Wednesday, 1 October 2014

የአዲስ ጉዳይ፣ ሎሚ ፣ ፋክት መፅሔትና ስራአስኪያጆቻቸው ጥፋተኛ ተባሉ

Magazine
ህዝብን ለአመፅ በማነሳሳት ፤ ሀሰተኛ ወሬዎችን አሳትሞ በማሰራጨትና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በሀይል ለመናድ ሲንቀሳቀሱ ነበሩ በሚል ክስ የቀረበባቸው ሶስት መፅሔቶች እና የድርጅቶች ስራ አስኪያጆች ጥፋተኛ ተባሉ ።
ጥፋተኛ የተባሉት አዲስ ጉዳይ መፅሔት እና የመፅሔቱ ስራ አስኪያጅ አቶ እንዳልካቸው ተስፋዬ፣ ሎሚ መፅሔትና የመፅሔቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ግዛው ታዬ፣ ፋክት መፅሔትና ስራ አስኪያጅዋ ፋጡማ ኑሪያ ናቸው።
ቀደም ሲል የመፅሄቶቹ ስራ አስኪያጆችን ፖሊስ በአድራሻዎቻቸው አፈላልጎ ሊያገኛቸው እንዳልቻለ በመግለፅ፣ ተከሳሾች በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጥሪ ማድረጉንና በዚህም ጥሪ መሰረት ባለመቅረባቸው ባቀረብኩት ማስረጃ መሰረት ብይን ይሰጥልኝ ሲል አቃቤህግ መጠየቁ ይታወሳል።
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 16ኛ ወንጀል ችሎትም ዛሬ የአቃቤህግን ማስረጃዎች በመርመር ነው ሶስቱ መፅሄቶችና ስራ አስኪያጆቻቸው ጥፋተኛ ናቸው ሲል ብይን የሰጠው።
በዚህም መሰረት የጥፋተኝነት ውሳኔ ለማስተላለፍ መስከረም 27፣2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

No comments:

Post a Comment