Monday, 19 October 2015

ማማረር በቃ! መሰደድ በቃ! መቆዘም በቃ

ማማረር በቃ! መሰደድ በቃ! መቆዘም በቃ! ሀገራችን ኢትዮጵያ ከመቸውም ጊዜ በከፍተኛ ችግር ላይ መሆኗ ግልጽ ነው፡፡ ይህንን ስቃዩዋን እንድንታደጋት ዘወትር የጣእር ድምጿ፡- ‹‹….ልጆቼ ድረሱልኝ፤ አድኑኝ፤….ቦጫጨቁኝ፤ ከፋፈሉኝ፤ ገደሉኝ፤…..›› እያለች በማቃሰት ላይ ትገኛለች፡፡ የሰይጣን ውልዶች ሰይጣኖች እርሷንና ልጆቿን የተፈጥሮ ሀብቷን ደብዛ እያሳጡ ናቸው፡፡ ከአብራኳ የወጡት ጥቁር ፋሽስቶች ለማንነቷ ቁብ ሳይሰጡ እየረገጧት፤ እየመዘበሯት፤ እያስመዘበሯት፤ እየተቧጨቋት፤ እየከፋፈሏት፤….ድምጿ እንዳይሰማ ‹ሱቅ በይ› እያሉ እያደሟት ይገኛሉ፡፡ ይህንንም ለመታደግ እውነተኛና ቆራጥ ልጆቿ የጊዜ፤ የገንዘብ፣ የእውቀት፣ የአካል፣ የሕይወት፣….ወዘተ መስዋእት በመክፈል ላይ ናቸው፡፡ ይሁንና ኢትዮጵያ እናት ሀገራችን ሆና እያለች በ‹መታደግ› ሽፋን እንደሴተኛ ቅሬ ሊዳሯት የሚራኮቱ ደነዝ ባለጌዎች በኢትዮጵያችን ላይ ከማላገጣቸውም በላይ የልጆቿን እንቁ መስዋእትነት የሚያራክሱ፤ የሚያመክኑ፤…..የዘመናችን አሙካዎች ከምንም በላይ ልንፋለማቸው ግድ ነው፡፡ አወን እናት ሀገራችንን ከጭንቋ የሚታደጋት ንጥር ዜጋ እንጂ በግግር አስተሳሰቡ ሊገዛት፤ ሊነዳት፤ ሊዘርፋት፤ ሊቦጫጭቃት፤ ….የሚሻ የስልጣን አለሌ ጨርሶ እድል ልንሰጠው፤ በቸልታ ልናልፈው፤ ልንታገሰው፤ …ወዘተ. አይገባም፡፡ ከውጥኑ የዘር ፖለቲካ ያነገበ፤ በውስጥ አሸምቆ የጎጠኝነት ጭነት የተጫነ፤ የስልጣንና የጥቅም አስተሳሰብ አንግቦ የሚነሳን ማንኛውም ነገር ቁም! ረፍ! ወይድ!....ሊባል ግድ ነው፡፡ እምዬ ኢትዮጵያን በዘር፣ በጎሳ፣ በጎጥ፣ በብሔር፣ በሀብት፣ በእውቀት(በምእራባውያን)፣ በድንቁርና፣…በልዩ ልዩ የሀሳብ ክፍፍል እየፈረጁ የጭንቋን ጣእር የሚያራዝሙ፣ በዜጎች መስዋእትነት ለመሰልጠን የሚቋምጡ አሰሮችና ደነዞች ‹ዘረኝነትን እንታገላለን › እያሉ ጎጠኝነትን የሚያቀነቅኑ - ቅንጅትን፣ መኢአድን ባፍ ጢሙ የደፉትና በርካቶችን በሞትና በእስር እያስረመረሙ( ዘመነ ምኅረት፣ መለሰ መንገሻ፣ …ወዘተ.በቂልንጦ፤ አብርሐም ጌጡ(ላለፉት ሁለት ወራት በማዕከላዊ እስር ቤት ብቻውን በጨለማ ክፍል እየማቀቀ፣ ‘አርበኞች ግንቦት- 7 የምታደራጅ’ እየተባለ በከፋ ድብደባ እየተሰቃየ ያለና ከማንም እንዳይገናኝ ተከልክሎ በቅርብ ቤተሰቡ እንዲያዩት የተፈቀደ እንዲሁም ፍ/ ቤት የ28 ቀናት ቀነ ቀጠሮ እየተሰጠው የሚጉላላ)፣ ማሩ አሻገር፣..ወዘተ. በማእከላዊ የጨለማ እስር ቤት፣ ሌሎች ለቁጥር የሚታክቱ እስረኞችን ፍዳቸውን እያሳዩ) ከውጭ በሚላክ ፍርፋሪ የሰከሩ የሰሜን ሽዋ ግርድፎች፤ - ‹የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች› በሚል የተቆነፀለውና የወያኔ ስልጣን አራዛሚ የሆነው ፀጉራሙ መለስ(በየነ ጴጥሮስ)፣ - ከ‘ቅንጅት ተወክለናል’ በሚል ከወያኔ የተባረሩ ውልግዶችን በአመራር ያካተተው ‘አንድነት’ ብዙም ሳይጓዝ ሙሉ በሙሉ የወያኔ ገቢ ሆነ፤ - በፕሮፌሰር መራራ የመመራው ኦብኮ/ ኦህኮ በሚዲያ ከማነብነብ በስተቀር ያመጣው ፋይዳ የለም፤……ሌሎችም እንዲሁ፣…… ይሁንና የወያኔን ገመና በማጋለጥ የራሱ አወንታዊ ጎን ቢኖረውም በጭራሽ እንደወያኔ ላለ በዘርና በብሄር ፍጹም ለተዋሀደና ለገገረ ደነዝ ስብስብ በምንም የሚበጅም የሚፈይድም አይደለም፡፡ ሀገሪቱንስ ለወራሪ ሰጥቶ መቆዘምና መሰደድ ምን ሚሉት ጅልነት ነው??? ምክንያቱም ወያኔ ከራስ ተፈሪና ከኮ/ል መንግስቱ የከፋ አወዳደቅ በበለጠ እጅግ ተዋርዶ መልቀቅ ያለበት እንጅ እሽሩሩ በማለት በማባበልና በመማፀን የሚገኝ አንዳች ነገር ስለሌለ፡፡ በመሆኑም እነኚህ የዘመናችን ጭራቅ ሰይጣኖች በሚያደርጉት እኩይ ስራ በዝምታ፣ በቸልታ፣ በርቀት፣ በፍርሀት፣ ወይም በማበር፣ ወይም በልዩ ልዩ መንገድ በሚደርሰው ግፍና በደል ባይተዋር መሆን በምንም መልኩ፡- በትውልድ፣ በሕግ፣ ‘በኅሊና’፣ በጊዜ፣ በታሪክ፣…..ከመጠየቅ አይዳንም፡፡ ስለዚህ ሁሉም ዜጋ ኢትዮጵያዊ በሚችለው አቅም፣ የትም ቦታ፣ በአለው ችሎታና መሣርያ በተናጠል፣ በጋራ፣ በኅብረት፣ በአንድነት፣…ቆርጦ በመነሳት ወያኔንና ጀሌውን እንዲሁም የውጭ ተባባሪውን እገባ ግቢቱ ገብቶ ማጥፋት ልብ በሉ ማጥፋት አለብን!! ከመሰቃየት፣ ከመበላት ካልዳን ለምንድን ነው ራሳችን ቀድመን እማንበላው? ‘ጅብ ከሚበላህ በልተኸው ተቀደስ!’ አይደል የአበው ብሒል? ይህ ሲሆን ነው ሀገርን የምንታደግ፤ ይሕ ሲሆን ነው ሕዝብን የምንታደግ!! ይሕ ሲሆን ነው የዜግነታችንን ድርሻ የምንወጣ! ይሕ ሲሆን ነው የራሳችንን ችግር ምንከላው!! ሀገራችንን እናድን! እራሳችንን እናድን! ትውልድን እናድን! ሁሉም ለራሱ፤ በራሱ፤ በጋራ፤ በአንድነት፤…የአርበኝነትን ወኔ፣ መሣሪያ፣… ታጥቀን እንነሳ!!! ሀገር የሚናድን ከሀገር አዳኝ ጋር በኅብረት እንሰለፍ! ማማረር በቃ! መሰደድ በቃ! መቆዘም በቃ! ርትእ- ንጽሮት! አዲስ አበባ- ኢትዮጵያ

No comments:

Post a Comment