Wednesday, 25 February 2015

ኢትዮጵያ ውስጥ ዳኛ ቢኖር

ኢትዮጵያ ውስጥ ዳኛ ቢኖር – ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም

Prof. Mesfin
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም
የጎረቤት ኬንያ ዳኛ ለኬንያ መንግሥት አስፈጻሚው ክፍል ልኩን ነገረው፤ ሕገ መንግሥቱን በመርፌ አስተኝተህ ሕገ መንግሥቱን የሚጻረር ሕግ ለማውጣት አትችልም፤ ስለዚህም የሰነዘርኸውን የጉልበት ሕግ አንሣ፤ አለው፤ ዳኛ አይጥፋ! ሌላ ቢቀር ከጎረቤት ዳኝነትን እንስማ፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ዳኛ ቢኖር ስንት ጋዜጠኛ፣ ስንት የሃይማኖትና ስንት የፖሊቲካ መሪዎች ከየወህኒ ቤቱ ይወጡ ነበር! ሁላችንም እንደልባችን ሳንፈራ፣ ሳንፈራራ በሙሉ ነጻነት ችግሮቻችንን የወያኔን ጭቆና ጨምሮ ለመወያየትና መፍትሔዎችን ለመለዋወጥ የምንችልበት መድረክ፣ ጋዜጣ፣ መጽሔት፣ ራድዮና ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ ውስጥ ይኖረን ነበር፤ ስንት ሰው ሥራ ያገኝ ነበር፡፡
ከሁሉም በላይ በየመንገዱ ጠመንጃ የያዘ ሊያስፈራራን የሚሞክር ሆድአደር እያየን፣ እንደዚሁም በየጫካው ያሉትን እያሰብን ሰላማችንን ከምናጣ አበባውን ትተን፣ ሩዙን ትተን፣ የተወደደልንን ጤፋችንን እያመረትን አዲስ ኑሮ ብንጀምር የተሻለ ነበር፡፡
ግን አንድ እንቅፋት አለብን፤ እነዚህ ከየኪዮስኩ እውቀት ገዝተን አዋቂዎች ሆነናል የሚሉት እንትኖች እንመጀመሪያ ችግሩ እንዲገባቸው፣ ሁለተኛ መፍትሔው እንዲገባቸው፣ ሦስተኛ ጉልበትና እውቀት አንድ አለመሆናቸውን ብቻ ሳይሆን በጉልበት እውቀት የማይገኝ መሆኑን ማሳመን በረዶ እየወረደ የስሜን ተራራን መውጣት ነው፤ በረዶ ሳይኖር ወጥቼዋለሁ!
እነዚህን የጉልበት አዋቂዎች — ስለሽማጌሌዎችና አሮጊቶች ሳያስቡ፣ ስለመብራት ኃይል ሳያስቡ፣ ስለውሀ ሳያስቡ ሁሉም በጉልበት ፎቅ ይውጣ የሚሉ! ይባስ ብለው ለእስረኛውም ፎቅ እየሠሩለት ውጣ! ሊሉት ነው!
እነዚህ የጉልበት አዋቂዎች የአበሻ ኑሮ፣ ቡናው፣ ሙቀጫው፣ ምጣዱ፣ በርበሬው፣ ቁሌቱ፣ ቄጤማው፣ ዶሮና በግ ማረዱ፣ ኧረ ስንቱ! ሳይገባቸው ቻይና በነገራቸው የሚያውቁትን የሚረሱ ማን ያስተምራቸው! እናውቃለን ስለሚሉ እንዴትስ ይማራለ? በእውነት ለመማር ቢፈልጉስ ስንት ዓመት ሊያስፈልጋቸው ነው! እግዚአብሔር እንሱንም እኛንም በምሕረቱ ይጎብኘን! የሚያስተምር ጎረቤት አያሳጣን!
source: satenaw

ገዢው ፓርቲ እየተፍረከረ ነው - ሽመልስ ከማል ሊከዳቸው ነው ተባለ

የገዢው ፓርቲ ቃለ አቀባይ የነበረዉና ጸያፍ ንግግሮች በመናገር የሚታወቀው ሽመለስ ከማል በህወሃቶች እንደ ሸንኮራ አገዳ ተመጦ እንደተተፋ ምንጮ ይገልጻሉ። ሕወሃቶች ዉስጥ ዉስጡን አገሪቷን እያደሙና እያጎሳቆሉ ላይ ላዩን የነርሱን የሽብር ተግባር በማስተዋወቅና በማብራራት፣ የነርሱም ቃለ አቀባይ በመሆን ለብዙ አመታት ያገለገለው ሽመልስ ከማል፣ ምናልባትም ከሕወሃት አባላት ቀጥሎ በዋናነት የሚጠላ ባለስልጣን እንደነበረ ብዙዎች ይገምታሉ።
የሽመለስ ከማል ወያኔን ከድቶ መሰደዱን የሚገልጹ ዜናዎች እየተሰሙ ቢሆንም፣ ከሽመለስ ከማል በይፋ ገና የተገለጸ ነገር የለም። ሽመለስ ከማል ከመድረኩ ከጠፋ ብዙ ጊዜ የሆኔ ሲሆን፣ ጊዜዉን ጫት በመቃም ያጠፋ እንደነበረም በስፋት ተዘግቧል።
ሽመለስ ከማል የቅንጅት መሪዎች ታስረው በነበረ ጊዜ አቃቤ ሕግ ከሳሽ የነበረ ሲሆን፣ አሁን ሕዝባችንን ለማሸበር ሕወሃት እየተጠቀመበት ያለዉን የጸረ-ሽብርተኝነት ሕግን ካረቀቁት ሰዎች መካከል አንዱ ነበር።
የሽመለስ ከማል አገር ለቆ መሄድ፣ በሕወሃት እና በሌሎች የኢሕአዴግ አባላት ዘንድ ትልቅ መቃቃርና አለመግባባት እንደተፈጠረ በርግጠኝነት የሚያመላከት መሆኑን ዉስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ። በተለይም ከፓርላማው 6% በመቶ፣ በኢሕአዴግ ብሄራዊ ምክር ቤትና ፖሊት ቢሮ 25% ብቻ መቀመጫ ያላቸው ሕወሃቶች፣ አሁን እያታየ ባለ መልኩ፣ ፍጹም አምባገነናዊ በሆነ ሁኔታ፣ ሌሎችን ሳያማክሩ ፣ እርስ በርሳቸው በትግሪኛ ብቻ እየተናጋገሩ የሚወስኑት ዉሳኔ፣ ብዙዎችን እያበሳጨ እንደሆነ ዉስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ። በተለይም በአራት የአገሪቷ ማእዘናት አንጋፋ የሆነውን የአንድነት ፓርቲ ጥቂት የሕወሃት አመራሮች፣ ከፓርላማዉም ሆነ ከሚኒስትሮች ምክር ቤት ዉሳኔ ዉጭ፣ በራሳቸው ቀጭን ትእዛዝ እንዲታገድ ማድረጋቸው ኢሕዴጎች ዉስጥ ትልቅ ዉይይት እየፈጠረ ነው።
እነ ዶር ቴዎድሮስ ያሉ ግለሰቦች፣ እርስ በርስ ያለው አለመስማማት የከረረ በመሆኑ፣ «እንደምንም ብለን ምርጫዉ በስልጣናችን ላይ ችግር እንደማያመጣ ካረጋገጥም በኋላ፣ ከዚህ በፊት ከነበረው የበለጠ የፓርላማ መቀመጫዎች ለታማኝ ተቃዋሚዎች በመልቀቅ ነገሮችን ትንሽ ከፈት እናደርጋለን” በሚል ነገሮችን ለማረገብ የሞከሩ ቢሆን፣ ሁኔታው አሁንም ዉስት ዉስጡን እየበሰለ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
አርአያ ተስፋማሪያም የጦመረዉን እንደሚከተለዉ ያንብቡ
ሽመልስ ከማል አሜሪካ ገባ ። የኰሚኒኬሽን ምክትል ሃላፊ የሆነው ሽመልስ ከማል ባለፈው ሳምንት አሜሪካ መግባቱን ምንጮች አስታወቁ። ከሬድ ዋን ሁሴን ጋር የከረረ ፀብና አለመግባባት ውስጥ የገባው ሽመልስ ለረጅም ሳምንት ከስራ ገበታው ርቆ መቆየቱን ያስታወሱት ምንጮቹ አሜሪካ የመጣው በግሉ እንደሆነ አስታውቀዋል።
በዲሲ ቆይታ ካደረገ በኋላ ኒውዮርክ ወደሚገኘው ወንድሙ ዘንድ ያቀናው ሽመልስ የፖለቲካ ጥገኝነት በመጠየቅ አሜሪካ ለመቅረት ሃሳብ እንዳለውና እንደሚፈልግ ምንጮቹ አጋልጠዋል።
ሽመልስ ከማል - አፋኙን የፕሬስ ህግ በማርቀቅ፣ በመቶ የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች ከአገር እንዲሰደዱ በማድረግ፣ ጋዜጦችንና መጽሔቶችን ከህትመት ውጭ እንዲሆኑ በማድረግ፣ በቅንጅት አመራሮችና ጋዜጠኞች ላይ የሞት ቅጣት እንዲበየን በመጠየቅ፣ እነእስክንድር ነጋ በሽብርተኝነት እንዲፈረድባቸው በማድረግ፣ የሙስሊም ማህበረሰብ ተወካዮች እስር ቤት እንዲገቡና በሽብርተኝነት እንዲከሰሱ በማድረግ እንዲሁም ሙስሊሙንና ተቃዋሚዎችን በጅምላ በመስደብና በማንጓጠጥ፣ ብርቱካን ሚዴቅሳ ለ2 አመት በጨለማ እስር ቤት እንድትማቅቅ በመፍረድ..ወዘተ የመብት ረገጣ ያካሄደና በበርካታ ወገኖች

Tuesday, 24 February 2015

ኢህአዴግ ” የአገራችን ህዳሴና የሲቪል ሰርቪስ ሚና”

ኢህአዴግ “የቀለም አብዮትና አመጽ የመምራት እድል አለው ያለውን የተማረውን የመንግስት ሰራተኛ ክፍል በፍጹም እንደማያምነው” ገለጸ
የካቲት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ ” የአገራችን ህዳሴና የሲቪል ሰርቪስ ሚና” በሚል ርዕስ ለከፍተኛ አመራሩ ስልጠና ባዘጋጀው ሰነድ ላይ፣ በመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ የሚገኘው የተማረው ክፍል በኢህአዴግ የመጨረሻው የማይታመነው ክፍል ነው ሲል ገልጾታል። “ይህ የተማረው ሃይል” ይላል ሰነዱ ” አመፅየመምራት፤ኢሳትና ቪኦኤን ከመሳሰሉ አፍራሽ ሚዲያዎች ጋር በመተባበር የቀለም አብዮት ለመምራት ፣ አመጽ ለማደራጀት እና መሪ ተዋናይ ለመሆን ያለው እድል ሰፊ ነው” ።
የተማረው የመንግስት ሰራተኛ “መንግስት ቢቀየር የኢህአዴግ ህልውና ቢንኮታኮት ግድ ” እንደማይሰጠው ሰነዱ ይጠቅስና፣ በምርጫ ድምጽ አሰጣጥም መርጦ ካልወጣ በስተቀር የማይታመን፣ በተጠራበት ሰልፍ የሚገኝ ” መሆኑን ይጠቅሳል።
በመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ ያለው የተማረው ክፍል ህልውናውን ከኢህአዴግ ጋር መመስረት አለመቻሉን የሚገልጸው ሰነዱ፣ ምክንያቱ ደግሞ “ከፍተኛ አመራሩ ፣ መካከለኛውና አባላቱም ጭምር፣ ሌላ መንግስት ቢመጣም በእውቀቱ እና በስራው መኖር እንደሚችል ማመኑ” ነው ይላል።
የተማረው የመንግስት ሰራተኛ “ለውጥ ፋላጊ ፣የመረጃ ሃይል እና አቅርቦት በተደራጀ አግባብ ያለው፣ እራሱን እንደሚዛናዊ ሃይል የሚቆጥር እና በበደሉት ጥቂት አመራሮች ላይ አቂሞ የሚገኝ “እንዲሁም ሌላውንም የማስካድ አቅም ያለው በኢህአዴግ የመጨረሻው የማይታመነው ክፍል ነው ተብሎ በኢህአዴግ መፈረጁንም ሰነዱ ይገልጻል።
የመንግስት ሰራተኛው ልማታዊ አልሆነም የሚለው የስለጠና ሰነዱ፣ ይህንኑ ለመፈጸም በአምስት ክፍሎች የተዋቀረ የለውጥ ሰራዊት አደረጃጀት መዘጋጀቱንም ይናገራል። አንደኛው እና የለውጥ ሰራዊቱን የበላይ ሆኖ የሚቆጣጠረው ኮማንድ ፖስት የሚባለው ክፍል ሲሆን፣ በዚህ እዝ ስር ሚኒስትሮችና የተቋማት ስራ አስፈጻሚዎች መካተታቸውን ይናገራል። ሁለተኛው የስልጣን ክፍል ደግሞ ፕሮሰስ ካውንስል የሚባለው ሲሆን፣ በዚህ ከፍል የተቋም ሃላፊዎች ፣ የስራ ሂደት ሃላፊዎች ተመድበዋል። የስራ ሂደት በሚባለው ሶስተኛው ክፍል ደግሞ የስራ ሂደት ሃላፊና የቡድን ሃላፊዎች ተካተውበታል። የቡድን ሰራተኞችን የያዘው አራተኛው ክፍል ፣ በስሩ ስለሚካተቱ ሰዎች አይዘረዝርም። 1 ለ5 ሰራተኞች የተባለው ደግሞ የመጨረሻው የአደረጃጀቱ ክፍሎች እና ታች ያለውን የመንግስት ሰራተኛ የሚመለከተው ነው።
የለውጥ ሰራዊቱ በዚህ መልኩ ተዋቅሮ እንደሚጓዝ ሰነዱ አስምሮበታል።
ኢህአዴግ የመንግስት ሰራተኛውን በራሱ መንገድ ለመቅረጽ የተጠቀመባቸው መንገዶች ሁሉ የተፈለገውን ውጤት እንዳላስገኙለት በሰነዱ ላይ ጠቅሶ፣ ቀጣዩ ስራ የለውጥ ሰራዊቱን በዚህ መልኩ አደራጅቶ መጓዝ መሆኑንም አስቀምጧል።
የመንግስት ሰራተኛው ስለ አገሪቱ ህገ መንግስት፣ ስለ ህዝቦች ትግልና አገራዊ ህዳሴ እንዲሁም የልማታዊ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ትግልና ፈተናዎች በቂ ግንዛቤ ካልያዘና ይህንንም በተጨባጭ በተግባር ማሳየት ካልቻለ ፣ ሚናውን ተወጥቷል ብሎ መናገር እንደማይቻል ሰነዱ ይጠቃሳል።

Monday, 23 February 2015

አዋራጅ ሰልፎችና ድግሶች እንዲያበቁ ህወሓት ይወገድ!


pg7-logoድግሶችን፣ ወታደራዊ ሰልፎችንና ሀውልቶችን ማብዛት የአባገነኖች ሁሉ የጋራ ባህርይ ነው። ዘረኛውና ፋሽስቱ የህወሓት አገዛዝም በሕዝብ እየተጠላ፣ እያረጀና እየወላለቀ በሄደ መጠን በየተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ደግሶ መብላት፤ ወታደራዊ ሰልፍና የመሣሪያ ጋጋታ ማሳየት እና በየመንደሩ ሀውልት መመረቅ ሙያው አድርጎት ቆይቷል።
የህወሓት ድግሶችና ፌሽታዎች የአገራችን ሀብት ከማሟጠጣቸውም በላይ የመንግሥት ሠራተኞችን፣ የአርሶ አደሮችንና የአነስተኛ ነጋዴዎችን ኪስ እያራቆቱ ናቸው። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ተወላጆች በእስር ቤቶች እየማቀቁ በሚገኙበት ሁኔታ፤ በመቶ ሺዎች የሚገመቱ የአማራ አርሶአደሮች ተፈናቅለው እያለ፤ በጋምቤላና በኦጋዴን ወገኖቻችን ላይ ዘግናኝ የጅምላ ጭፍጨፋዎች እየተደረጉ፤ በአፋር፣ በሲዳማ፣ በቦረና፣ በወልቃይት እና በመላው ኢትዮጵያ ግጭቶች በበዙበት፤ ሕዝብ እያለቀሰ ባለበት በአሁኑ ሰዓት “የብሔር፣ ብሔረሰቦች መብት ተከበረ” እያሉ እነዚህኑ በደል እየደረሰባቸው ያሉ ዜጎችን ማስጨፈር እና ለእነዚህ ጭፈራዎች በርካታ ሚሊዮኖች ብር ማውጣት በእጅጉ ያስቆጫል። እነዚህ ጭፈራዎች ለህወሓት ሰዎች የገቢ ምንጮች መሆናቸው ጥርጥር የለውም፤ ለድሀው ኢትዮጵያዊ ግን መራቆቻዎች ናቸው። ከዚህም አልፎ በዘረኝነት እየተበደለ ያለ ሕዝብ ስለእኩልነት ዝፈን ማለት ክብረ ነክ ተግባር ነው። ዘንድሮ በአሶሳ የተደረገው አገር አቀፍ ድግስ ካለቀ ጥቂት ወራት በኋላ አገራችን በሌላ ዙር የህወሓቶች ድግስ ተወጥራለች።
ሰሞኑን በባህር ዳር በተደረገው የጦር ሠራዊት ሰልፍ እና ሰልፉን ተከትሎ በነበረው የድግሶች ግርግር ከሁሉም በላይ የተሰደበውና የተዋረደው የሠራዊቱ አባል ነው። አዛዦቹ መቶ በመቶ የህወሓት አባላት የሆኑበትን ሠራዊት “የኢትዮጵያ መከላከያ” ተብሎ መጠራቱ ራሱ የሚያሳፍረው ኢትዮጵያዊ ወኔ በልባቸው ውስጥ እየተንቀለቀለና እልህ እየተናነቃቸው ያሉ የሠራዊቱን አባላት ነው። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እንዴት የኢትዮጵያ ጠላቶች በሆኑ የህወሓት ካድሬዎች ይመራል? እንዴት የአስር አለቃ እንኳን ሊሆን የማይገባው የህወሓት ካድሬ “ጄኔራል” ተብሎ ኢትዮጵያዊያን ወታደሮችን እንደ ሎሌው ያዛል? እንዴት አንድ የህወሓት ሎሌ ሹመት ተሰጥቶት እየፏለለ በልምድ፣ በትምህርትና በእውቀት የሚበልጠውን ኢትዮጵያዊ ተንቆ ይዋረዳል? ይህ ቁጭትና እልህ ሠራዊቱ የዘረኛውን ህወሓት ሰልፍ አድማቂ መሆኑ የሚያከትምበት ጊዜ ይበልጥ እንዲናፍቅ የሚደረገው ነው። አልያማ ሰልፍ ያሳመረ ሠራዊት ሁሉ አሸናፊ እንዳልሆነ የታወቀ ነው። በሰልፍ ብዛትና በመሣሪያ ትዕይንት ማሸነፍ ቢቻል ኖሮ የትም አገር አምባገነኖች ባልወደቁም፤ ህወሓት ራሱን ስልጣን ላይ ባልወጣም ነበር።
የህወሓት ምሥረታ 40ኛ ዓመት ድግስም ሌላው የታሪክና የሀብት ውድመት የሚያስከትል ክስተት ነው። የካቲት 11 ቀን 1967፣ ጥቂት ኢትዮጵያዊያን እናታቸውን ኢትዮጵያን ለመግደል ያሴሩበት እና ልጆች በእናታቸው ላይ ቢላዋ የሳሉበት ዕለት በመሆኑ በሀዘንና በሱባኤ እንጂ በድግስና በጭፈራ የሚታሰብ ዕለት አይደለም። ሲነሳ ምንም ይሁን ምን ዛሬ በደረስንበት ሁኔታ ሲገመገም፣ ኢትዮጵያ በታሪኳ ውስጥ ህወሓትን የመሰለ መሠሪና አድርባይ ድርጅት ገጥሟት አያውቅም። እነሆ ዘንድሮም ይኸው አድርባይ ድርጅት የመሪዎቹን የሀብትና ዝና ረሀብ ለማስታገስ ሲል ያልነበረ ታሪክ እየፈጠረ በድግስ ስም ከድሀው ገንዘብ እየሰበሰበ ለሀብታም የህወሓት አባላትና ደጋፊዎች ያሸጋግራል። የድግሶቹ ሁሉ አዘጋጆች፣ እቃ አቅራቢዎችና ተጠቃሚዎች ራሳቸው የህወሓት መሪዎችና አሽቃባጮቻቸው ሲሆኑ ከፋዩ ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው። በህወሓት ድግስ የሚባክነው የሕዝብ ሀብት ስንት ሆስፒታል ይገነባ እንደነበር ስናስብ እና ይህ ሀብት በተገቢው ቦታ ውሎ ቢሆን ኖሮ ዛሬ ስም ብቻ የያዙ ዩንቨርስቲዎቻችንን ትምህርት መቅሰሚያ ማድረግ እንችል እንደነበር ስናሰላ ሀዘናችን ጥልቅ ነው። ህወሓት ለልጅ ልጆቻችን የሚተርፍ ዕዳ እየቆለለ ዳንኪራ ሲረግጥና ሲያስረግጥ ማየትና መስማት ህሊና ሊሸከመው ከሚችል በላይ ነው።
አርበኞች ግንቦት 7፡ የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በህወሓት ወታደራዊ ሰልፍ እና የመሣሪያዎች ትዕይንት የሚረበሽ ድርጅት አይደለም። ይልቁንም በሰልፉ ጨኸት የታፈነው የኢትዮጵያዊ ወታደር ጩኸት ይሰማዋል። ኢትዮጵያዊ ወታደር በአዛዦቹ ላይ ጥርሱን ነክሶ፣ ቂም አርግዞ ሰልፋቸውን እንደሚሰለፍ አርበኞች ግንቦት 7 ያውቃል። አርበኞች ግንቦት 7፣ የሠራዊቱ አባላት ውስጥ ውስጡን እየተሰቃዩ የታዘዙትን መፈፀማቸው መብቃት አለበት ይላል፤ ወይ ተቀላቀሉን፣ አሊያም እውስጡ ሆናችሁ ሥርዓቱን የማዳከም ሥራዎችን ሥሩ። በእናንተ ውርደት የዘራፊዎች፣ ሙሰኖች፣ ጎጠኞችና ዘረኞች ደረት አብጦ መታየት የለበትም።
አርበኞች ግንቦት 7፣ የዘንድሮው የህወሓት 40ኛ ዓመት በዓል የጨረሻው በዓል እንዲሆን፤ ከርሞም ተመሳሳይ አዋራጅ በዓል እንዳናከብር፤ ሠራዊቱ በዘራፊዎች ታዞ የሚሰለፍበት ውርደት እንዲያበቃ ተባብረን ህወሓትን እንቅበር ይላል።


    ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

    Sunday, 22 February 2015

    Anti-terrorism law and it's out put in Ethiopia

    Since the adoption of anti-terrorism law in Ethiopia, many  private newspapers and magazine have been eventually  shut down. bloggers, Journalist, human right  activists and opposition party leaders and members have been targeted and thrown into jail as they are considered as a terrorist. the regime uses anti-terrorism law to curb our freedoms of expression.  only state run newspapers, TV and radio remain as a propaganda instrument in the country. 

    ምርጫ በሎተሪ!!!!!

    በአዲስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ሰማያዊ ፓርቲን ወክላ ለተወካዮች ምክር ቤት በዕጩነት ቀርባ የነበረችው ወይንሸት ሞላን ጨምሮ ሌሎችም አዲስ አበባ ውስጥ ሰማያዊ ፓርቲን ወክለው ለተወካዮች ምክር ቤት በዕጩነት የቀረቡ ዕጩዎች ‹‹ዕጣው ስላልደረሳችሁ አትወዳደሩም›› መባላቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ከወይንሸት ሞላ በተጨማሪ ብሌን መስፍንና አማኑኤል አዱኛ የተባሉ የሰማያዊ ዕጩዎች ‹‹ዕጣው አልደረሳችሁም›› ተብለው ከዕጩነት ውጭ ሆነዋል፡፡

    ታሪክ አጥፍተን ታሪክ አንሠራም

    የቤተክርስቲያን ነዋየ -ቅድሳት ለዓባይ ግድብ ተብሎ መሰጠቱ ተዘገበ
    የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሪፖርተር ጋዜጣ እንደዘገበው በእንጦጦ ማርያም ሙዚየም የወርቅ መስቀሎች ጠፍተዋል መባሉ በምእመናን ዘንድ ተቃውሞ አስነስቷል።
    ለርዕሰ አድባራት እንጦጦ መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን፣ ከተለያዩ ምዕመናን በስለትና በስጦታ የተሰጡና እስከ አራት ኪሎ ግራም ሊመዝኑ ይችላሉ የተባሉ ሁለት የወርቅ መስቀሎችና አንድ የወርቅ ሐብል፣ በቅርስነት ከተቀመጡበት ሙዚየም ውሰጥ መጥፋታቸውን የደብሩ ካህናትና የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡
    የቤተ ክርስቲያኗ ካህናት፣ ሠራተኞችና የአካባቢው ነዋሪዎች-በጋራ በመሆን የደብሩ አስተዳዳሪና ሌሎች ኃላፊዎች ተባብረው ወርቆቹን ማጥፋታቸውን በመግለጽ ተቃውሟቸውን በፊርማ አስደግፈው ለመንበረ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት፣ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት፣ ለሀገረ ስብከቱ ቅርሳ ቅርስ ክፍል፣ ለአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮና ለጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምርያ በፊርማ አስገብተዋል፡፡
    የደብሩ ካህናት፣ የተለያዩ ሠራተኞችና የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት፣ በቤተ ክርስቲያኗ የቅርስ ማስቀመጫ ሙዚየም ውስጥ፤ የአፄ ምኒልክ የወርቅ ጫማ፣ የእቴጌ ጣይቱ ብጡል የተለያዩ አልባሳት፣ አልጋና በተለያዩ ምክንያቶች ለቤተ ክርስቲያኗ የገቡ በርካታ የወርቅ፣ የብር፣ የነሐስ፣ የተለያዩ ቅርፃ ቅርፆችና ቅርሶች ይገኛሉ፡፡
    በማንና በምን ሁኔታ እንደተወሰዱ ባይታወቅም፣ በቱሪስቶች በመጎብኘትም ከፍተኛ ገቢ ሲያስገኙ ከቆዩት ከእነኚህ ቅርሶች መካከል ጥቂት የማይባሉ ቅርሶች መጥፋታቸውን ካህናቱ ተናግረዋል።
    የቤተ ክርስቲያኗ አስተዳዳሪ መልዓከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ገብረኢየሱስ መኮንን ጥቅምት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. ለሙዚየሙ ቁልፍ ያዥ ለመምሬ አስፋው ገብረ ማርያም በጻፉት ደብዳቤ ፦ በቅርሶች መመዝገቢያ (መረካከቢያ) ቁጥር 170 ላይ የሚገኙትን ሁለት የወርቅ መስቀሎችና አንድ የአንገት ወርቅ ሐብል ወጪ አድርገው ለሊቀ ህሩያን ቃለጽድቅ ኃይሌ እንዲሰጡ ትእዛዝ ማስተላለፋቸው ተመልክቷል፡፡
    ከቅርስ ማስቀመጫ ሙዚየሙ ወጥተዋል የተባሉት ወርቆች የት እንደደረሱ ባለመታወቁ ካህናቱ፣ ሠራተኞቹና ምዕመናን ግራ ተጋብተው ባለበት ሁኔታ፣ አስተዳዳሪው መልዓከ ጸሀይ ታኅሳስ 27 ቀን 2007 ዓ.ም. ሠራተኞችን ሰብስበው ለዓባይ ህዳሴ ግድብ ቦንድ ለመግዛት በሙዚየሙ ውስጥ ያሉ ወርቆች መሸጥ እንዳለባቸው ሐሳብ ማቅረባቸውን ሰራተኞቹ ተናግረዋል፡፡
    ‹‹ታሪክ አጥፍተን ታሪክ አንሠራም፤›› በማለት የአስተዳዳሪውን ሐሳብ በአንድ ድምጽ መቃወማቸውን የገለጹት ሰራተኞቹ ፣ ደመወዛቸውን በማዋጣት ለህዳሴ ግድብ ቦንድ እንደሚገዙ የተናገሩ ቢሆንም፣ አስተዳዳሪው ግን እንዳስፈራሩዋቸው አስረድተዋል፡፡
    ስለጉዳዩ የተጠየቁት የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ መልዓከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ገብረ ኢየሱስ መኮንን፣ ‹‹የተባለው ሁሉ በተለይ ቦንድ የተባለው ጉዳይ ውሸትና ሐሰት ነው፤›› በማለት አስተባብለዋል፡፡ ሀገረ ስብከቱ ከወሰነበት ውጪ የተደረገ ነገር እንደሌለም አስተዳዳሪው አክለዋል፡፡ ጸሐፊው መጋቤ ሐዲስ ዲበኩሉ ገብረዋህድ ግን፣ “ተሰጠ የሚባለው ወርቅ የአንገት ሐብልና የጣት ቀለበት ከምዕመናኑ በስለት የሚገባና ሀገረ ስብከቱ የወሰነበት መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡ ጉዳዩን ያውቀዋል የተባለውን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን <<ምእመናኑና ካህናቱ ወርቅ ጠፍቷል በሚል ያቀረቡት ተቃውሞ ዝም ተብሎ የሚታይ ሳይሆን መጀመርያ ማጣራት ተገቢ ነው” ብለዋል።
    ሀገረ ስብከቱ የካቲት 10 ቀን 2007 ዓ.ም. ጉባዔ አድርጎ አጣሪ ኮሚቴ መሰየሙን የተናገሩት ስራ አስኪያጁ፤ ከቅርስ ጥበቃና ባላደራ ባለሥልጣን፣ ከጉለሌ ክፍለ ከተማ ፍትሕ ጽሕፈት ቤት፣ ከሀገረ ስብከቱ ካህናት አስተዳዳሪ መምርያ፣ ከቅርሳ ቅርስና ከክፍለ ከተማው ሀገረ ስብከት አምስት አባላት ያሉት ኮሚቴ ተሰይሞ የካቲት 11 ቀን 2007 ዓ.ም. በደብሩ በመገኘትና ኃላፊዎቹ ባሉበት እንደሚያጣራም አስታውቀዋል፡፡
    'የቤተክርስቲያን ነዋየ -ቅድሳት ለዓባይ ግድብ ተብሎ መሰጠቱ ተዘገበ
የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሪፖርተር ጋዜጣ እንደዘገበው በእንጦጦ ማርያም ሙዚየም የወርቅ መስቀሎች ጠፍተዋል መባሉ በምእመናን ዘንድ  ተቃውሞ አስነስቷል።
ለርዕሰ አድባራት እንጦጦ መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን፣ ከተለያዩ ምዕመናን በስለትና በስጦታ የተሰጡና እስከ አራት ኪሎ ግራም ሊመዝኑ ይችላሉ የተባሉ ሁለት የወርቅ መስቀሎችና አንድ የወርቅ ሐብል፣ በቅርስነት ከተቀመጡበት ሙዚየም ውሰጥ መጥፋታቸውን የደብሩ ካህናትና የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡
የቤተ ክርስቲያኗ ካህናት፣ ሠራተኞችና የአካባቢው ነዋሪዎች-በጋራ በመሆን  የደብሩ አስተዳዳሪና ሌሎች ኃላፊዎች ተባብረው ወርቆቹን ማጥፋታቸውን በመግለጽ ተቃውሟቸውን በፊርማ አስደግፈው  ለመንበረ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት፣ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት፣ ለሀገረ ስብከቱ ቅርሳ ቅርስ ክፍል፣ ለአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮና ለጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምርያ በፊርማ  አስገብተዋል፡፡
የደብሩ ካህናት፣ የተለያዩ ሠራተኞችና የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት፣ በቤተ ክርስቲያኗ የቅርስ ማስቀመጫ ሙዚየም ውስጥ፤ የአፄ ምኒልክ የወርቅ ጫማ፣ የእቴጌ ጣይቱ ብጡል የተለያዩ አልባሳት፣ አልጋና  በተለያዩ ምክንያቶች ለቤተ ክርስቲያኗ የገቡ በርካታ  የወርቅ፣ የብር፣ የነሐስ፣ የተለያዩ ቅርፃ ቅርፆችና ቅርሶች ይገኛሉ፡፡
በማንና በምን ሁኔታ እንደተወሰዱ ባይታወቅም፣ በቱሪስቶች በመጎብኘትም ከፍተኛ ገቢ ሲያስገኙ ከቆዩት  ከእነኚህ ቅርሶች መካከል  ጥቂት የማይባሉ ቅርሶች መጥፋታቸውን ካህናቱ ተናግረዋል።
የቤተ ክርስቲያኗ አስተዳዳሪ መልዓከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ገብረኢየሱስ መኮንን ጥቅምት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. ለሙዚየሙ ቁልፍ ያዥ ለመምሬ አስፋው ገብረ ማርያም  በጻፉት ደብዳቤ ፦ በቅርሶች መመዝገቢያ (መረካከቢያ) ቁጥር 170 ላይ የሚገኙትን ሁለት የወርቅ መስቀሎችና አንድ የአንገት ወርቅ ሐብል  ወጪ አድርገው ለሊቀ ህሩያን ቃለጽድቅ ኃይሌ እንዲሰጡ  ትእዛዝ ማስተላለፋቸው ተመልክቷል፡፡
ከቅርስ ማስቀመጫ ሙዚየሙ ወጥተዋል የተባሉት ወርቆች የት እንደደረሱ ባለመታወቁ ካህናቱ፣ ሠራተኞቹና ምዕመናን ግራ ተጋብተው ባለበት ሁኔታ፣ አስተዳዳሪው  መልዓከ ጸሀይ ታኅሳስ 27 ቀን 2007 ዓ.ም. ሠራተኞችን ሰብስበው ለዓባይ ህዳሴ ግድብ ቦንድ ለመግዛት በሙዚየሙ ውስጥ ያሉ ወርቆች መሸጥ እንዳለባቸው ሐሳብ ማቅረባቸውን  ሰራተኞቹ ተናግረዋል፡፡
‹‹ታሪክ አጥፍተን ታሪክ አንሠራም፤›› በማለት  የአስተዳዳሪውን ሐሳብ  በአንድ ድምጽ መቃወማቸውን የገለጹት  ሰራተኞቹ ፣ ደመወዛቸውን በማዋጣት ለህዳሴ ግድብ ቦንድ እንደሚገዙ የተናገሩ ቢሆንም፣ አስተዳዳሪው ግን እንዳስፈራሩዋቸው አስረድተዋል፡፡
ስለጉዳዩ የተጠየቁት የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ መልዓከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ገብረ ኢየሱስ መኮንን፣ ‹‹የተባለው ሁሉ በተለይ ቦንድ የተባለው ጉዳይ ውሸትና ሐሰት ነው፤›› በማለት አስተባብለዋል፡፡ ሀገረ ስብከቱ ከወሰነበት ውጪ የተደረገ ነገር እንደሌለም  አስተዳዳሪው አክለዋል፡፡ ጸሐፊው መጋቤ ሐዲስ ዲበኩሉ ገብረዋህድ  ግን፣ “ተሰጠ የሚባለው ወርቅ የአንገት ሐብልና የጣት ቀለበት ከምዕመናኑ በስለት የሚገባና ሀገረ ስብከቱ የወሰነበት መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡ ጉዳዩን ያውቀዋል የተባለውን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን  <<ምእመናኑና ካህናቱ ወርቅ ጠፍቷል በሚል ያቀረቡት ተቃውሞ ዝም ተብሎ የሚታይ ሳይሆን መጀመርያ ማጣራት ተገቢ ነው” ብለዋል።
ሀገረ ስብከቱ የካቲት 10 ቀን 2007 ዓ.ም. ጉባዔ አድርጎ አጣሪ ኮሚቴ መሰየሙን የተናገሩት ስራ አስኪያጁ፤ ከቅርስ ጥበቃና ባላደራ ባለሥልጣን፣ ከጉለሌ ክፍለ ከተማ ፍትሕ ጽሕፈት ቤት፣ ከሀገረ ስብከቱ ካህናት አስተዳዳሪ መምርያ፣ ከቅርሳ ቅርስና ከክፍለ ከተማው ሀገረ ስብከት አምስት አባላት ያሉት ኮሚቴ ተሰይሞ የካቲት 11 ቀን 2007 ዓ.ም. በደብሩ በመገኘትና ኃላፊዎቹ ባሉበት እንደሚያጣራም አስታውቀዋል፡፡'
    source: ESAT 

    Friday, 20 February 2015

    ምርጫ ቦርድ ከ200 በላይ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎችን ሰረዘ

    ‹‹ምርጫ ቦርድ ሰማያዊ በምርጫ ሂደቱ እንዲቆይ አይፈልግም›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
    ሰማያዊ ፓርቲ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ከ200 በላይ ዕጩዎቹ በምርጫ ቦርድ ትዕዛዝ እንደተሰረዙበት የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በመላ አገሪቱ በተለይም በደቡብ ወሎ፣ በሰሜን ሸዋ፣ በወላይታ፣ በቤንች ማጅ፣ በምዕ/ጎጃም፣ በሲዳማ፣ በከምባታ፣ በጋሞጎፋ፣ አዲስ አበባ፣ በደቡብ ጎንደርና ጉጅን ጨምሮ በሌሎችም የአገሪቱ ክፍሎች ከ200 በላይ ዕጩዎቹ አንድን ዕጩ ለመሰረዝ የሚያበቃ ምንም አይነት ህጋዊ ምክንያት ሳይኖር ‹‹ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደብዳቤ ታዘናል›› በማለት ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤትና ለክልል ምክር ቤቶች ያስመዘገብናቸው ዕጩ ተወዳዳሪዎቹን በመሰረዝ ከምርጫው ውድድር ውጪ እንዲሆኑ እየተደረገ እንደሆነ ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ገልጸዋል፡፡
    በየክፍለ ሀገሩ የተሰረዙት ዕጩዎች ‹‹ፓርቲው ትብብር የሚባል ህገ ወጥ አደረጃጀት መስርቷል፣ የሌሎች ፓርቲዎች አባላት ናችሁ›› የመሳሰሉ ምክንያቶችና ደብዳቤ የተሰጣቸው ሲሆን በአንጻሩ በአዲስ አበባ የተሰረዙት ዕጩዎች ከምርጫ አስፈጻሚዎች ምንም አይነት ምክንያትና ደብዳቤ እንዳልተሰጣቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡ ዕጩዎቹ ‹‹የተሰረዝንበትን ምክንያት ንገሩን፣ ደብዳቤ ልትሰጡን ይገባል›› ቢሉም የምርጫ አስፈጻሚዎቹ ‹‹እኛ እናንተን ለመመዝገብ ችግር የለብንም፡፡ ግን ከበላይ አካል እንዳንመዘግብ ተነግሮናል፡፡ ደብዳቤም ልንሰጣችሁ አንችልም፡፡›› የሚል መልስ እንደሰጧው ተግልጾአል፡፡
    በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎች መሰረዛቸውን ተከትሎ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች የቦርዱን ሰብሳቢ ፕ/ር መርጋ በቃናን ለማግኘት ቢጥሩም ‹‹ከከተማ ውጭ ናቸው፡፡ አሁን አታገኟቸውም›› የተባሉ ሲሆን ፕ/ር መርጋ የህወሓትን 40ኛ አመት ለማክበር መቀሌ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በትናንትናው ዕለት በጉዳዩ ላይ ከቦርዱ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ነጋ ዱፌሳ ጋር የተነጋገሩ ሲሆን አቶ ነጋ ‹‹ማመልከቻ አስገቡ›› ከማለት ውጭ ዕጩዎቹ ለመሰረዛቸው ተጨባጭ ምክንያት መስጠት እንዳልቻሉ ኢ/ር ይልቃል ገልጸውልናል፡፡
    ‹‹የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎችን ያለ አግባብ የሚሰርዙት ሰማያዊ በምርጫ ሂደቱ ጫና መፍጠር ስለሚችል በሂደቱ እንዲቆ ስለማይፈልጉ ነው›› ያሉት ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት፤ ሆኖም ይህ የምርጫ ቦርድ ውሳኔ ለነጻነት የሚያደርጉትን ትግል ትክክለኛ እንደሆነ እንዳስረገጠላቸው፣ ይህን የነጻነት ትግልም አጠናክረው እንደሚቀጥሉና የካቲት 22 ፓርቲያቸው ከትብብሩ ፓርቲዎች ጋር በ15 ከተሞች በተመሳሳይ ጊዜ በ15 ከተሞች የሚያደርገው ሰልፍ የዚሁ የነጻነት ትግል አካል እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
    source:ነገረ ኢትዮጵያ

    Thursday, 19 February 2015

    February 10 ESAT news  

    ሚኒስትሮችንና አፈ-ጉባኤዎችን ጨምሮ የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች በቤተ መንግስት የተገመገሙበት ሰነድ ኢሳት እጅ ገብቷል።
    የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግምገማው የተካሄደው እንደተለመደው ባለስልጧናቱ በየተራ አስቀድመው ችግራቸውን እንዲናገሩ በማድረግና የራሱን ችግር በተናገረው አመራር ላይ ሌሎቹ ያላቸውን ተጨማሪ ትችት እንዲያቀርቡ
    በማድረግ ነው።
    በአቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ መሪነት በተካሄደው በዚህ ግምገማ ከ አዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ የተገመገሙት አፈ-ጉባኤ አባዱላ ገመዳ፣”የሀሰት የስራ አፈጻጽመ ታቀርቢያለሽ” የተባሉት የሴቶችና የወጣቶች ሚኒስትር ዘነቡ ታደሰ፣”ሳሞራን ትፈራዋለህ”ተብለው የተገመገሙት የመከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈርጌሳ፣”ኮምፒዩተርና ሞባይል ላይ ጥብቅ ትላለህ” የተባሉት አቶ ሬድዋን ሁሴን፣”ከባልደረቦችሽ ጋር ትጋጫለሽ”የተባሉት ወይዘሮ አስቴር ማሞ ፣”ፈሪ ነህ” የተባሉት ዶፐክተር ካሱ ይላላ፣ “ከደባል ሱስ የጸዳህ አይደለህም”የተባሉት የገንዘብ ሚኒስትሩ ሶፊያን አህመድ እና ሌሎች በርካታ ባለስልጣናት ” ሲ” አግኝተዋል።
    የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አባይ ወልዱ፣ የትምህርት ሚኒስትር ሽፈራው ሽጉጤ፣የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ ጸጋይ በርሄ፣ የ አማራ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት ዓለምነው መኮንን፣አቶ ስዩም መስፍን፣አቶ አርከበ እቁባይ እና ሌሎች በርካታ ሹመኞች “ቢ” ውጤት ተሰጥቷቸዋል።
    እስካሁን ለ ኢሳት በደረሰው ሰነድ በግምገማው “ኤ”ውጤት የተሰጣቸው የ ኢህአዴግ አመራር የህወሀቱ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖም ብቻ ናቸው። ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖም “በሶሻል ሚዲያ የግለሰቦችን ታሪክ ለራስህ ገፅታ ግንባታ አውለሀል፣ ስራ ታዘገያለህ” የሚሉና ሌሎችም ደከማ ነጥቦች የተነሱባቸው ቢሆንም፤ ከሌሎቹ አመራሮች በተለየ ሁኔታ “የቀረበብኝን ድክመት”አልቀበልም በማለት ነው ውድቅ ያደረጉት። ሌሎቹ አመራሮች በሙሉ፤ ከግምገማቸው በሁዋላ፦ “ድክመታችንን ተቀብለናል፤እናሻሽላለን”
    ማለታቸውን ተከትሎ ነው “ቢ” እና “ሲ” የተሰጣቸው። “ሲ”ከተሰጣቸው የኢህአዴግ አመራሮች መካከል ” ኢህአዴግ ገለልተኛ ነው” እያለ የሚናገርለትን ምርጫ ቦርድን በሰብሳቢነት የሚመሩት ፕሮፌሰር መርጋ በቃና ይገኙበታል። በኢህአዴግ ውስጥ ቀደም ሲል አንድን ነገር “ድርጅቱ ነው ያለው” ሲባል፤ “መለስ ነው ያለው”ማለት እንደሆነ የቀድሞው የኮሙኒኬሽን ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ኤርሚያስ ገሠሰ “የመለስ ትሩፋቶች” በተሰኘው መጽሐፋቸው መግለጻቸው ይታወቃል። ኢሳት እጅ የገባው የግምገማ ሰነድ እንደሚያመለክተው፤ የመለስን ቦታ-አቶ በረከት ስምኦን መያዛቸውን ነው።
    አቶ ሬድዋን፤”የሀገሪቱን ገጽታ ለውጪ ሚዲያ ዝግ አድርገኸዋል” ተብለው ሲገመገሙ <<ዝግ ያደረኩት እኔ ሳልሆን ድርጅቱ ነው” ብለው መልስ የሰጡ ሲሆን ፤ <<ድርጅቱ ማን ነው?>>ተብለው በአቶ ሀይለማርያም ሲጠየቅ፦<<በረከት>> በማለት መልሰዋል።

    Tuesday, 17 February 2015

    በትጥቅ ትግል የሚያምኑ ሶስት የአፋር ድርጅቶች ግንባር ፈጠሩ

    በትጥቅ ትግል የሚያምኑ ሶስት የአፋር ድርጅቶች ግንባር ፈጠሩ
    በስልጣን ላይ ያለውን የህወሃት /ኢህአዴግ መንግስት በሃይል ለመጣል የሚንቀሳቀሱት ሶስቱ የአፋር ድርጅቶች ማለትም አርዱፍ፣ ጋድሌና የአፍዴራ ታጋዮች የካቲት 8 ቀን 2007 ዓም የጋራ ግንባር ፈጥረዋል።
    የአርዱፍ ሊቀመንበር አቶ ኢብራሂም ሙሳ ለኢሳት እንደገለጹት ሶስቱም የአፋር ድርጅቶች በተናጠል ሆነው መዋጋታቸው ለስርአቱ እድሜ መርዘም አስተዋጽኦ በማድረጉ በቅድሚያ ድርጅቶቹ የጋራ ግንባር ፈጥረው በጋራ ለመዋጋት አስፈላጊ መሆኑን ስምምነት ላይ በመድረሳቸው፣ በአንድ ወታደራዊ እዝ ስር ሆነው ለመታገል ወስነዋል።
    አዲሱ ግንባር ከሌሎች የኢትዮጵያ ሃይሎች ጋር ጥምረት በመፍጠር ለመታገል ፍላጎት እንዳለውም አቶ ኢብራሂም ተናግረዋል።
    ድርድሩ የተካሄደው በአፋር ህዝብ ፓርቲ በኩል መሆኑንም ለማወቅ ተችሎአል።

    Ethiopia's media war

    Ethiopian anti-terrorism laws are forcing journalists into exile and prison, a push the government says will secure the nation.
    Ethiopia's jailed Zone 9 bloggers are on trial this week for terrorism and treason, charges facing more than two dozen journalists, bloggers and publishers. To avoid arrest, 30 journalists fled the country in the past year. The government says they’re criminals, destabilizing Ethiopia's fragile democracy in the name of “press freedom.” Rights groups say they’re victims of repression.
    source: Aljazeera

    Monday, 16 February 2015

    Ethiopia: A land grab twice the size of France

    February 16, 2015

    Stealing the Omo Valley, destroying its ancient Peoples

    Megan Perry / Sustainable Food Trust | ECOLOGIST
    A land grab twice the size of France is under way in Ethiopia, as the government pursues the wholesale seizure if indigenous lands to turn them over to dams and plantations for sugar, palm oil, cotton and biofuels run by foreign corporations, destroying ancient cultures and turning Lake Turkana, the world’s largest desert lake, into a new Aral Sea.
    Ethiopia's Omo River in 2008.
    Ethiopia’s Omo River in 2008. Photo: Marc Veraart via Flickr.com.
    There is growing international concern for the future of the lower Omo Valley in Ethiopia. A beautiful, biologically diverse land with volcanic outcrops and a pristine riverine forest; it is also a UNESCO world heritage site, yielding significant archaeological finds, including human remains dating back 2.4 million years.
    The Valley is one of the most culturally diverse places in the world, with around200,000 indigenous people living there. Yet, in blind attempts to modernise and develop what the government sees as an area of ‘backward’ farmers in need of modernisation, some of Ethiopia’s most valuable landscapes, resources and communities are being destroyed.
    A new dam, called Gibe III, on the Omo River is nearing completion and will begin operation in June, 2015, potentially devastating the lives of half a million people. Along with the dam, extensive land grabbing is forcing thousands from their ancestral homes and destroying ecosystems.
    Ethiopia’s ‘villagisation’ programme is aiding the land-grab by pushing tribes into purpose built villages where they can no longer access their lands, becoming unable to sustain themselves, and making these previously self-sufficient tribes dependent on government food aid.
    A total disregard for the rights of Ethiopia’s Indigenous Peoples
    What is happening in the lower Omo Valley, and elsewhere, shows a complete disregard for human rights and a total failure to understand the value these tribes offer Ethiopia in terms of their cultural heritage and their contribution to food security.
    There are eight tribes living in the Valley, including the Mursi, famous for wearing large plates in their lower lips. Their agricultural practices have been developed over generations to cope with Ethiopia’s famously dry climate.
    Many are herders who keep cattle, sheep and goats and live nomadically. Others practice small-scale shifting cultivation, whilst many depend on the fertile crop and pasture land created by seasonal flooding.
    The vital life source of the Omo River is being cut off by Gibe III. An Italian construction company began work in 2006, violating Ethiopian law as there was no competitive bidding for the contract and no meaningful consultation with indigenous people.
    The dam has received investment from the Industrial and Commercial Bank of China and the World Bank, and the hydropower is primarily going for export rather than domestic use – despite the fact that 77% of Ethiopia’s population lacks access to electricity.
    People in the Omo Valley are politically vulnerable and geographically remote. Many do not speak Amharic, the national language, and have no access to resources or information. Foreign journalists have been denied contact with the tribes, as BBC reporter Matthew Newsome recently discovered when he was prevented from speaking to the Mursi people.
    There has been little consideration of potential impacts, including those which may affect other countries, particularly Kenya, as Lake Turkana relies heavily on the Omo River.
    At risk: Lake Turkana, ‘Cradle of Mankind’
    Lake Turkana, known as the ‘Cradle of Mankind’, is the world’s largest desert lake dating back more than 4 million years. 90% of its inflow comes from the Omo. Filling of the lake behind the dam will take three years and use up to a years’ worth of inflow that would otherwise go into Lake Turkana.
    Irrigation projects linked with the dam will then reduce the inflow by 50% and lead to a drop of up to 20 metres in the lake’s depth. These projects may also pollute the water with chemicals and nitrogen run-off. Dr Sean Avery’s report explains how this could devastate the lake’s ancient ecosystems and affect the 300,000 people who depend on it for their livelihoods.
    Tribal communities living around the lake rely on it for fish, as well as an emergency source of water. It also attracts other wildlife which some tribes hunt for food, such as the El Molo, who hunt hippo and crocodile. Turkana is home to at least 60 fish species, which have evolved to be perfectly adapted to the lake’s environment.
    Breeding activity is highest when the Omo floods, and this seasonal flood also stimulates the migration of spawning fish. Flooding is vital for diluting the salinity of the lake, making it habitable. Livestock around the lake add nutrients to the soil encouraging shoreline vegetation, and this is important for protecting young fish during the floods.
    Lake Turkana is a fragile ecosystem, highly dependent on regular seasonal activity, particularly from the Omo. To alter this ancient ebb and flow will throw the environment out of balance and impact all life which relies on the lake.
    Severely restricted resources around the lake may also lead to violence amongst those competing for what’s left. Low water levels could see the lake split in two, similar to the Aral Sea. Having acted as a natural boundary between people, there is concern that conflict will be inevitable.
    Fear is already spreading amongst the tribes who say they are afraid of those who live on the other side of the lake. One woman said, “They will come and kill us and that will bring about enmity among us as we turn on each other due to hunger.”
    Conflict may also come from Ethiopians moving into Kenyan territory in attempts to find new land and resources.
    A land grab twice the size of France
    The dam is part of a wider attempt to develop the Omo Valley resulting in land grabs and plantations depending on large-scale irrigation. Since 2008 an area the size of France has been given to foreign companies, and there are plans to hand over twice this area of land over the next few years.
    Investors can grow what they want and sell where they want. The main crops being brought into cultivation include, sugar, cotton, maize, palm oil and biofuels. These have no benefit to local economies, and rather than using Ethiopia’s fragile fertile lands to support its own people, the crops grown here are exported for foreign markets.
    Despite claims that plantations will bring jobs, most of the workers are migrants. Where local people (including children) are employed, they are paid extremely poorly. 750km of internal roads are also being constructed to serve the plantations, and are carving up the landscape, causing further evictions.
    In order to prepare the land for plantations, all trees and grassland are cleared, destroying valuable ecosystems and natural resources.
    Reports claim the military have been regularly intimidating villages, stealing and killing cattle and destroying grain stores. There have also been reports of beatings, rape and even deaths, whilst those who oppose the developments are put in jail. The Bodi, Kwegi and Mursi people were evicted to make way for the Kuraz Sugar Project which covers 245,000 acres.
    The Suri have also been forcibly removed to make way for the Koka palm oil plantation, run by a Malaysian company and covering 76,600 acres. This is also happening elsewhere in Ethiopia, particularly the Gambela region where 73% of the indigenous population are destined for resettlement.
    Al-Moudi, a Saudi tycoon, has 10,000 acres in this region to grow rice, which is exported to the Middle East. A recent report from the World Bank’s internal watchdog has accused a UK and World Bank funded development programme of contributing to this violent resettlement.
    For many tribes in the Omo Valley, the loss of their land means the loss of their culture. Cattle herding is not just a source of income, it defines people’s lives. There is great cultural value placed on the animals. The Bodi are known to sing poems to their favourite cattle; and there are many rituals involving the livestock, such as the Hamer tribe’s coming of age ceremony whereby young men must jump across a line of 10 to 30 bulls.
    Losing their land also means losing the ability to sustain themselves. As Ulijarholi, a member of the Mursi tribe, said, “If our land is taken, it is like taking our lives.”
    They will no longer be independent but must rely on government food aid or try to grow food from tiny areas of land with severely reduced resources.
    Ethiopia’s food security
    Ethiopia is currently experiencing economic growth, yet 30 million people still face chronic food shortages. Some 90% of Ethiopia’s national budget is foreign aid, but instead of taking a grass-roots approach to securing a self-sufficient food supply for its people, it is being pushed aggressively towards industrial development and intensive production for foreign markets.
    There is a failure to recognise what these indigenous small-scale farmers and pastoralists offer to Ethiopia’s food security. Survival of the Fittest, a report by Oxfam, argued that pastoralism is one of the best ways to combat climate change because of its flexibility.
    During droughts animals can be slaughtered and resources focused on a core breeding stock in order to survive. This provides insurance against crop failure as livestock can be exchanged for grain or sold, but when crops fail there can be nothing left. Tribal people can also live off the meat and milk of their animals.
    Those who have long cultivated the land in the Omo Valley are essential to the region’s food security, producing sorghum, maize and beans on the flood plains. This requires long experience of the local climate and the river’s seasonal behaviour, as well as knowledge of which crops grow well under diverse and challenging conditions.
    Support for smallholders and pastoralists could improve their efficiency and access to local markets. This would be a sustainable system which preserved soil fertility and the local ecosystem through small-scale mixed rotation cropping, appropriate use of scarce resources (by growing crops which don’t need lots of water, for example) and use of livestock for fertility-building, as well as for producing food on less productive lands.
    Instead, over a billion dollars is being spent on hydro-electric power and irrigation projects. This will ultimately prove unsustainable, since large-scale crop irrigation in dry regions causes water depletion and salinisation of the soil, turning the land unproductive within a couple of generations.
    Short of an international outcry however, the traditional agricultural practices of the indigenous people will be long gone by the time the disastrous consequences becomes apparent.
    source: ecadf

    Ethiopian Intelligence Network: Who is behind the growth?

    Ethiopia is a low income country with a population of just under 92 million people. The country has since 1991 been under one party rule of the Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF). Dissidents who use the internet to criticise the one party rule have been accused of promoting terrorism and have been subjected to strict surveillance. According to Human Rights Watch, the increasing technological ability of Ethiopians to communicate, express their views, and organise, is viewed less as a social benefit and more as a political threat for the ruling party, which depends upon invasive monitoring and surveillance to maintain control of its population. Ethiopia regularly blocks websites, undertakes surveillance of websites and social media, and charges journalists over content published offline and online.

    The country’s laws provide for legal sanctions against individuals for content they publish online, or the ‘illegal use’ of telecoms services. Such charges have often been framed as ‘promoting terrorism’, which can attract a 20 year jail term. Thus, the country has been creating a speedily expanding, state-of-the-art surveillance state, with tacit Western back up.
    Rumors of the extent of Ethiopia’s digital surveillance and censorship state have echoed around the information security community for years. Journalists have spoken of being shown text messages, printouts of emails, and recordings of their own telephone conversations by the Ethiopian security services. From within the country, commentators connected growing telecommunications surveillance to the increasing presence of East telecommunications company ZTE.
    On the external front, analysis of the targeted surveillance of exiled Ethiopians has turned up surveillance software built and sold by Western companies, such as FinFisher and Hacking Team. Observers of the country’s national Internet censorship have reported keyword filtering of websites and blocking of Tor nodes that reveal a sophisticated national firewall conducting deep packet inspection. Ethiopia’s position as an American ally also gives it the opportunity to purchase technology made in the West to carry out its campaigns of censorship and surveillance. Ethiopia has also bolstered its surveillance capabilities with drones built by Israeli company Bluebird Systems.
    However, it is widely believed that Ethiopians have not developed the surveillance network using the available resources in the country. Indeed it is even futile to think that a third world country like it, which does not have enough resources to feed its poverty stricken population will invest heavily in surveillance technology.
    There are many who believe that West is funding such programs. However, on a more detailed look, it looks as if East technology is behind the program.
    Screenshots of extra fields on ZTE’s ZSmart customer relations management tool appear to show that Ethiopia’s telco administrators can check customers against a “blacklist,” and digitally record calls with the press of a single button.
    These features could simply be a result of Ethiopia’s censorship team quickly adopting new techniques — or it could mean that Ethiopia is one of the few countries that benefits from the direct export of Great Firewall technology. In the case of Ethiopia, there have been reports that East is training the surveillance team for as period of six months and then using it for own proxy intelligence. Whether or not the activities of such companies represent cybersecurity concerns – these rapid changes in Africa’s media and telecommunications sphere are an overlooked and illustrative example of the impacts and influences of a rising East, which warrant greater study and attention from policymakers and civil society in Africa and elsewhere, in particular those who are keen to ensure both increased cooperation and connectivity and free and secure communications among citizens.
    source:  newdelhitimes 

    Saturday, 14 February 2015

    የ2007ቱን ሀገራዊ ምርጫ ሂደት እና ከምርጫዉ ዉጭ ያሉ አዋጭ አማራጮችን በተመለከተ የአርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ የአቋም መግለጫ

    pg7-headerአርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሰላማዊ፣ ተዓማኒና ፍትሀዊ በሆነ ምርጫ የማይፈልጋቸውን መሪዎች መሻር፤ የሚፈልጋቸውን ደግሞ መሾም የሚያስችሉትን መሠረቶች ለመጣል የሚታገል ንቅናቄ ነው። እንደሚታወቀው የሕዝብ እውነተኛ ፍላጎት የሚገለጽበት እውነተኛ ምርጫ እንዲኖር ገለልተኛና ቀልጣፋ የፍትህ ሥርዓት፣ የጦርና የፓሊስ ሠራዊት ሊኖሩ ይገባል። ነፃ የሚዲያ ተቋማትና በነፃነት የሚንቀሳቀሱ የሲቪክ ማኅበራት መኖርም መታለፍ የሌለባቸው አቢይ ጉዳዮች ናቸው። አማራጭ ፓሊሲዎችን ማቅረብ የሚችሉ በነፃነት የሚንቀሳቀሱ የፓለቲካ ፓርቲዎች ከሌሉም አማራጮች የሉምና ምርጫ ትርጉም የለውም። ይህ ሁሉ ቢሟላ እንኳን ምርጫውን የሚያስፈጽመው አካል ገለልተኛ፣ ሀቀኛና ተዓማኒ ካልሆነ የሚደረገው ምርጫ የመራጩን ሕዝብ ፍላጎት የሚያንፀባርቅ ሊሆን አይችልም።
    ከላይ የተዘረዘሩትን የምርጫ እሴቶች ሙሉ በሙሉ ባይሆንም እንኳን የተወሰኑትን በመጠኑም ቢሆን ያካተተ ምርጫ እንዲኖር መጣርና በሂደት የምርጫውን አፈፃፀም ማሻሻል ይቻል ይሆናል በሚል እምነት የዲሞክራሲ ኃይሎች በህወሓት የሴራ ምርጫዎች ሲሳተፉ ቆይተዋል። ሆኖም በህወሓትና በእውነተኛ ምርጫ መካከል ያለው ተቃርኖ እያደር እየሰፋ ሲሄድ እንጂ ሲጠብ አልታየም። በህወሓት ሙሉ ቁጥጥር ስር በሚካሄድ ምርጫ ኢትዮጵያን የሚጠቅም ለውጥ ሊመጣ ይችላል የሚለው እምነት ለአርበኞች ግንቦት 7 ፈጽሞ የተሟጠጠው ከምርጫ 97 ማግስት ጀምሮ ነው። በግንቦት 7 ቀን 1997 ዓም የኢትዮጵያ ሕዝብ በታላቅ የለውጥ ተስፋ የሰጠው ድምጽ በህወሓት የተዘረፈው ከላይ የተዘረዘሩት ተቋማት ያልነበሩ በመሆናቸው፤ ስለዚህም ከምርጫ በፊት ተቋማቱን መገንባት፤ ተቋማቱን ለመገንባት ደግሞ ህወሓትን ከስልጣን ማስወገድ ይገባል ብሎ በማመኑ ነው አርበኞች ግንቦት 7 በሁለገብ የትግል ስልት በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኘው።
    ያም ሆኖ ግን በምርጫ ላይ ያላቸው ተስፋ ፈጽሞ ያልተሟጠጠ ፓርቲዎችን በማክበርና ሥራቸውንም አስቸጋሪ ላለማድረግ ሲባል ከምርጫ 97 ወዲህ የነበሩ ብሄራዊም ሆነ ክልላዊ ምርጫዎችን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከምርጫ ዉጭ ያሉ ሌሎች አማራጮችን ብቻ እንዲመለከት አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪ አድርጎ አያውቅም ነበር። አሁን ግን የአገራችን ኢትዮጵያ የፓለቲካ ሁኔታዎች ይህንን የቆየ አቋም በሚያስቀይር መንገድ፤ የአገራችንን የወደፊት ዕድል ብቻ ሳይሆን ባጠቃላይ ያካባቢውን ሰላም በሚጎዳ መልኩ ተቀይሯል። የሰሞኑ የወያኔ እርምጃዎች ትንሽ ተስፋ ያደርግ የነበረውን የዴሞክራሲ ወገንተኛ ተስፋም እምሽክ አድርጎ በልቶታል:: እየተቃረበ ያለው ዓይነት የፌዝ ምርጫ ወያኔ እንደ እንጄራ የራበውን የተቀባይነት እጦት ለአጭር ጊዜ ያስታግስለት ይሆናል እንጂ የሀገሪቱን እያደር እየተወሳሰበ የመጣ ችግር ለጊዜውም እንኳን የሚያስታግስ አይሆንም፤ ይልቁንም ጊዜው በገፋ ቁጥር ችግሩ መቋጠሪያ የጠፋው እየሆነ ይሄዳል::
    የሁኔታውን አሳሳቢነት ከግምት ውስጥ በማስገባት የአርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ አመራር የወቅቱን የአገራችን የፓለቲካ ሁኔታ በጥንቃቄ መርምሮ የሚከተሉት ግንዛቤዎች ላይ ደርሷል።
    1. ህወሓት ብዙዎች እትዮጵያዊያን የተሰውላቸውን አንድነት ፓርቲንና መኢአድን በመበተን የድርጅቶቹን ስምና ንብረት ለአገልጋዮቹ መስጠቱ፤ ከዚህ በፊት ሲያደርግ እንደነበረው የመራጭን ድምጽ መስረቅ ሳይበቃው የምርጫ ተወዳዳሪንም መዝረፍ መጀመሩን አመላካች ነው። ይህ ተግባር ህወሓት የምርጫ ውጤትን ብቻ ሳይሆን ተወዳዳሪዎችንም እሱ ራሱ ለመምረጥ መወሰኑን ያሳያል፤ ከዚህ በተጨማሪ የሴራ ምርጫውን ከጅምሩ ጀምሮ አስቀድሞ እስከተወሰነለት መዳረሻው ድረስ ለምንም ዓይነት ያልተጠበቀ አጋጣሚ (በምርጫው ወቅት የሚደረጉትን ክርክር ተብዬዎች ጨምሮ) እድል ላለመስጠት ወስኖ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን በግልጽ ያሳያል፤
    2. ይህ እኩይ ውሳኔ በምርጫ ቦርድ ፊርማና አንደበት ቢነገርም ምንጩ የህወሓት ፓሊት ቢሮ መሆኑን የሚከተሉት ተግባራት ይጠቁማሉ፤
    2.1. በምርጫ ቦርድ በኩል እንዲገለጽ የተወሰነው እርምጃ ለማስመሰል ያክልም ቢሆን የህጋዊነት ሽፋን እንዲኖረው አለመደረጉ ውሳኔው ፍጹም እብሪተኛ በሆነ አካል መወሰኑን ያመለክታል። እንዲህ ዓይነቱ እብሪተኛ አካል ደግሞ የህወሓት ፓሊት ቢሮ ነው። ውሳኔውን ለማስፈፀም የነበረው ጥድፊያም ይህንኑ ያጠናክራል።
    2.2. ለማስመሰያ ያክል እንኳን ምንም አይነት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሳይኖር ፓሊስ የአንድነትና የመኢአድ ቢሮዎችን መውረሩ፤ ህወሓት አንድነትንና መኢአድን አጥፍቶ የድርጅቶቹን ስሞችና ንብረቶች ለሚፈልጋቸው ሰዎች ሰጥቶ በአስቸኳይ ለምርጫ ድራማው በፊት መስመር ሊያሰልፋቸው መወሰኑን አመላካች ነው። እንዲህ ዓይነት ከባድ ውሳኔ የሚሰጠው ደግሞ የህወሓት ፓሊት ቢሮ ብቻ ነው።
    2.3. ወደ ፈቃድ መንጠቅ ከመደረሱ በፊትም በሰማያዊ ፓርቲ፣ በአንድነትና በመኢአድ አባላት የደረሰው አረመኔያዊ ድብደባ፤ ንቁ የፓለቲካ ተሳትፎ የሚያደርጉ ዜጎች ላይ የሚደርሰው እስር፣ መሰወርና እና ባልታወቁ ሰዎች ተገድሎ መገኘት መብዛት እነዚህን አገራዊ ፓርቲዎች የመበተን የፓለቲካ ውሳኔ መሰጠቱን አመላካቾች ናቸው።
    3. ለጊዜው የፈቃድ ነጠቃና የንብረት ዘረፋ የተፈፀመው በአንድነትና በመኢአድ ላይ ቢሆንም በሰማያዊ ፓርቲ ላይ በየእለቱ እየጠነከረ የመጣው የአፈና እርምጃም በተመሳሳይ ፓርቲውን ወደማገድ አለዚያም ፈጽሞ መንቀሳቀስ ወደማይችልበት ደረጃ ሊያደርሰው ይችላል የሚል እምነት አሳድሯል። ሌሎች ፓርቲዎችም ከዚህ ህወሓት ካሰመረው የውሸት ጫወታ መስመር የመውጣት ዝንባሌ ቢያሳዩ ተመሳሳይ እርምጃ አይቀርላቸውም።
    4. የህወሓት የወቅቱ የጥፋት ዒላማ ያነጣጠረው አንፃራዊ በሆነ መንገድ የተሻለ መዋቅርና ማኅበራዊ መሠረት ባላቸው እና በአገራዊ አጀንዳዎቻቸው በሚታወቁ ፓርቲዎች ላይ መሆኑ፤ የወቅቱ የጥፋት ዘመቻ የኢትዮጵያ አንድነትን የማዳከምና ከፋፍሎ የመግዛት የህወሓት ትልቁ አጀንዳ አካል መሆኑን ያሳያል።
    5. እራሱን በዘር ያደራጀዉና ኢትዮጰያ ዉስጥ ያለዉ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ አደረጃጀት ከዚሁ እሱ ከተደራጀበት የዘር አደረጃጀት ዉጭ እንዲሆን በፍጹም የማይፈቅደዉ የወያኔ አገዛዝ፤ መጣፊያው ሲያጥረውና ወደ ማይቀረው ውድቀቱ ሲያመራ፤ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል እንዳለችው አህያ አገራችን ኢትዮጵያን በቀላሉ ወደማትወጣዉ የዘዉግ ግጭት ዉስጥ አስገብቶ ዘመናት ያስቆጠረዉ አንድነቷ እንዲፈረስ በትጋት እየሠራ መሆኑን ያሳያል።
    6. ከመለስ ዜናዊ ሞት ወዲህ ህወሓት ከሁሉን ጠቅላይ (totalitarian) አገዛዝ ወደ ፋሽስታዊ ቡድንነት ያሽቆለቆለ መሆኑን አርበኞች ግንቦት 7 ተገንዝቧል። ህወሓት ዘረኛ፣ ጠቅላይና ፈላጭ ቆራጭ ጨቌኝ በመሆኑ ፋሽስት ብለነዋል። ሆኖም በታሪክ የሚታወቁ ፋሺስታዊ አገዛዞች ከፍተኛ ብሄራዊ ስሜት የነበራቸው ሲሆን የህወሓት ፋሽስታዊ አገዛዝ ግን ብሔራው ስሜት አልባ መሆኑ ልዩ እና የበለጠ አደገኛ ያደርገዋል። ይህ ፋሽስታዊ ቡድን የህወሓት መሪዎችንና ጥቂት ሌሎች አጫፋሪዎቻቸውን የያዘ ለጊዜው አስተባባሪ መሪ የሌለው ሆኖም ግን የጦር ሠራዊትን፣ የስለላ መዋቅሩንና ፓሊስን ተቆጣጥሮ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያን እየገዛ ያለው ይህ አስኳል የለሽ ፋሽስታዊ ቡድን መሆኑ እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን አርበኞች ግንቦት 7 ተገንዝቧል። ይህ ፋሽስታዊ ቡድን ተደላድሎ መሪ እንዲፈጥር ከተፈቀደለት አገራችንን የከፋ መከራ ውስጥ ሊከታት እንደሚችል ግንዛቤ ተወስዷል።
    ከላይ በአጭሩ ከተራ ቁጥ 1 እስከ 6 የተዘረዘሩትን በማገናዘብ በግንቦት 2007 ሊደረግ የታቀደውን አምስተኛው ዙር ሀገር አቀፍ የሴራ ምርጫን በተመለከተ የአርበኞች ግንቦት 7 አመራር ውሳኔዎችን አስተላልፎ ከዚህ የሚከተሉት ጥሪዎችን ለኢትዮጵያ ሕዝብ አቅርቧል።
    1. በምርጫ 2007 መሳተፍ ለዲሞክራሲያዊ ለውጥ ሁኔታዎችን ከማመቻቸት ይልቅ ፋሽስታዊውን ቡድን የሚያጠናክርና የኢትዮጵያን ሕዝብ የወደፊት ዕድል የሚገድል በመሆኑ፣ ለፍትህ፣ ለነፃነት፤ ለዲሞክራሲና ለአገር አንድነት ግድ ያላቸው ወገኖች ሁሉ ከአሁኑ ከዚህ የይስሙላ ምርጫ ዉጭ ዓይኖቻቸውንና ሙሉ ጉልበታቸዉን በሌሎች የኢትዮጵያን ሕዝብ ነፃነት በሚያፋጥኑ አማራጮች ላይ እንዲያሳርፉ ጥሪ ያደርጋል። አርበኞች ግንቦት 7 የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዚህ ዓይን ያወጣ የሴራ ምርጫ ይልቅ መብቱን፤ ነፃነቱንና እኩልነቱን በሚያፋጥኑለት በሕዝባዊ እምቢተኝነትና በሕዝባዊ አመፅ የትግል አመራጮች ላይ እንዲሳትፍ ለመላው ያገሪቱ ሕዝብ ጥሪ ያስተላልፋል። ህወሓት ማኅበረሰባችንን ለመከፋፈልና ለማባላት የሚያደርገውን እኩይ ሴራ በጋራ እንድናከሽፈው ወገናዊ ጥሪ ያስተላልፋል፤ “አንከፋፈልም፤ ተከፋፍለንም አንጠቃም“ እንበል ይላል::
    2. ህወሓትን ማስወገድ የሚቻለው በሕዝባዊ እምቢተኝነትና በሕዝባዊ አመጽ በመሆኑ፤ ከሁለቱ አንዱንም አለመያዝ ሌላ ሰው ታግሎ ነፃነቴን ያቀዳጀኝ እንደማለት የሚቆጠር በመሆኑ፤ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በአፋጣኝ ከእነዚህ ሁለት የትግል ዘርፎች ዉስጥ የተሻለ አስተዋጽኦ አበረክታለሁ በሚለው የትግል ዘርፍ ውስጥ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ ያቀርባል።
    3. አርበኞች ግንቦት 7፣ በሁለቱም የትግል ዘርፎች ድርጅታዊ መዋቅሩን እያሰፋና ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በመተባበር በሕዝባዊ እምቢተኝነትና በሕዝባዊ አመጽ ህወሓትን ከስልጣን ለማስወገድ አቅዶ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ኢትዮጵያዊያን በስፋት እንዲቀላቀሉት፤ በኅብረት እንድንቆም እና የህወሓትን ውድቀትና የኢትዮጵያን ትንሳኤ እንድናፋጥን ጥሪ ያደርጋል::
    4. ያለንን አቅም በሙሉ ህወሓትን በማስወገድ ላይ ካዋልነው አንድ ጠንክር ያለ ሕዝባዊ አመጽ አገዛዙን ሊያፍረክርክው የሚችል በመሆኑ፤ በአንድ ወይም በሌላ መንገድ ከምርጫ ጋር ለተያያዙ ሥራዎች ሊውል ታስቦ የነበረው የሰው ኃይል፣ ጊዜ፣ ገንዘብና እውቀት ለሕዝባዊ አብዮት መቀስቀሻነት እንዲውል ጥሪ ያደርጋል።
    5. በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንም በ2007 ምርጫ ላይ ጊዜና ንብረት ከማባከን ይልቅ በአንድ ልብ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሕዝባዊ አብዮት መቀስቀስ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪ ያደርጋል። ከሁሉም ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች የተውጣጣ አካል የዚህን ጥሪ ተፈፃሚነት እንዲከታተል ቢደረግ ይበልጥ ውጤታማ ይሆናል ብሎ ያምናል።
    ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!
    አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ

    አንድ አባት የልጃቸውን የሙት አመት በማክበራቸው ታሰሩ

    በምእራብ ሸዋ አንድ አባት የልጃቸውን የሙት አመት በማክበራቸው መታሰራቸው ታወቀ
    የካቲት ፮(ስድስት) ቀን፳፻፯ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በምእራብ ሸዋ ዞን በአቡነ ግንደበረት ወረዳ በመንዲዳ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ ባልቻ፣ በፌደራል ፖሊሶች በግፍ የተገደለባቸውን ደሜ ባልቻ የተባለውን ልጃቸውን የሙት አመት በመዘከራቸው፣ ለምን ይህን አደረጉ በሚል እርሳቸውና ሌሎች 10 ወጣቶች ባለፈው ሰኞ ተይዘው መታሰራቸው ታውቋል።
    አቶ ባልቻ የልጃቸው ገዳዮች እንዲያዙ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ ቢቆዩም አልተሳካላቸውም። የልጃቸውን ፎቶ ይዘው ፖሊስ ጣቢያ አካባቢ ሲያለቅሱ መታየታቸውን የገለጹት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ የአካባቢውን ሰዎች ሰብስበው ለልጃቸው በማልቀስ ላይ ነበሩ። በስፍራው የተገኙ ከ10 ያላነሱ የሟች ጓደኞች ተይዘው መታሰራቸውንና አመጽ በመቀስቀስ ወንጀል መከሰሳቸው ታውቋል።
    አቶ ባልቻ የልጃቸው ገዳይ የሆነው የፌደራል ፖሊስ አባል እንዲያዝ ለወራት ከደከሙና ተስፋ ካጡ በሁዋላ የመጨረሻውን የማስታወሻ ዝግጅት ማዘጋጀታቸው ታውቋል። ተማሪ ደሜ ባልቻ የ12ኛ ክፍል ትምህርትን ማጠናቀቁን ተከትሎ ፣ የመሸኛ ዝግጅት በሚደረግበት ወቅት በፌደራል ፖሊሶች መገደሉ መዘገቡ ይታወቃል።
    በጉዳዩ ዙሪያ የወረዳውን ፖሊስ አስተያየት ለማግነት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

    Friday, 13 February 2015

    FreeZone9Bloggers!!!!!!!

    Ban Ki-moon’s silence on Ethiopian Bloggers Case

    February 13, 2015

    Amid UN Free Press Talk, Ban Still Silent on Zone 9 Bloggers, Kaye at IPI

    by Matthew Russell Lee
    UNITED NATIONS, February 12 — Amid news that Egypt has released two Al Jazeera journalists MohammedOpen letter to Mr. Ban Ki-moon, Secretary General United Nations Fahmy and Baher Mohammed on bail, statements are churning out from all corners. UN Secretary General Ban Ki-moon may have one — but he should still explain his silence while in Ethiopia for the recent African Union summit about the terrorism trial of that country’s Zone 9 Bloggers.
    The Free UN Coalition for Access has been asking Ban’s UN, and those who pass through it, about #FreeZone9Bloggers, as it asked about Peter Greste and his colleagues, for example here.
    But the UN in New York, and the UN in Addis Ababa, have been silent.
    On February 12 across First Avenue from the UN there was a panel discussion on protection of journalists at the International Peace Institute. Al Jazeera’s Gabriel Elizondo spoke.
    Inner City Press ran across First Avenue and posed a question: does the UN system do for independent journalists and bloggers what it does for corporate or state media?
    The panelist who answered was David Kaye, UN Special Rapporteur on the Promotion and Protection of the Right to Freedom of Opinion and Expression. Kaye said, “As an independent journalist, it’s good to see you here. From different perspectives, I think that’s right. Sometimes the UN can do so loudly and publicly. Some situation might call for a little bit more of a quieter engagement.”
    Rapporteur Kaye said that “from the OHCHR perspective, we have different tools. Our first tool is to communicate with governments on the quiet side, send them allegation letters or urgent appeals, Zone 9 Bloggers being a good example of that.
    If we don’t get a response, to issue press releases, to call out bad behavior. I agree with the tenor or your comment — we should be out there calling out the bad behavior at the moment that it happens, quietly or more publicly. Article 19 is not written to protect only journalists, it protects everyone’s right to seek, receive and impart information.”
    The other panelists were Bård Glad Pedersen, Deputy Minister of Foreign Affairs of Norway, Agnes Callamard, Director of the Global Freedom of Expression and Information Project at Columbia University and former Executive Director of Article 19, Matthew Rosenberg, Foreign Correspondent of the New York Times (with interesting stories of Afghanistan but who declined to discuss the NYT’s coverage of Iraq before the US invasion) and Judith Matloff of Columbia University Graduate School of Journalism. There will be video.
    Back on January 30 when the UN held a “Social Media Summit,” it concluded with a panel about trends, from mobile to analytics to video and Facebook’s acquisition of Snapchat.
    But what about the UN defending or at least speaking up for freedom of expression on the Internet?
    Earlier on January 30, Inner City Press for the Free UN Coalition for Access asked Secretary General Ban Ki-moon’s spokesman Stephane Dujarric why Ban while in Ethiopia for the African Union summit had not raised the terrorism charges brought against the Zone 9 Bloggers. Video here.
    Dujarric said Ban has spoken elsewhere about freedom of expression in Africa, and that the (other) contents of his AU speech were interesting.
    So Inner City Press went to the #SocialUN final panel and asked, does the UN do enough to speak up for freedom in social media? One of the panelists had just finished praising high tech in Qatar. What about arrests for insulting the leader? What about Nabeel Rajab in Bahrain? Video here.
    Panelist Hayes Brown of BuzzFeed, who advised and practices Be a Person on Twitter, including baking and (good) jokes, said it is hard for the UN, since it has member states that pay its bills. He said he agreed about bloggers in Ethiopia but wasn’t sure what the UN could do, beyond speaking up.
    Well, as to the Zone 9 Bloggers, the UN has yet to speak up. That would be a start.
    Panelist Liz Borod Wight, who moderator Sree Sreenivasan marveled is paid to do Instagram for the BBC, cites those who tweeted #JeSuisCharlie and said those who have freedom of expression should use it.
    Panelist Adam Glenn from CUNY Journalism School said, hoping not to offend the hosts the UN, that the UN should ensure that all of its staff have training and can tweet.
    Inner City Press and FUNCA note, for example, that a UN staffer in South Sudan abruptly stopped tweeting after she tweeted this: “#breaking Lou Nuer youth are mobilising in big numbers leaving #Akobo town empty heading towards Dengjok #Southsudan.”
    As Inner City Press reported at the time, after Mathilde Kaalund-Jørgensen raised this alarm, the tweet and her Twitter account profile both disappeared. So much for Rights Up Front.
    At the end of the panel a UN staffer took the floor to acknowledge that UN staff cannot tweet what they think. But can’t Ban Ki-moon say what he thinks? Or doesn’t he think it? We’ll have more on this.
    source: ECADF

    Thursday, 12 February 2015

    የእሥር ማዘዣ በመዉጣቱ አቶ ጸጋዬ አላምረው አገር ለቀው ተሰደዱ!!

    February 11th, 2015
    የአንድነት ፓርቲ ምክትል አፈጉባኤ የሆኑትና በቅርቡ ሰማያዊ ፓርቲ የተቀላቀሉት አቶ ጸጋዬ አላምረው፣ ከወያኔ የፀረ-ሽብር ግብረ ኅይል እንዲታሰሩ የማዘዣ ወረቀት በመዉጣቱ፣ ለተወሰነ ቀናት አገር ቤት ራሳቸውን ሰዉረውከቆዩ በኋላ፣ በአሁኑ ጊዜ ከኢትዮጵያ ዉጭ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
    አቶ ጸጋዬ የአንድነት ፓርቲ የፋይናንስ ሃላፊ ሆነው የሰሩ ሲሆን፣ አቶ ሃብታሙ አያሌው ከታሰሩ በኋላ የመኢአድ አመቻች ኮሚቴ ዋሃ ሰብሳቢ ሆነው ሰርተዋል።፣ ሕወሃቶች መሰናክል ፈጠርበት እንጂ በመኢአድ እና በአንድነት መካከል ዉህደቱ ጫፍፍ እንዲደርስ፣ ቁልፍ ሚና ከተጫወቱ የአመራር አባላት መካከል አንዱ ነበሩ። የአንድነት ፓርቲ ያደርግ በነበረው የምርጫ ዘመቻም፣ የምርጫ ኮሚቴ አባል በመሆን ትልቅ ድርጅታዊ ሥራ ይሰሩም ነበር።
    የአንድነት ፓርቲ በአዲስ አበባ ጠርቶት በነበረው ሰልፍ ፣ የሕወሃት ታጥቂዎች በሰላማዊ ዜጎችን ላይ ኢሰባአዊ የሆነ ከፍተኛ ድብደባ በፈጸሙበት ወቅት፣ በአካል ከተጎዱት ወገኖች መካከል አንዱ አቶ ጸጋዬ ነበሩ። ከስድስት ወራት በፊትም በግንቦት ወር 2006 ዓ.ም፣ አንድነት እና መኢአድ የቅድመ ዉህደት ፊርማ በፈረሙበት ጊዜም፣ የአገዛዙ ካድሬዎች ስብሰባዉ ለመረበሽ በሞከሩበት ወቅት ተፈንክተው ትልቅ ጉዳት ደሮባቸውም ነበር።
    ሕወሃቶች በአቶ ጸጋዬ ላይ ያነጣጠሩት፣ በርካታ የአንድነት አባላትን ይዘው አቶ ፀጋዬ ሰማያዊን ከተቀላቀሉ በኋላ ሲሆን፣ ዋና ክስ አድርገው የወሰዱትም “አንድነት ፓርቲ የገንዘብ እርዳታ ከሽብርተኞች ይቀበላል፣ የሚቀበለዉም በአቶ ጸጋዬ አላምረው በኩል ነበር” የሚል እንደሆነ ታውቋል። ሕወሃቶች በሚቆጣጠሩት ኢቲቪና ራዲዮ ፋና ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ በአንድነት ላአይ የጅመሩ ሲሆን፣ እነ ትግስቱ አወሉንም በሜዲያ፣ የአቶ ጸጋዬ አላምረዉን ስም እየጠሩ “ገንዘብ ተቀባይ እርሱ ነበር” እያሉም እንዲናገሩ እያደረጓቸው ነው።
    የአንድነት ፓርቲ በዉጭ አገር ካሉ ኢትዮጵያዊያን ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ያገኝ እንደነበረ ይታወቃል። በዉጭ ያሉ የአንድነት ድጋፍ ድርጅቶችም፣ ከቅንጅት ጊዜ ጀምሮ በሰማዊ ትግል የሚያምኑ እንደመሆናቸው፣ በነርሱ በኩል ተሰብስቦ የሚላክን ገንዘብ ከሽብርተኞች እንደመጣ አድርጎ መቁጠር በሕግ፣ በሞራልም በአሰራር ተቀበያነት እንደሌላው የድጋፍ ድርጅቱ አባላት ይናገራሉ።
    10502165_813527682075480_8666019553634494465_n source: abugidainfo.com

    Monday, 9 February 2015

    Ethiopia refuses allow access to imprisoned British citizen

    Ethiopia has refused to allow a delegation of parliamentarians to visit a British dissident facing the death penalty in the African country. Andy Tsege, who is the secretary-general of a banned Ethiopian opposition movement, was sentenced to death at a trial held in his absence in 2009. He was travelling from Dubai to Eritrea last June when he disappeared during a stopover in Yemen, in what campaigners regard as a politically motivated kidnapping. Weeks later, he emerged in detention in Ethiopia.

    source: http://ecadforum.com/2015/02/08/ethiopia-refuses-allow-access-to-imprisoned-british-citizen/

    The real hero sits in unknown jail on his Birthday !!!!!





    My birthday wish for you and for all prisoners of 
    conscience behind  bars in Ethiopia are released!!! Happy Birthday  to Andargachew Tsege (Ethiopians Mandela) !!!!!

    09/02/2015