Sunday, 25 January 2015

ከእናንተ ከዳኞቹና የሞት ፍርድ እንድትበይኑብኝ ካዘዛቹ ሰው ይልቅ እኔ ፍርድ ተቀባይ የዛሬ ወንጀለኛ የነገ ባለታሪክ ነኝ።

                                                                                                                                                                       
                                                                                                                                                                       After i saw about today's brutality committed by Ethiopian regime agenist  peaceful rally called by Ethiopia’s one of major opposition Unity for Democracy and Justice Party UDJ (Andinet). i decided to share with u what i read yesterday. 


መንግስቱ ነዋይ መጋቢት ፩፱ ፩፱፭፫(19 1953)የሞት ፊርድ ከተፈረደባቸው በኋላ የተናገሩት ነበር
ከእናንተ ከዳኞቹና የሞት ፍርድ እንድትበይኑብኝ ካዘዛቹ ሰው ይልቅ እኔ ፍርድ ተቀባይ የዛሬ ወንጀለኛ የነገ ባለታሪክ ነኝ።
እናንት ዳኞች የበየናችሁብኝን የሞት ፍርድ ያለ ይግባኝ ተቀበያለሁ። ይግባኝ ብዬ ጉዳዩን የሚመለከተልኝ የኢትዮጰያ ህዝብ ቢሆን ኖሮ ይግባኝ ማለት በፈለኩኝ ነበር። ነገር ግን ይህ አንደማይሆን ኣውቃለውና በይግባኝ የኣፄ ኃ/ ስላሴን ፊት ማየት ኣልፈቅድም።
በእግዚኣብሄር ስም ተሰይማችሁ ከተቀመጣችሁበት የፍርድ ወንበር ላይ ከመቀመጣጭሁ በፊት በእኔ ላይ የምትሰጡትን የዛሬውን ፍርድ ታውቁት እንደነበር ሳስብና ፍርድ እስከዚህ መርከሱን ስታዘብ ሃዘኔ ይበዛል። ለኢትዮጰያ ህዝብ ኣንድነት ነፃነትና አርምጃ የተነሳሁ ወዳጅ ነኝ አንጅ ለማፋጀት የተነሳሁ ወንበዴ ኣይደለሁም። ይህንን ማድረግ ፈልጌ ቢሆን ኖሮ ማንም የማይወዳደረው ሰራዊት አና መሳሪያ ሳላጣ ዛሬ አዚህ ከአናንተ ፊት ባልቆምኩኝ ነበር።
    እኔ ከኣፄ ኃ/ ስላሴ ድንክ ውሾች ያነሰ ደሞዝ የሚያገኙ ሁለት የተራቡ ወታደሮችን ኣጣልቼ ለማደባደብና ኣገር ለማፍረስ ኣለመምጣቴን የሚያረጋግጥልኝ አናንተ በትእዛዝ ያገኛችሁትን ፍርድ ለመቀበል እዚህ መቆሜ ነው። ከእኔ በፊት በግፍ የፈሰሰው ንፁህ ኢትዮጰያን ደም ብዙ ነው። በኣፄ ኃ/ ስላሴ ዘመነ መንግስት ግፍ ሸልማት በመሆኑ አኔ ለመሞት የመጀመሪያው ኣልሆንም። ስልጣን ኣላፊ ጠፊ ነው።

      እናንተ ዛሬ ከጨበጣችሁት በላይ ስልጣን ነበረኝ። ሀብትም ኣላጣሁም። ነገር ግን ህዝብ የሚበደልበት ስልጣንና ደሃ የማይካፈለው ሀብት ስላልፈለግሁ ሁሉንም ትቼ ተነሳሁ። አሁንም እሞታለሁ።ሰው ሞትን ይሽሻል አኔ ግን በደስታ ወደሞት እሄዳለሁ። ለኢትዮጰያ ህዝብ ታላቅነት ቀድመውኝ መስዋት የሆኑትን ኣብረውኝ ተነስተው የነበሩትን ጀግኖች ወንድሞቼን ለመገናኝት ናፍቄኣለሁ። የጀመርኩት ስራ ቀላል ኣይደለም። ኣልተሽነፍኩም።

    ወገኔ የሆነው መላው የኢትዮጲያ ህዝብ የጀመርኩለትን ስራ በቅርቡ ጊዜ ውስጥ ፈጽሞ እራሱን በራሱ አንደሚጠቅም ኣልጠራጠርም። ከሁሉ በበለጠ የሚያስደስተኝ ለኢትዮጲያ ህዝብ ልሰራለት ካሰብኩኣቸው ስራዎች ውስጥ ኣንዱ የኢትዮጵያ ወታደር ዋጋና ክብር ከፍ ማድረግ ሲሆን ይህ ሃሳቤ ህይወቴ ከማለፉ በፊት ማየቴ ነው። ዛሬ መኖራችሁን በማየቴ ነገ መሞታችሁን እረስታችሁ ኣሜን ብላችሁ ቀናችሁን በማሰተላለፍ በመገደዳቹ በእኔ ላይ ሳትፈርዱ በራሳቹሁ ላይ መፍረዳችሁን ኣላስተዋላችሁም። እኔ የተነሳሁት ከትክክለኛው ህግና ከህሊናችሁ ውጭ ለመፍረድ እንዳትገደዱ ለማድረግ ነበር። በኣጭሩ በእኔ ላይ ለመፍረድ የቸኮላችሁትን ያህል ኣስር አና ኣስራ ኣምስት ኣመት በቀጠሮ የምታጉላሉትን ህዝብ ጉዳይ አንደዚህ ፈጥናቹህ ብትመለከቱትና ብትሽኙት ኖሮ የእኔ መነሳት ባላስፈለገ ነበር።

       ከእናንት ከዳኞቹ አና የሞት ፍርድ አንድትበይኑብኝ ካዘዛችሁ ይልቅ እኔ ፍርድ ተቀባይ የዛሬ ወንጀለኛ የነገ ባለታሪክ ንኝ። እኔ ከጓደኞቼ መካከል በሂወት መቆየትና ለናንተ ፍርድ መብቃት የመመዘኑን ፍርድ ለመጪው ትውልድ የሚያሳይ ይሆናል።

   ዋ!ዋ!ዋ ለእናንተና ለገዢኣችሁ። የኢትዮጵያ ህዝብ ሃሳቤ በዝርዝር ገብቶት በኣንድነት በሚነሳበት ጊዜ የሚወርድባቹ መኣት ኣስቃቂ ይሆናል። በተለይ የዓፄ ኃ/ ስላሴ የግፍ መንግስት ባለኣደራዎች ሆነው ድሀውን ህዝብ ሲገሽልጡ ከነበሩት መኮንን ሀ/ወልድ እና ገ/ወልድ አንግዳወርቅን ከመሳሰሉት በመንፈስ የታሰሩ በስጋ የኮሰሱ መዠገሮች መካከል ጢቂቶቹን ገሸሽ ማድረጌን ሳስታወስና የተረፉትንም ፍጻሜአቸዉን በሚበድሉት በኢትዮጱያ ህዝብ እጅ ላይ መውድቅ ሲሰማኝ ደስ ይለኛል።
     ከዛሬ ፬፬(44) ኣመት በፊት ነበር በኣንድ ሰው ኣንደበት ነገር ግን የሚሊዮኖች ጥያቄ የሆነው የፍትሕ ጥያቄ ተደጋጋሚ ኣገዛዞች ውድቀትና የኣምባገነኖች የእዣቸውን ማግኘት ቢያስክትልም አስከዘሬ ምላሽ ሳያገኝ ዛም በሃገራችን ከኣድማስ ኣድማስ በሚሊዮኖች ሲስተጋባ ይኖራል።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

No comments:

Post a Comment