Friday, 25 April 2014

 አፈናው ተጧጥፎ ቀጥሏል

 ፖሊስ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትን ማሰሩን ቀጥሏል
Semayawi party members on action
ፖሊስ ቀስቃሾቹን እያሰረ ነው ፖሊስ የእውቅናው ደብዳቤ አልደረሰኝም በሚል በተለያዩ የአዲስ አበባ ክፍሎች ቅስቀሳ ላይ የተሰማሩትን የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች እያሰረ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት በየካ፣ ካሳንቺስና አቧሬ ሲቀሰቅሱ የነበሩ ወጣቶች በፖሊስ ተይዘው ታስረዋል፡፡ ቀስቃሾቹ ሰልፉ እውቅና እንደተሰጠው የሚያመለክተውን ወረቀት ለፖሊስ ቢያሳዩም ፖሊሶች የእውቅናው ደብዳቡ አልደረሰንም በሚል አስረዋቸዋል፡፡ ቀስቃሾቹ የያዙት የእውቅና ደብዳቤ ግልባጭ ለፖሊስ የተጻፈበት በመሆኑ ሰልፉ እውቅና አግኝቶ እያለ ሆን ተብሎ ለማደናቀፍ እንደሆነ ምክትር ሊቀመንበሩ አቶ ስለሽ ፈይሳ ገልፀዋል፡፡
በላም በረት፣ ቦሌ ድልድይ፣ ኮተቤ፣ መገናኛ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ቅስቀሳቸውን በተሳካ መልኩ አጠናቀዋል፡፡ በሌሎች አካባቢዎች የተሰማሩት አባላት ቅስቀሳውን አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡ በሌላ በኩል በየካ፣ ካሳንቺስና አቧሬን ጨምሮ በሌሎች የከተማይቱ ክፍሎች ፖሊስ ከ20 በላይ አባላትን ማሰሩ ታውቋል፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ ፖሊስ ቅስቀሳው ላይ ያልነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችንም እያሰረ ነው፡፡ የታሰሩትን አባላትና ደጋፊዎች ሁኔታ ለማጣራት ወደ የካ ፖሊስ ጣቢያ ያቀኑ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላትን ፖሊስ አስሯቸዋል፡፡
በዛሬው ቀን ካሳንቺስ ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ የታሰሩት
1. ብሌን መስፍን
2. አስናቀ በቀለ
3. መስፍን
4. ተስፋዬ አሻግሬ
5. እዮብ ማሞ
6. ኩራባቸው
7. ተዋቸው ዳምጤ
የካ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች
1. ፍቅረ ማሪያም አስማማው
2. እያስፔድ ተስፋዬ
3. ጋሻው መርሻ
4. ተስፋዬ መርኔ
5. ሀብታሜ ደመቀ
6. ዘሪሁን ተስፋዬ
7. ጌታነህ ባልቻ
8. ንግስት ወንዲፍራው
9. ሜሪን አለማየሁ ናቸው
የካ አካባቢ ታስረው የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ምግብ እንዳይገባላቸው ተከልክለዋል፡፡ በሌላ በኩል አህመድ መሃመድ፣ሀይለማሪያም፣ ሱራፌልና አምሃ የተባሉ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት መገናኛ አካባቢ ተይዘው ወደ የካ ፖሊስ ጣቢያ ተዘዋውረዋል፡፡ በአጠቃላይ የካ ፖሊስ ጣቢያ የሚገኙት 14 መሆናቸው ታውቋል፡፡ በሁሉም ፖሊስ ጣቢያዎች የሚገኙት አመራሮችና አባላት በአሁኑ ወቅት ቃል እየሰጡ ሲሆን ሊያድሩ እንደሚችሉም ተነግሯቸዋል፡፡
በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ቢሮ ተደውሎ የሰላማዊ ሰልፉን አስተባባሪዎች ጧት ሁለት ሰዓት ላይ ‹‹ኑ እና እንነጋገር!›› የሚል ጥሪ አድርጓል፡፡ ከሰልፉ አስተባባሪዎች መካከል አቶ ጌታነህ ባልቻ ታስሮ ይገኛል፡፡

No comments:

Post a Comment