ሕዝብ ለሕዝብ የሚያናክሰው የሕወሓት የመስፋፋት ፖሊሲ ተከዜን የወልቃይት እና ጠገዴን ምድር ከነሕዝቡ ወደ ትግራይ በማካለል በአከባቢው ከፍተኛ የፖለቲካ ቀውስ እንዲነሳ ያደረገ ሲሆን ቀውሱ እየተባባሰ ሕዝቡ መሳሪያውን እንደታጠቀ በዱር ሲገኝ በሽምግልና ለማዘናጋት እና ጊዜ ለመግዛት ሽምግልና አልቀመጥም ሲሉ በግዳጅ በዛቻ የሽምግልናው መሪ የሆኑት አንድ ጳጳስ ጨምሮ የተደረገው ሙከራ እንደተንጠለጠለ ይገኛል::#ሽኸት_ናብ_ትግራይ_ትመለስ የሚለው ዘመቻ የአፋር ክልል ወረዳዎችን በሙሉ ከጥንት ጀምሮ የትግራይ መሬዎች ናቸው የሚል እደምታ ይዞ ተጀምሯል::
እንዲሁም በቅማንት ሕዝብ አከባቢ እየተደረገ ያለው ሕዝብን የማጨፋጨፍ እና የመጨፍጨፍ ስራ በተክል ድንጋይ እንዲፈነዳ የተደረገ ሲሆን የውልቃይት ሕዝብን ጥያቄ ለማድበስበስ እና ለጊዜ መግዣ የሚደረጉ ሕወሓታዊ ተኮሎች ቀጥለዋል::አስተዳደራዊ ጉዳዩን መቀሌ እየመጣ እንዲያስፈጽም እየተደረገ ያለው የቅማንት ሕዝብን ወደ ትግራይ ጠቅልሎ እስከ ጎንደር መግቢያ ድረስ ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት እስካሁን ሊሳካ አልቻልም::ለዚህ ስራ የሚረዱ የሕወሓት ሚሊሻዎች እና የጦር መሳሪያዎች ካለፈው ሳምንት ጀምሮ እየተንጠባጠቡ በአከባቢው ሰፍረዋል::ሕዝቡን ይህንን በማወቁ መሳሪያውን ወልውሎ በተግባር እየተንቀስቀሰ ለሕወሓት ጦር የእግር እሳት ሆኖበታል::
ይህንን የአማራ ክልልን ሰነጣጥቆ የራሱን ግዛት ለማስፋፋት የሚመኘው የሕወሓት አገዛዝ የሱዳን ድንበርን ይዞ ከኩምሩክ ጀምሮ እስከ ሁመራ ድረስ የጉምዝ ተወላጆችን እና የሕወሓት ሚሊሻዎችን በማስፈር አስፈላጊውን እየሰራ ሲገኝ በአፋር ክልል ደግሞ ለመስፋፋት ያለውን እቅድ ለማሳካት #ሽኸት_ናብ_ትግራይ_ትመለስ የሚል አዲስ ዘመቻ በካድሬዎቹ እና በአሽቃባጭ ዘረኛ አማሳኞቹ በኩል ዘመቻ መጀመሩን ታውቋል::ይሕው ዘመቻ ተያይዞ የአፋር ክልል ሕዝብን አሳዶ ግዛቱን በማስፋፋት አከባቢዎቹን ከትግራይ ክልል ጋር ለመቀላቀል ነው::ይህ #ሽኸት የተባለ ቦታ ከጥንት ጀምሮ የትግራይ መሬት ነው ለስራ ጉዳይ አፋር ክልል የገቡ መሬትች ስለሚገኙ ከትግራይ ካልተቀላቀለ በትግሪኛ ትምሕርት ካልተሰጠ አፋርና አከባቢው ላይ መነገር ካልቆመ ለትግራይ ትልቅ ችግር አለ በማለት ሕወሓት እና ካድሬዎቹ እያራገቡ ነው::