Wednesday, 31 December 2014

የኢትዮጵያመከላከያሰራዊት‬ ገመና ሲጋለጥ



1)አስደንጋጩ አሀዝ
ባሰለፍነው 2006ዓ.ም መጨረሻ "የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን አጠቃላይ ይዞታና አቋም በተለይ ደግሞ ከነሐሴ 2003ዓ.ም እስከ ነሐሴ 2006ዓ.ም በሰራዊቱ የተከሰቱ አበይት ሁነቶችን " የግምገማ ውጤትን መሰረት አድርጎ እንደተዘጋጀ የተገለፀን ሪፖርት የማየት አጋጣሚን እንዳገኙ ከገለፁልኝ "የመከላከያ ሰራዊት ምንጮች " በአገኘውት መረጃ መሰረት "በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ስር ከሚገኙ ማለትም ከአራቱ የጦሩ እዞች፣አጋዚ ልዩ ኮማነዶን ጨምሮ ከተለያዩ የጦሩ ዲፓርተመንቶች እና ከሁሉም የጦር ማሰልጠኛ ኮሌጆች ስር ከሚገኙት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ውስጥ 13,895 የሚሆኑት ከነሐሴ 2003ዓ.ም እስከ ነሐሴ 2006ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ጦሩን ትተው ጠፍተዋል"
እነደ መረጃው ከሆነ ከ2003ዓ.ም እስከ 2006ዓ.ም ማለትም ለሶስት ዓመታት በአማካኝ በየቀኑ ከ12-13 የሚሆኑ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ሰራዊቱን ትተው ጠፍተዋል፡፡
(የ"መከላከያ ሰራዊት ምንጮቸ "ያደረሱኝ መረጃዎችን በመመርኮዝ የጠፉትን ወታደሮች ለማግኘት ላለፉት ሶስት ዓመት ሲደረግ የነበረን ብዙም ያልተሳካ አሰሳንና ውጤቱን እንዲሁም ሌሎች ሁነቶችን በቀጣይ አቀርባለው)
ሀና መታሰቢያ ታህሳስ 2007

No comments:

Post a Comment