Sunday, 11 May 2014


የወያኔን መንግስት በመቃወም በኖርዌ ኦስሎ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተደረገ
በኖርዌ ኦስሎ ሜይ 8 ቀን 2014 (ሚያዚያ 30 ቀን 2006 ዓ.ም ) የወያኔ መንግስት በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ:ያደረሰውን ግድያ በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ተደረገ ::
በኦሮሚያ ክልል በከፍተኛ የትምህርት ተቋማትበሚማሩ የኦሮሞ ተማሪዎች ላይ የወያኔ መንግስት ሀይሎች በወሰዱት እርምጃ ቁጥሩ በውል ያልታወቀ የሰው ህይወት መቀጠፉና ብዙዎችም ለአካል ጉዳት መዳረጋቸው ይታወቃል::
ይህንንም ተከትሎ በኖርዌ ኦስሎ ከተማ በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አዘጋጅነት ታላቅ የሰላማዊ ሰልፍ የተደረገ ሲሆን በሰላማዊ ሰልፉ ላይ በመቶዎቹ የሚቆጠሩ በኦስሎና በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች የድጋፍ ድርጅቱ ባደረገላቸው ጥሪ መሰረት ሰልፉ በተጀመረበት ቦታ በመገኛት በግፍ ለሞቱት የኦሮሞ ተማሪዎች የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት ካደረጉ በኋላ ዘረኛውና አንባገነኑ የወያኔ መንግስት በኦሮሞ ወጣት ተማሪዎች ላይ ያደረሰውን የአካል ጉዳትና ግድያ በመቃወም ድምጻቸውን አሰምታዋል ::

No comments:

Post a Comment