የአዲስ አበባ የኢህአዴግ ጽ/ቤት ድርጅት ጉዳይ ኃላፊዋ ህወሓትን ከዳች
ከምርጫ ዘጠና ሰባት በኋላ በኢሕአዴግ አደረጃጀት ዉስጥ ትልቅ ቦታ የነበራት ናት። ከሴቶች አደረጃጀት ሃልፊ ነበረች። ከዚያም በአዲስ አበባ የኢሕአዴግ ጽ/ቤት የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ ሆና እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ትሰራለች። በአዲስ አበባ ይለ የኢሕአዴግ አባል የማያወቃት የለም።
ከአዲስ አበባ የኢሕአዴግ ጽ/ቤት የድርጅቱ ጉዳይ ሃላፊነቷ በተጨማሪ በአዲስ አበባ የሴቶች መዋቅርም የአድን ክላስተር ሃላፊም ነበረች። አበባ ገብረ ሕይወት ትባላለች።አበባ በቅርቡ ለአንድ ስብሰባ ወደ አሜሪካን አገር ባቀናችበት ወቅት አጋጣሚዉን በመጠቀም፣ የፖለቲካ ጥገኝነት ለመጠየቅ እንደወሰነችና ወደ አገር ቤት የመመለስ ሀሳብ እንደሌላት ለርሷ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ጠቁመዋል፡፡
በተለይም በኢሕአዴግ ዉስጥ ፍጹም የሆነ የሕወሃት የበላይነት ከመኖሩ የተነሳ፣ በሞያቸውና በእውቀታቸው የመወሰንና የማገልገል እድል የሌላቸውና፣ የታዘዙትን ብቻ ማድረግ የሚጠበቅባቸው ሌሎች የኢሕአዴግ አባላት ደስተኛ እንዳልሆኑ በስፍት ይነገራል። ብዙዎች ባላቸው አጋጣሚ ሁሉ ኢሕአዴግን እየከዱ እንደሆነ፣ ያሉት ደግሞ ከዉስጥ መረጃዎች በማቀበል ከአዝዙ ያላቸውን ጥላቻ በማሳየት ላይ መሆናቸው በግልጽ እየታየ ነው።
ከዚህ በፊትም ሚኒስቴር ዴታ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ኤርምያ ለገሰን ጨምሮ ብዙዎች ኢሕአዴግ እንደከዱ ይታወቃል።
No comments:
Post a Comment