Tuesday, 24 May 2016

የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር ዶ/ር ታደሰ ብሩ ከአሜሪካን ሀገር የተለያዩ ሴነተሮችና ባለስልጣናት ጋር በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረጉ።

የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር ዶ/ር ታደሰ ብሩ ከአሜሪካን ሀገር የተለያዩ ሴነተሮችና ባለስልጣናት ጋር በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረጉ።
ዶ/ር ታደሰ ብሩ ለአጭር ጊዜ ጉብኝት አሜሪካን ሀገር የሚገኙ ሲሆን፤ በቆይታቸው ወቅት በኢትዮጵያ የሰባዊ መብት፣ ዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር ዙሪያዎች ከአሜሪካን ኮንግረስማን ተወካዮች ጋር ውይይት አድርገዋል። በተለይም ከከሎራዶው ኮንግረስማን ማይክ ኮፍማን ጋር በወቅታዊ እና ዘላቂ መፍትሄዎች ላይ አመርቂ ውይይት ማድረጋቸው ተገልጾል።

ኮንግረስማን ኮፍማን ዶ/ር ታደሰን ስለ ኤርትራ ቆይታቸው ምን እንደሚመስል ጠይቀዋቸው፡- ዶ/ር ታደሰም ሲመልሱ፡- በህወሃት መንግስት የሚደረገው ህዝብን የማጣላት፣ በኢትዮጵያና ኤርትራ ህዝበ መካከል በጠላትነት እንዲተያዩ የሚያደርገው ዘመቻ የተሳሳተ መሆኑን ገልጸው አርበኞች ግንቦት 7 ዘላቂ ወዳጅነትን እየጠናከረ እንደሚገኝ እና የሁለቱ ህዝብ ጠላት TPLF እንጂ ሌላ መሰረታዊ ችግርች እንደሌሉ እና ለኤርትራ ህዝብ ያላቸውን አድንቆት በመግለጽ አብሮ መስራት እንደሚቻል ያላቸውን እምነት ገልጸውላቸዋል። አሜሪካ በኢትዮጵያ የምትከተለውን የውጪ ፖሊሲዋን እንደገና እንድትመረምረውም አሳስበዋል።  አያይዘውም ኮንግረስማን ማይክ ኮፍማንና ሌሎች ሴነተሮች በቅርቡ በሜሪላንዱ ሴነተር ካርደን ቤንጃሚን ተረቆ የቀረበውን Resolution 432 በርካታ ሴነተሮች የፈረሙበትን የኢትዮጵያ ሰበአዊ መብትና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ድጋፋቸውን ይሰጡ ዘንድ ኮንገርሰማኑን ጠይቀዋል።

በመጨረሻም ኮንግረስማን ማይክ ድርጅቱ በሁለቱ ሀገራት ህዝብ መካከል እየፈጠረ ያለውን የሰላም ድልድይ እና የማቀረረብ ሂደት አድንቀው፤ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ጉዳዮችም እንደሚከታተሉ ገልጸውላቸዋል።
Abbay media

ሰበር ዜና.. ጌታቸዉ አሰፋ ስብሰባ አቋር ጦ ወጣ

ሰበር ዜና..
ጌታቸዉ አሰፋ ስብሰባ አቋር ጦ ወጣ..
በትናንትናዉ እለት የወያኔ ተላላኪ ከሆኑት እና ከብሔራዊ መረጃ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ካላቸዉ ግለሰቦች መካከል አምባሳደር ቀጸላ ከብሀራዊ መረጃዉ ሐላፊ ከጌታቸዉ አሰፋ ጋር አርበኞች ግንቦት 7 በአርባ ምንጭ ላይ የወሰደዉን እርምጃ ተንተርሶ ዉይይት በሚያደርጉበት ወቅት በተመሳሳዩ በደቡብ ኢትዮጵያ ኮንሶ አካባቢ በትግራይ ነጻ አዉጪ ቡድን መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት ተፈስሞ ከ 55 በላይ የሚጠጉ የፖለቲካ እስረኞች ማምለጣቸዉ 19 የወያኔ ታጣቂዎች መገደላቸዉና ቁስለኛ መሆናቸዉን የሚያበስር ዜና በስብሰባዉ ላይ የደረሰዉ ጌታቸዉ አሰፋ በአፋጣኝ ስብሰባዉን አቋርጦ መዉጣቱን ታማኝ ምንጮች ገልጸዋል።
አርበኞች ግንቦት 7 በፓርላማ ዉስጥ ሳይቀር መነጋገሪያ እርእስ መሆኑን የገለጹት ምንጮቻችን አክለዉ የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ የፈጠረዉ ፖለቲካዊና ህዝባዊ ጫና እንዳለ ሆኖ በጎንደር አርማጭሆ ሁመራ እና በትግራይ ጎንደር አዋሳኝ በኡማህጅር አካባቢ ድንገተኛና አደገኛ ጥቃቶች መሰንዘራቸዉን እንዲሁም በ24 እና በ25ኛ ክፍለጦር ተዉጣጪ የጸረ ሽብር ሐይል ላይ በተደረገ ሽምቅ ዉጊያ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን መረጃዎች ጠቁመዋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
(ጉድሽ ወያኔ)

Saturday, 14 May 2016

በኢትዮጵያ ጥቃት ያደረስኩት እኔ ነኝ ሲል አርበኞች ግንቦት ሰባት ኃላፊነቱን ወስዷል

ሰሞኑን በደቡብ ኢትዮጵያ ጥቃት ያደረስኩት እኔ ነኝ ሲል አርበኞች ግንቦት ሰባት ኃላፊነቱን ወስዷል። የድርጅቱሊቀ መንበር ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ዛሬ ከዝግጅት ክፍላችን ጋር ባደረጉት አጭር ቆይታ፥  "ትግላችንን የምናካሂደው እዚያው ኢትዮጵያ ውስጥ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ሆነን ነው" ብለዋል። የኤርትራ መንግሥት አሰልጥኖ የላካቸውን አሸባሪዎች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና የፌዴራል ፖሊስ ፀረ-ሽብር የጋራ ግብረ ኃይል ማስታወቁ ይታወቃል።

Monday, 2 May 2016

በቂሊንጦ እስር ቤት የሚገኘው ወጣት አባይ ዘውዱ ሕይወቱ አዳጋ ላይ መድረሱ ታወቀ፡፡

ከሰሜን ጎንደር ታፍኖ በቂሊንጦ የስቃይ ማጎሪያ የሚገኘው የቀድሞ ኣንድነት ፓርቲ ኣመራር ወጣት ኣባይ ዘውዱ በእስር ቤት ሕይወቱ ሊያልፍ እንደሚችል በከፍተኛ ሰጋት ላይ ወድቋል፡፡ ኣባይ ዘውዱ በደረሰበት የጉበት እና ጣፊያ እብጠት ሊፈነዳ ሲሆን በተጨማሪም በቲቪ-በከፍተኛ ደረጃ መታመሙ በደረሰን ጥቆማ ዛሬ 22/08 ቂሊንጦ በመሄድ ከራሱ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ወጣት ኣባይ ዘውዱ በህመሙ ሰውነቱ ኣልቆ በሰው ተደግፎ እያቃሰተ ማየት ያማል፡፡  የተሟላ ህክምና እንደተከለከለ ኣባይ እንባውን እያፈሰሰ ይናገራል፡፡ ይህ ለመላው ኣገር ወዳድ በተለይ የኣማራ ሕዝብ በዝምታ ተመልክቶ የወጣት ኣባይ ዘውዱ ሕይወት ልናጣው ከቻልን ለኣማራ ሕዝብ ትልቅ ውድቀት ትልቅ ዋጋ እንደሚያስከፍል መገንዘብ ያሻል፡፡ ኣባይ ዘውዱ-ሁለተኛ ድግሪውን ከቅርብ ጊዜ በፊት ያጠናቀቀ ሲሆን በከፍተኛ ትምህርት የቆይታውም ቢሆን ከባሕር ዳር ዩንቨርስቲ የማዕረግ ተመራቂ የነበረ ወጣት ምሁር ነው፡፡ ኣባይ ዘውዱ የቀድሞ ኣንድነት ፓርቲ ከተቀላቀለ በኃላ በነበረው ንቁ ተሳትፎ ከሚሰራበት ቦታ ከማባረር እንስቶ በኣካሉ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሲደርስበት የቆየ ጠንካራ ጓዳችን መሆኑ ይታወቃል፡፡ በተለይ ለሱዳን ሊሰጥ በታሰበው መሬት ዙሪያ ኣባይ ዘውዱ ከጎንደር ኣዲስ አበባ ድረስ በመምጣት በኣንድነት ፅ/ቤት ሰፊ የዳሰሳ ጥናቱን ካቀረበ ወዲህ በወያኔ አይን እንደገባ ይነገራል፡፡ ለዚህ ጀግና ጓዷችን ኣገር ወዳድ ሊደርስለት ይገባል፡፡ ኣማራ ልጆቹን በዘረኞች እያስበላ የሚኖረው እስከመቼ ነው?
ወጣት አክቲቪስቶች የሚዲያ ኣካሎች በሙሉ ወጣት ኣባይ ዘውዱ የተሻለ ህክምና እንዲሰጠው ግፊት ማድረግ ሕይወቱን መታደግ ግዴታ ኣለበት፡፡ የነቃ ተሳትፎ ያላቸው የኣማራ ተወላጅ የሚደርሰው ዘር የማጥፋት ድርጊት ሊወገዝ ኣምሮ ሊታገሉት የሚገባ ተግባር ነው፡፡ ሁሉም ወገን ወዳድ ለኣባይ ዘዉዱ ድምፁን ያሰማለት፡፡ ኣማራ ነገ ታሪኩ ሲነገር ሊያፍርበት ይችላል፡፡

Saturday, 9 April 2016

17 ዓመት ሙሉ መታኮስ ይኖራል ብላችሁ አትጠብቁ

ብዙ ሰዎች የጥይት ድምፅ ካልሰሙ ፣ ዛሬ በተደረገው ውጊያ ይሄን ያህል ሞተ ይሄን ያህል ቆሰለ የሚል ዜና ካልሰሙ እየተደረገ ያለው ትግል እውነት አይመስላቸውም። ወደዳችሁም ጠላችሁም ወያኔን በቁሙ የማፍረስ ስራ በሚገርም ሁኔታ እየተሰራ ነው። 2008 ከገባ በኋላ እንኳን በሀገሪቷ በአራቱም ማዕዘን አስገራሚ ህዝባዊ ንቅናቄን መፍጠር ተችሏል። ልክ እንደወያኔ 17 ዓመት ሙሉ መታኮስ ይኖራል ብላችሁ አትጠብቁ አሁን እየተሰራ ያለው ስራ ስርዓቱን በቁሙ የመግደል ስራ ነው። ስርዓቱ መሞቱ ከተረጋገጠ በኋላ የቀብሩ እለት ከባድ የተኩስ ልውውጥ ሊኖር ይችላል። ከዛ ባለፈ ረዥም ዓመታት የሚፈጅ የተኩስ ልውውጥና ብዙ ሕይወት የሚቀጠፍበት ነገር አትጠብቁ ምክንያቱም ትግሉ የሚመራው በተማሩ ሰዎች ስለሆነ።

Tuesday, 5 April 2016

መክሸፍ ባሀል በመሆኑ ዛሬ ኢትዮጵያ በሁሉም ነገር ከአብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገሮች በታቺ ነች፣

የዛሬ ትውልድ የቀዳማዊ ሀይለ ስላሴን ዩኒቨርስቲ ታሪክ አያቅም፣በአስራ ዘጠኝ ሀምሳዎቹ በአፍሪካ ውስጥ የሚወዳደረው ዩኒቨርስቲ አልነበረም፣ በምእራብ አፍሪካ ከናይጀርያና ከጋና ፣በምስራቅ አፍሪካ ከኬንያ፣ከታዛንያና ከዩጋዳ ነፃ ትምሀርት እየተሰጣቸው ይማሩ ነበር፣ ሮበርት ኡጎ የሚባለው የቀዳማዊ ሃይለ ስላሲ ምሩቅ የኬንያ የውጭ ጉዳ ምኒስተር ነበር፣ጆርጅ ማጎምቤየሚባለው የታንዛንያ ወጣት በሁዋላ በብዙ ሀገሮች በኢትዮጵያም ጭምር አምባሳደር እየሆነ ሰርቷል፣ የኢትዮጵያ አየር ሀይልም፣ የኢትዮጵያ አየር መገድም ለብዙ የአፍሪካ አገሮች የዘመናዊ እውቀትና ጥበብ ምጮች ነበሩ።መክሸፍ ባሀል በመሆኑ ዛሬ ኢትዮጵያ በሁሉም ነገር ከአብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገሮች በታቺ ነች፣ ቁልቁል መውረድ ባሀል ሲሆንና ሀዝብ እሪ! ሳይል ሳይጮሀና ሳያለቅስ ገደል አፋፍ ላይ የደረሰ ይመስለኛል።
#ከአዳፍኔመፅሀፍገፅ22የተወሰደ።

Saturday, 2 April 2016

የኢትዮጵያ የታሪክ ፈተናዎች እና የሚጋጩ ህልሞች- የኢሕዴግ ቆርጦ ቀጥል ፖለቲካ

የዶ/ር መራራ ጉዲና ምልከታ
በተቃዋሚ ጎራ፣ ብዙ ሳይንቀሳቀስ እያየሁ ያለሁት የኦሮሞና የአማራ ልሂቃን ፖለቲካ ነው። የሁለቱም ልሂቃን ፖለቲካ በዋናነት በሁለቱ ጫፎች ላይ ቆሞ ገመድ ከመጓተት ወደመሃል መጥቶ የጋራ ዴሞክራቲክ አጀንዳ መቅረጽ አላስቻለቸውም። ብዙዎቹ ሂሳብ የማወራረድ ፖለቲካን የዛሬ 30 እና 40 አመታት ብቻ ሳይሆን የዛሬ 130 እና 140 አመታት በፊት የነበረውም ጭምር የታሪክ ሂሳብ እንተሳሰብ የሚሉ ይመስሉኛል። የኦሮሞ ልሂቃን ዋናው ችግራቸው የጋራ የፖለቲካ አጀንዳ ለመቅረጽ ከመጣር ይልቅ ለብቻቸው የሚያደርጉትን ትግል የመንግስተ ሰማያት አስተማማኝ መንገድ አድርገው መምለካቸው ነው።
የአማራው ልሂቃን ዋናው በሽታቸው በዋናነት በአማራው ልሂቃን የተፈጠረችው ኢትዮጵያ በዋናነት እንደዛው ትቀጥል መቀጠለም ትችላለች የሚል ነው።
የሁለቱም ልሂቃን ያለፉት አርባ አመታት ጉዞ ሌኒን እንደሚለው "የሞኝ ሩጫ ፍጥነት አይጨምርም" አይነት ነው። በእኔ እምነት ሁለቱም ከታሰሩበት የታሪክ እስር ቤት ወጥተው በጋራ የዴሞክራቲክ አጀንዳ ላይ ተስማምተው በመሃል መንገድ ላይ ካልተገናኙ የኢትዮጵያ ፖለቲካ በአሁኑ ትውልድ ዘመን ፈቀቅ የሚል አይመስለኝም።
ዶ/ር መራራ ጉዲና
የኢትዮጵያ የታሪክ ፈተናዎች እና የሚጋጩ ህልሞች-የኢሕዴግ ቆርጦ ቀጥል ፖለቲካ