጅን ያለውቀን አበበ እና ኮንስታብል ሙሉጌታ የተባሉትን የፖሊስ አባላትን አፍኖ መውሰዱን ለኢሳት በላከው መረጃ አስታውቋል። ስለታፈኑት ፖሊሶች የአካባቢውን ባለስልጣናት ለማናገር ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም። በሌላ በኩል ከዚህ ቀደም በአማራ ክልል የጸጥታ ስራ ለመስራት ለክልሉ ፖሊሶችና ለክልሉ ልዩ ሃይል አባላት ተሰጥቶ የነበረው ስልጣን በኮማንድ ፖስቱ እንዲወሰድ ከተደረገ በሁዋላ የክልሉ የጸጥታ አካላት አመኔታ አጥተው ከጥቅም ውጭ መደረጋቸውንና ማንኛውም ውሳኔ በህወሃት በሚመራው ኮማንድ ፖስት እንደሚሰጥ የፖሊስ ምንጮች ገልጸዋል። ፖሊሶች “ለኮማንድ ፖስቱ ታማኝ የሆኑና ያልሆኑ” በሚል መከፈላቸው እርስ በርስ እንዳይተማመኑ አድርጓቸዋል። የፖሊስ ሙያ ገለልተኛ ነው በወታደራዊ እዝ ሊመራ አይችልም የሚሉ አስተያየቶችን ያቀረቡ ፖሊሶች የተለያዩ ሰበቦች እየተፈጠሩላቸው ከስራ እንዲሰናበቱ ወይም በፈጠራ ወንጀል እንዲታሰሩ እየተደረገ ሲሆን የኮማንድ ፖስቱን ተእዛዝ አሜን ብለው የሚቀበሉ ደግሞ የደረጃ እድገት እየተሰጣቸው ነው። እንደ ምንጮች መረጃ ኮማንድ ፖስቱ “የክልሉ አመራር በክልሉ ውስጥ የሚታየውን የጸጥታ መደፍረስ እንዲቆጣጠር ስልጣኑን ከመመለሳችን በፊት የለውጥ ሃይሎችን የሚደግፉት አብዛኞቹ ፖሊሶች ግምገማ ተካሂዶ እንዲባረሩ ይጠይቃል። አሁን ያሉት ፖሊሶች በሚያሳዩት አቋም የክልሉን ጸጥታ የማስከበር ስራ እንዲሰሩ መፍቀድ ማለት ከወራት በፊት የታየውን ህዝባዊ አመጽ እንዲደገም ማድረግ ነው በሚል ቁጥጥሩን ለክልሉ ባለስልጣናት ለመመለስ ፈቃደኛ አለመሆኑን ግልጽ አድርጓል። በዚህም የተነሳ የአማራ ክልል ባለስልጣናት በክልላቸው ውስጥ ስለሚደረገው ነገር ምንም መረጃ እንደሌላቸውና ተንሳፈው እንደሚገኙ ምንጮች ገልጸዋል።

Wednesday, 12 April 2017

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ትላንት ከእስር ቤት የላከው አጭር ደብዳቤ

  “እኔና ዳንኤል ሺበሺ ባለቤት አልባ የግፍ እስረኞች ሆነናል።  ታስረንም በምንገኝበት ቦሌ ፖሊስ መምሪያ ‘የእናንተ ጉዳይ ከአቅሜ በላይ ነው፤ እናንተን መክሰስም ይሁን መፍታት አልችልም’ በማለቱ  ወደ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ እንደምንሔድ ዛሬ ጠዋት ተነገረን። በተባልነውም መሠረት በጠዋት እቃችንን ሸክፈን (ይዘን) ወደ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ሔድን - ከመርማሪዎቻችን ጋር። 

ማዕከላዊ እኛን አልቀበልም አለ። ወዲያውም ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን (3ተኛ) ተላክን። ይህም ኮሚሽን "አልቀበልም፤ አልችልም" የሚል ምላሽ ሰጠ።

በመጨረሻም ልደታ ፍርድ ቤት የሚገኘው የዐቃቤ ሕግ ቢሮ ጉዳያችንን እንዲያየው መዝገባችንን የያዙት መርማሪ ፖሊሶች ማስረጃ የሚሏቸውን ሰነዶች (ስልኮቻችንን ጭምር) ሰጥተው ተመልሰን ወደ ቦሌ ፖሊስ መምሪያ መጣን።

“አምስት ወራት በግፍ መታሠራችን ሳያንስ፣ ለተጠራጠርንበት ጉዳይ እስካሁን መፍትሔ የሚሰጠን አካል በመጥፋቱ በሀገራችንም በጣም አዝነናል። ግን ለተሻለች ሀገር ግንባታ ዛሬም ሆነ ነገ ጠንክሬ እንደምታገል ልቤ በፅኑ ያምናል። 

“ኃይልን በሚሰጠኝ በፈጣሪ ሁሉን እችላለሁ።" ~ ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ፡፡ ምንጭ በፍቃዱ ሀይሉ ከ ዞን 9




Tuesday, 11 April 2017

The Ethiopian Human Rights Commission says prison guards had opened fire at prisoners who were running away from the fire that gutted down a building at the Qilinto prison in August last year.
The Commissioner, Adisu Gebregziabher, told the Law and Justice Committee of the House of Peoples Representatives that prison administrators and security guards who shot at prisoners running away from the arson should be brought to justice.
The government has denied that prison guards fired shots at prisoners running away from fire, but instead says the guards fired at those who were trying to escape from prison.
The government says 23 inmates died in the arson but independent rights groups confirmed the death of at least 67 prisoners and examination of the bodies indicate that 45 of the prisoners died from gunshot wounds.
It is the first time that a government body admitted guards at the Qilinto prison fired at inmates but the commissioner stops short of saying the shootings were the cause of the death of inmates.
Political analysts say the report by the Commissioner was a whitewash and attempt to dodge responsibility for the death of prisoners and blame few guards for a heinous crime that  the regime could be held responsible.
Ethiopian regime prosecutors instead charged jailed political prisoners for the arson at the notorious Qilinto prison. The charge alleges that 38 prisoners were responsible for the death of 23 inmates in the fire.
The human rights commission is widely criticized for overlooking human rights abuses and justifying for gross rights violations perpetrated by the regime. Dr. Gebregziabher was previously head of the electoral commission accused of conducting stage-managed and undemocratic elections that ensured total domination for the ruling TPLF-led party.
https://ethsat.com/2017/04/ethiopia-govt-commission-says-qilinto-prison-guards-shot-inmates-escaping-fire/ 

በወላይታ ዞን አረካ የሚገኝ አንድ የገበያ ቦታ መቃጠሉ ተነገረ


ኢሳት (ሚያዚያ 3 ፥ 2009)
በጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ የትውልድ ቦታ አረካ የሚገኝ አንድ የገበያ ቦታ መቃጠሉ ተነገረ።
የቃጠሎው ምክንያት በውል ባይታወቅም በህዝቡ ውስጥ ከንግድና ከአስተዳደር በደል የመነጨ ሊሆን እንደሚችል የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ።
ነዋሪዎቹ እንደሚሉት የገበያ ቦታው እና በዚያው የነበሩ ሱቆች በደህዴን ካድሬዎች እና በአቶ ሃይለማሪያም ደጋፊዎች የተያዙ ነበሩ። በዚሁ ሳቢያ ወጣቶች የስራ ዕድል ባላገኙበት ሁኔታ ጥቂቶች ተጠቃሚ መሆናቸው በህዝቡ ውስጥ ከፍተኛ ምሬት መፍጠሩን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። በቃጠሎው ስለደረሰው የጉዳት መጠን የታወቀ ነገር የለም።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ለምርጫ በተወዳደሩበት አረካ መቶ በመቶ አሸናፊ ሆነዋል በተባለበት ጊዜ አንድም ሰው ለተፎካካሪያቸው ድምፅ አልሰጠም መባሉ ይታወሳል።

በዚህ ውጤት ተፎካክረው እና ቤተሰቦቹ ወይም ደጋፊዎቹ ምንም ድምፅ አልሰጡትም የሚለው የምርጫ ቦርድ ሪፖርት በህዝቡ ዘንድ መሳለቂያ እንደነበር አይዘነጋም።
በወላይታ አረካ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ህዝቡን ወክለው ከተመረጡና ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆኑ በኋላ መራጮች ዞር ብለው አይተዋቸው እንደማያውቁ ታዛቢዎች ይናገራሉ።

Thursday, 6 April 2017

Ethiopia: New trial for bloggers accused of encrypting messages flies in the face of justice

 April 6, 2017

Amnesty International UK
Press releases
The Ethiopian Supreme Court’s ruling today that two bloggers who were facing terrorism charges under the draconian Anti-Terrorism Proclamation (ATP) should face a new trial for offences against the Constitution, including encrypting messages, flies in the face of justice, said Amnesty International today.Ethiopia's Zone9 bloggers says "thank you"
The court ruled that, although the prosecution did not provide sufficient evidence to support terrorism charges against Nathnael Feleke and Atnaf Birhane (members of the Zone 9 Bloggers Collective), it had presented enough to support charges of “provocation and preparation to commit or support outrages against the Constitution or the Constitutional Order.”
Muthoni Wanyeki, Amnesty International’s Director for East Africa, the Horn and the Great Lakes, said:
“Learning how to encrypt messages is not a crime, but a freedom protected under the right to privacy and freedom of expression.
“The court’s reasoning that the bloggers confession as to having taken training on ‘security-in-a-box,’ as well as on campaigning, monitoring demonstrations and leadership, demonstrates their malicious intention against the government is not only ridiculous, but also inconsistent with their human rights as guaranteed under the Ethiopian Constitution, as well as regional and international standards.”
Security-in-a-Box is a guide to digital security widely used by activists and human rights defenders.
Amnesty International calls on the Ethiopian authorities to immediately drop the charges against Nathnael Feleke and Atnaf Birhane.
http://ecadforum.com/2017/04/06/ethiopia-new-trial-for-bloggers-accused-of-encrypting-messages/ 

Wednesday, 5 April 2017

‹‹የዐማራ ገበሬዎች ተጋድሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መራዘም ምክንያት ሆኗል›› IRIN

ብራና ሬዲዮ - Branna Radio፤ መቀመጫውን በስዊዘርላንድ ያደረገው የተባበሩት መንግሥታት የተቀናጀ የዜና አውታር (IRIN) በዐማራ ገበሬዎች ተጋድሎ ላይ ሰፋ ያለ ትንታኔ ይዞ ወጥቷል፡፡ የዜና አውታሩ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው የዐማራ ገበሬዎች ተጋድሎ ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አራት ወራት መራዘም ብቸኛ ምክንያት መሆኑን በዝርዝር ያስረዳል፡፡ መጋቢት 3 ቀን 2009 ዓ.ም የታተመው የኢሪን ዘገባ በጎንደርና በባሕር ዳር አስጎብኝ ግለሰቦችን፣ የሃይማኖት አባቶችን፣ የመንግሥት ኃላፊዎችንና የተለያዩ ዜጎችን እንዲሁም በአሜሪካ የተለያዩ ዪንቨርሲቲዎች ተመራማሪዎችንና የኢትዮጵያን ተወላጆች በማነጋገር የሰበሰበው መረጃ እንደሚያመለክተው ገዥው ቡድን በከተማ ያለውን አመጽ የተቆጣጠረው ቢሆንም በገጠር ያለው የዐማራ ታጣቂዎች የእግር እሳት ሆነውበታል ብሏል፡፡ 
የወልቃይት የዐማራ የማንነት ጥያቄ እስካልተመለሰ ድረስ የዐማራ ተጋድሎ ተዋናኝ ገበሬዎች መቼም ቢሆን ትግላቸውን እንደማያቆሙ በየቦታው ያነጋገራቸው ዜጎች በአጽንኦት አስረድተዋል፡፡ ከ20 ሺህ በላይ ወጣቶች ታስረው የስቃይ ሰለባ ቢሆኑም እንዲሁም በብዙ ቦታዎች ያለው አመጽ የቆመ ቢመስልም በሰሜን የዐማራ ገበሬዎች መራር የትጥቅ ትግል ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ እየሄደ ነው ይላል የኢሪን ዘገባ፡፡ 
በነሐሴ 1 ቀን 2008 ዓ.ም ባሕር ዳር በግፍ ወደ ትግራይ የተወሰደውን የወልቃይትን ሕዝብና መሬት ለማስመለስ ጩኸቱን ያሰማውን የዐማራ ሕዝብ የአገዛዙ ወታደሮች በጥይት ደብድበው ከ52 በላይ ሰዎችን ገደሉ፤ የዐማራ ተጋድሎ በተቀጣጠለባቸው ሳምንታት ብቻ ከ227 በላይ ዜጎች በጥይት ተገደሉ፤ ይህን ተከትሎም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ ይላል የዜና አውታሩ ዝርዝር ምልከታ፡፡ 
ይኼው የዜና አውታር በጎንደር ያሉ የሃይማኖት አባቶችንና ግለሰቦችን አናግሮ ‹‹በጎንደር ስለ አርበኛው ጎቤ መልኬና የወልቃይት የዐማራ ማንነት ጥያቄ አስተባባሪው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ በፍቅርና በኩራት የማያወራ የለም፤ ገበሬዎች ለማንነታቸው ሕይወታቸውን ከመስጠት ወደ ኋላ አይሉም፤ ዐማራነት ካልተከበረ ወደ ኋላ የሚል የለም›› እንዳሉት በዳሰሳው አስፍሯል፡፡

ሙሉቀን ተስፋው
(ሙሉ የዜና አውታሩን ዘገባ ለመመልከት ከዚህ ቀጥሎ ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑት
http://www.irinnews.org/analysis/2017/04/03/ethiopia-extends-emergency-old-antagonisms-fester

Tuesday, 4 April 2017

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በብድር ስም እየተራቆተ መሆኑ ተገለጸ

ኢሳት (መጋቢት 26 ፥ 2009)

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደ ሃገሪቱ ልማት ባንክ በብድር ስም እየተራቆተ መሆኑን ምንጮች ገለጹ። ለባንኩ ፕሬዚደንት በጉቦ መልክ እጅግ ዘመናዊ ቤት የተሰራላቸው ቢሆንም፣ እርሳቸው የሚኖሩበት ግን ባንኩ በዋስትና በወረሰው ቤት ውስጥ መሆኑንም መረዳት ተችሏል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የህወሃት ንብረት ለሆነው ኤፈርት ኩባንያዎች ብድር ምንጭነት በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት፣ ከገዢው ፓርቲ ጋር ቅርበት ያላቸው ባለሃብቶችም ከህግና ደንብ ውጭ ከፍተኛ ገንዘብ እየወሰዱ ሲሆን፣ የአንዳንዶቹ ብድር ከ2 ቢሊዮን ብር መብለጡንም ለኢሳት በዝርዝር የደረሰው መረጃ ያስረዳል።

በዚሁ ረገድ በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱት አንዱ የተክለብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን ባለቤት አቶ ተክለብርሃን አምባዬ መሆናቸውም ተመልክቷል። ባለሃብቱ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወሰዱትና ያልተመለሰው ብድር 1.5 ቢሊዮን ብር የደረሰ ቢሆንም፣ ዕዳቸውን ሳይከፍሉ ያለጨረታ ግዙፍ የባንኩን ፕሮጄክቶች እየወሰዱ ይገኛል።

መገናኛ አደባባይ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ህንጻ ያለጨረታ መስራታቸውን የሚገልፁት የባንኩ ምንጮች፣ ባንኩ ልደታ አካባቢ የሚያሰራውንም ህንጻ በተለየ ሁኔታ ያለጨረታ እንዲወስዱ መደረጉም ተመልክቷል። ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት ተገልሎ ግንባታው ለተክለብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽ የተሰጠበት ሁኔታ በግልፅ አልተመለከተም።

የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ህወሃት አመራሮች እንዲሁም ቀደምት ታጋዮችና የጦር አዛጆች በይበልጥም ከአቶ አባይ ጸሃዬና ከብ/ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ጋር በቅርበትና በሽርክና ይሰራሉ የሚባሉት አቶ ተክለብርሃን አምባዬ፣ በአቶ አባይ ጸሃዬ ትዕዛዝ ይንቀሳቀሳሉ ለሚባሉት የባንኩ ፕሬዚደንት አቶ በቃሉ ዘለቀ ዘመናዊ መኖሪያ ቤት ገንብተው በስጦታ መስጠታቸውን መረዳት ተችሏል።

አቶ በቃሉ ዘለቀ በስጦታ የተበረከተላቸው ቤት በዋስትና አስይዘው ራሳቸው ብድር እንደወሰዱ የሚገልጹት ምንጮች፣ አዲሱን ቤት አከራይተው ባንኩ በዋስትና በወረሰው ቤት ውስጥ እንደሚኖሩ ገልጸዋል። ባንኩ በ10 ሚሊዮን ብድር በዋስትና ይዞ የወረሰውን ቤት ባንኩ ሽጦ ገቢ ማድረግ ሲገባው፣ የባንኩ ፕሬዚደንት እንዲኖሩበት መደረጉ ጥያቄ ማስነሳቱን መረዳት ተችሏል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቦርድ ሊቀመንበርነትን በአሁኑ ወቅት የያዙት አቶ በረከት ስምዖን ቢሆኑም፣ በእያንዳንዱ የባንኩ እንቅስቃሴ የባንኩን ፕሬዚደንት አቶ በቃሉ ዘለቀን እየተቆጣጠሩ የፈቀዱትን የሚያስፈጽሙት የባንኩ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ አባይ ጸሃዬ መሆናቸውንም የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።

አቶ አባይ ጸሃዬ አሁን የቦርድ ሊቀመንበርነቱን ቢለቁም፣ የቦርድ አባል መሆናቸው ታውቋል።