Monday, 28 December 2015

የወልቃይት ጉዳይ

የወልቃይት ጉዳይ
ህወሀት ከ10 ዓመት በላይ ሽፍታ እያለ: ለ25 ዓመታት ቤተመንግስት ሆኖ ከፈጸማቸው ወንጀሎች ዋናው በወልቃይት ህዝብ ላይ ታሪክ ይቅር የማይለው የዘር ማጽዳት ወንጀሉ ነው። አንድን ህዝብ እንዳለ ማንነቱንና መሬቱን መዝረፍ ከሃጢያትም በላይ ነው። የግድ ትግሬ ሁኑ: መሬታችሁ በትግራይ ስር መካለል አለበት በሚል በጭካኔ በወሰደው እርምጃ በሺዎች የሚቆጠሩ ወልቃይቶችን ገደለ። አሰረ። ከሀገር እንዲሰደዱ አደረገ። ...ይሄ እስከአሁን የነበረው ነው። ወደፊት በሰፊው ይነሳል።
ሰሞኑን ወልቃይቶች ማንነታችን ይመለስ ብለው የጀመሩት እንቅስቃሴ ህወሀትን አስደንግጦታል። የማንነቱን ጉዳይ ከዳር ለማድረስ የተቋቋመውን ኮሚቴ አባላትን እያዋከበ: እያሰረም ነው። ኮሚቴው ፔትሽን በተለያዩ ከተሞችና መንደሮች ህዝቡን አስፈርሞ ከጨረሰ በኋላ ፊርማው ህወሀት እጅ ወደቀ። ባለፉት 3 ቀናት ህወሀት ሰም ዝርዝር ይዞ ወልቃይቶችን ለሰልፍ እያዘጋጀ ነው። ትግሬ ነን በሉ: በትግራይ ክልል መቆየት እንፈልጋለን ብላችሁ ሰልፍ ውጡ ዓይነት የቤት ለቤት ቅስቀሳና ማስፈራራት እያደረገ ነው። እንግዲህ አሁን ጊዜው ተቀይሯል። የመረጃ ጨለማ በዋጠን ጊዜ የፈጸመውን ወንጀል በዚህ ዘመን ሊፈጸም ከሞከረ የሚከፍለው ዋጋ ከባድ ነው። ለማንኛውም ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተልን ነው። በአከባቢው ያላችሁ ኢትዮጵያውያን ባገኛችሁት መንገድ መረጃውን አድርሱን። ይሄን ኋላ ቀርና ፋሽስት ስርዓት የምንገላገለው አንድም በመረጃ ነው።.

No comments:

Post a Comment