Tuesday, 14 October 2014

shameless Ethiopian government

ቻችን ስቃይ የኛም ስቃይ ነው ያገባናል ብለው የሳኡዲን መንግስት ለመቃወም የወጡ የተለያዩ የህብረተሰቡ ክፍሎች የድብደባው ሰለባዎች ነበሩ።
ሰልፉ ፍጹም ሰላማዊ ነበር።(ፌደራል ድንገት ደርሶ የዱላ ውርጅብኝ እስኪያወርድብን ድረስ)
ከዚያ በኋላ እንግዲህ የሆነው ሆነ...።
***
ታዲያ ይሄ ዛሬ ለምን ትዝ አለኝ?(ጥሩ ጥያቄ ነው)
ዛሬ...
ኢህአዴግ ሆዬ አኢሴማ (ሴቶች ሊግ) እና አኢወማውን(ወጣት ሊግ) አስከትሎ አሜሪካ ኤንባሲ ፊትለፊት ሰልፍ ማድረጉን ስሰማ ድርቅናው ገረመኝ።(አሜሪካ ያለው ኢንባሲያችን ተደፈረ፣ ሽጉጥ የተኮሰውን አባላችንንስ ለምን ታባርራላችሁ.... ነው ነገር)
ግርምርምርም...
***
የኛ ሃገር ዲሞክራሲ እንግዲህ እንዲህ ናት፣
ለፈለጉት የሚያድሏት፣ ላልፈለጉት የሚነፍጓት!!!
እነሱ ሲያሻቸው መዥረጥ አድርገው የሚከናነቧት፣ ለሌላው ግን እንቁልልጭ የሚሏት!!!
እንዲህ እየተቀለደ ግን የት ድረስ ይኬዳል ጎበዝ?????

No comments:

Post a Comment