Tuesday, 16 February 2016

የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ተገኔ ጌታነህ ከአገሪቱ ብልሹና ጣልቃገብ አሰራር የፍትህ ስርኣት ራሳቸውን አገለሉ

በሕወሓት የፍትህ ስርኣት ደስተኛ ያልሆኑት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ተገኔ ጌታነህ ስራቸውን በፈቃዳቸው ከስራቸው የለቀቁ መሆኑን ፎርቹን ጋዜጣ ገልጿል::የጠቅላይ ፍ/ቤቱ ፕሬዝዳንቱ ከሳምንት በፊት መልቀቂያ ደብዳቤ ያስገቡ መሆኑ የታወቀ ሲሆን የመልቀቂያቸው ምክንያት ከጤና ጋር የተያያዘ መሆኑን በደብዳቤያቸው አስፍረዋል። ይህ ቢሆንም ፕሬዝዳንቱ በጤንነት ያሳቡ እንጂ በሕወሓት የፍትህ ስርዓት ውስጥ ባለው ብልሹ እና ጣልቃገብ አሰራር ደስተኛ እንዳልነበሩ የሚያውቋቸው ተናግረዋል።በዚህ ሳምንት ሕገመንግስቱ ይከበር ሕወሓት ከዳኝነት ስራ እጁን ያውጣ ያሉ ከዳኝነት ስራቸው መባረራቸው ይታወሳል:: ‪‎


No comments:

Post a Comment