ንብረትነታቸው የኢትዮጵያ የመንገዶች ባለስልጣን የሆኑና ዋጋቸው ከ65 ሚልዬን ብር በላይ 88 የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ለጥገና ተብለው ወጥተው ከመስሪያ ቤቱ ወደትግራይ ተወስደው እንደወጡ ቀሩ ። መመለሱ ይድከማቸው ፣ ይደብራቸው ወይም መጋዘን ውስጥ ተነው ይጥፉ የታወቀ ነገር የለም ፣ ሁኖም ግን የመንገድ ባለ ሥልጣን የተባለው ማሽኖቹን ከወሰደው አካል መጠየቅ ባይችልም ከኢትዮጵያ ሕዝብ ንብረትነት እንዲሰረዙ የፌዳራል መንግሥት ከሚባለው የጠየቀ መሆኑ ተገልጿል ። እንደተባለው ወይም እንደተለመደው እንደ 10,000ቶን ቡና ለወደፊቱ እንዳይደገም ከተደገመም ለወደፊቱ እጅ እንቆርጣለን ተብሎ ይሆን አይታወቅም ። የኢትዮጵያ የሕዝብ ሀብት እንዲህ እንደዋዛ ያለምን ተቆጭ በተራ ዘራፊ እንዲህ ይወሰዳል ፣ ይች ሀገር የኢትዮጵያዊው ናት ወይስ እንደምናያት የባዕዳኖች ናት ።
ዜጋ የሚዋከብባት ዜጎች ከትውልድ መንደራቸው የሚባረሩባት ባዕዳን እንደፈለጉ የሚሆኑባት በግድ መሬት ውሰዱልን ወይም እንስጣችሁ ሱዳኖች የሚለመኑባት ሀገር
No comments:
Post a Comment