የጅንካ ነዋሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ
መስከረም ፲፭(አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ኦሞ ዞን በጅንካ ከተማ በአይነቱ ልዩ ነው ተባለ የተቃውሞ ሰልፍ መደረጉን የአካባቢው ምንቾች ገልጸዋል።
የተቃውሞ ሰልፉ የተደረገው ከጅንካ ከተማ ወደ ሃና በመጓዝ ላይ የነበረ አንድ ሰራተኛ መገደሉን ተከትሎ ነው። ሃና አዲሱ የስኳር ፋብሪካ ግንባታ የሚካሄድበት ቦታ ሲሆን፣ ግድያውን የፈጸሙትም የስኳር ልማቱ ከቀያቸው ያፈናቀላቸው የሙርሲ ብሄረሰብ አባላት ሳይሆኑ እንደማይቀር ይገመታል። የጅንካ ተወላጁ ኡመር ንጋቱ አይሱዚ መኪና ይዞ ለስራ ከሄደ በሁዋላ ሲመለስ በጥይት ተደብድቦ እንደተገደለ ታውቋል። ድርጊቱን ተከትሎ የከተማው ነዋሪዎች ” ቀጣዩ ሟች ማን ይሆን፣ የጅንካ ህዝብ መብት የለውም ወይ? ለህይወታችን እንሰጋለን፣ ዝም አንልም” የሚሉ መፈክሮችን ይዘው ተቃውሞቸውን አሰምተዋል። የከተማው ነዋሪዎች ከዚህ ቀደም ተደጋጋሚ ግድያዎች ቢፈጸሙም በመንግስት በኩል የተወሰደ እርምጃ አለመኖሩን የከተማው ነዋሪዎች ይናገራሉ።
በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው የአንድነት ፓርቲ አካባቢው ተወካይ አቶ ስለሺ ጌታቸው መንግስት የአካባቢውን አርብቶአደሮች ሳያማክር በማናለብኝነት የጀመረው የስኳር ፕሮጀክት ለዜጎች ህይወት መጥፋት ምክንያት እየሆነ መምጣቱን ይናገራሉ።
የአሜሪካ ኮንግረስ በዞኑ የሚካሄደው ስራ በአርብቶአደሮችን ህይወት ላይ ችግር የሚፈጥር መሆኑ ከተረጋጋጠ ለኢትዮጵያ የሚሰጠው እርዳታ እንዲቋረጥ ወስኖ ነበር። የተለያዩ አለማቀፍ ድርጅቶችም የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በአርብቶ አደሩ ህዝብ ላይ ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ መውሰዳቸውን የሚያሳይ ሪፖርት ማውጣታቸው ይታወቃል።
Thursday, 25 September 2014
Former Gambella regional government President Okello Akway, 52, who was charged with terrorism and plot to take over the Gambella Regional State with an attempt of establishing an autonomous state of Gambella by overthrowing the government in June 2014, has been beaten by prison guards for allegedly entering a fight with another prisoner last week.
He was abducted from South Sudan by Ethiopian securities.
He was reportedly forced to sit in the sunshine after the beating.
Okello is being detained in Kilinto prison in the outskirts of Addis Abeba. He reportedly entered the minor fight with another prisoner who was allegedly placed in the prison as a mole and later accused the ex-president.
Okello administered the region from 2003 to 2004 before he fled the country in 2005.
http://news.bbc.co.uk/2/hi/programmes/newsnight/9556288 i found this link in my archive and decided to share with u in case u haven't seen this, enjoy the truth ....... how Ethiopia using AID as weapon of oppression.
በመላ ሃገሪቱ የተነደፈው የተቀናጀ የጐልማሶች ትምህርት ስኬታማ አይደለም ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሺፈራው ሽጉጤ ተናገሩ፡፡
በመላ አገሪቱ ከ40 ሚሊዮን በላይ መጻፍና ማንበብ የማይችሉ ወጣት እና ጎልማሶች አሉ ያሉት አቶ ሺፈራው ፤ ይህንን የትምህርት እድል ያለገኙ ወጣቶች እና ጎልማሶች አማራጭ ትምህርት እንዲያገኙ የተደረገው ሙከራ አፈፃጸሙ ከዜሮ በታች ነው ብለዋል።
በኢህአዴግ የእቅድ ትውውቅ መድረክ ላይ እንደቀረበው በጎልማሶች የትምህርት አቀራረብ አማራ 0.9፣ ኦሮምያ ፣ 0.71 ፣ደቡብ 0.63 ፣ትግራይ 2.9 በመቶ ፈጽመዋል።
ኢህአዴግ ደርግን ባመሰገነበት የምክር ቤት ውይይት ፤ "ለምን ህዝቡን በዘመቻ አናስተምርም?" ተብሎ ለተነሳው ጥያቄ ፤ "ኢህአዴግ የተፈጠረው ከዘመቻ ነው፡፡ ወጣቱ ሌላ የትጥቅ ትግል እንዲያደራጅ መሳሪያ አንሳ ብለን አንልክም" የሚል መልስ ተሰጥቷል።
"በገጠር መሬት አልባ የሆነው ወጣት ፤ በከተማ ስራ አጥ የሆነው የተማረው ሃይል በአንድነት ተገናኝቶ ሊፈጥረው የሚችለው አደጋ ሰፊ ነው፤ ይህ ስጋት ሳይሆን ሃቅ ነው" ሲሉ አቶ በረከት እና አቶ አበይ ፅሃየ በመደጋገፍ እየተናገሩ ጎልማሶችን በዘመቻ ለማስተማር የቀረበውን ሃሳብ ውድቅ አድርገዋል፡፡ አቶ በረከት እንዲህ አይነቱን አስተያየት የሚያቀርቡት በትጥቅ ትግሉ ወቅት ያልነበሩ አመራሮች ናቸው በሚል አዳዲስ የኢህአዴግን አመራሮች መወረፋቸው ከኢህአዴግ የደረሰን መረጃ አመልክቷል።

Friday, 5 September 2014
ወጣቶች እየመጡ ነው!!!
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ “ወጣት፤ የነብር ጣት!” በሚል ርዕስ ጥር 26 ቀን 2003 ዓ.ም. በቁጥር 142 ባወጣው ርዕሰ አንቀጹ “ወጣት በነብር ጣት መመሰል ያንሰው እንደሆን እንጂ አይበዛበትም።
የኢትዮጵያም ወጣት የነብር ጣት ሆኖ ያውቃል … አሁንም ነው” ብሎ ነበር። በዚያ ጽሁፍ እና በሌሎችም አጋጣሚዎች በተደጋጋሚ እንዳብራራው ግንቦት 7 በወጣቱ ችሎታና ተነሳሽነት ላይ ከፍተኛ እምነት አለው። የወደፊቷ ብቻ ሳይሆን የአሁኗ ኢትዮጵያም የወጣቱ መሆኗን ግንቦት 7 ያምናል። ግንቦት 7: ወጣቶችን ለማሳተፍና ለመሪነት ለማብቃት የሚጥር፤ ራሱም በወጣቶች የተገነባ ድርጅት ነው።

ኢትዮጵያ አገራችንና ሕዝቧን ከወያኔ አደንቋሪ አገዛዝ ለማላቀቅ ቆርጠው የተነሱ ወጣቶች እየበረከቱ መምጣታቸው የግንቦት 7 እምነትን የሚያጠናክር ሆኗል። አምባገነኑን የወያኔ አገዛዝን በትጥቅ ትግል መፋለም ይኖርብናል ብለው የተነሱ ወጣቶች በከፍተኛ ፍጥነት እየተደራጁ መሆናቸውን እንሰማለን። እድሜያቸው በሀያዎችና በሠላሳዎች መጀመሪያ ላይ የሚገኙ ለጋ ወጣቶች ናቸው የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል የሚባለውን የትግል ድርጅትን የፈጠሩት። ይህ ኃይል ሰሞኑን ለአራተኛ ጊዜ እጩዎችን አሰልጥኖ ማስመረቁን በተለያዩ ሚዲያዎች ባሰራጨው ዜና ገልጿል።
በተመሳሳይም የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትህዴን) በሺህ የሚቆጠሩ ወጣቶችን አሰልጥኖ ለወሳኝ ትግል ዝግጁ መሆኑን አብስሯል። የኢትዮጵያ አርበኖች ግንባርም በወጣቶች የተሞላ ለትግል የተዘጋጀ ድርጅት ነው። ሌሎችም አሉ። እነዚህን ድርጅቶች ድርጅት ያደረጓቸው ወጣቶች ናቸው።
በሰላማዊ የትግል ዘርፍም ወያኔ የሚያደርስባቸው እስር፣ ዱላና እንግልት እየተቋቋሙ በየእለቱ እየበረቱ የመጡ ጀግኖች ወጣቶችን ማየት ችለናል። ወያኔ፣ በማኅበረሰቡ ውስጥ ብሩህ አዕምሮና ልብ ያላቸው ወጣቶችን አስሬ፣ አሸማቅቄ ጨረስኩ ሲል ከዚያ የባሱ እየፈለቁ ነው። በነፃነት ሲጽፉ የነበሩ እነ እስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታየ እና ርዕዮተ ዓለሙ በሀሰት ክስና ምስክር ሲታሰሩ ወያኔ ተስፋ እንዳደረገው ወጣቶች በፍርሃት ተሸማቀው ልሳኖቻቸውን አልዘጉም። እንዲያውም ከነሱ የባሱ፣ የበሰሉ ጦማርተኞች መጡ። ሰላማዊ ታጋዮቹ እነ አንዱ ዓለም አራጌና ናትናኤል መኮንንን ሲያስር ከእነሱ የበለጡ ወጣት ወንድና ሴት ታጋዮች መጡ። እስከ ድል ድረስ ይህ ዑደት ይቀጥላል፤ ኢትዮጵያ ወጣት ጀግኖችን ማፍራቷ አያቋርጥም።
ወያኔ “ኢህአዴግ” በሚባል ቀፎ በሰበሰባቸው አድርባይ ድርጅት ውስጥ የተሰባሰቡ ወጣቶችም ወደ ህሊናቸው እየተመለሱ፣ ድፍረት እያገኙና እየከዱት ነው። በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ምክንያቶች በወያኔ ድርጅቶች ውስጥ የገቡ ህሊና ያላቸው ወጣቶች “ምን እናርግ?” እያሉ ነው። ለእነዚህ ወገኖቻችን ግንቦት 7 አጭር ምላሽ አለው – “ከቻላችሁ ጥላችሁ ውጡና የነፃነት ትግሉን በይፋ ተቀላቀሉ፤ ካልቻላችሁ ኢህአዴግን ከውስጥ ሆናችሁ ውጉት፣ አዳክሙት፣ ግደሉት” ።
በሁሉም ረገድ በኢትዮጵያ ወጣት ላይ ያለ ተስፋን የሚያጠናክሩ ነገሮችን የምናስተውልበት ወቅት ላይ መሆናችን የሚያስደስት ነገር ነው። “እንዴት ልታገል? ከማን ጋር ልታገል?” የሚሉ ጥያቄዎች ምላሽ አግኝተዋል። ነፃነቱን የሚወድ ወጣት ሁሉ እንደ ፍላጎቱና ዝንባሌው የሚሳተፍበት መድረክ ተዘጋጅቶለታል።
ወያኔ፣ ወጣቱን ያህል የጎዳው የኢትዮጵያ የኅበረተሰብ ክፍል የለም። የህወሓት መሪዎች በወጣትነታቸው ዘመን “መብት ተነፈግን” ብለው ብረት አንስተዋል፤ የዛሬው ወጣት ግን እነሱ ያኔ የነበራቸውን እኩሌታ ያህል እንኳን መብት እንዳያገኝ አድርገዋል። የህወሓት ሁሉንም ጠቅልሎ የመግዛት ፍላጎት ወጣቱን መናገርም ሆነ መፃፍ ብቻ ሳይሆን ማሰብ እንኳን እንዳይችል ለማድረግ እየሞከረ ነው።
የኑሮ እድሎች የሚከፋፈሉት በዘርና በፓለቲካ ወገንተኝተኝነት በመሆኑ ከሁለቱም ያልሆነው ወጣት ኑሮው የተጎሳቆለ፤ የነገ ተስፋውም የጨለመ ሆኗል። ስደት የኢትዮጵያ ወጣት እጣ ፈንታ ሆኗል። ዛሬ የተማረውና ከተሜው ብቻ ሳይሆን በትምህርት ያልገፋውና በገጠር በግብርና የሚተዳደረውም ወጣት ስደተኛ ሆኗል። አረብ አገራት፣ ሱዳን፣ ኬኒያ፣ ደቡብ አፍሪቃ በኢትዮጵያውያን ወጣት ወንዶችና ሴቶች ተጨናንቀዋል። ወያኔ ወጣቱን በእድሜና በዝንባሌ ሳይሆን በዘር በማደራጀት የጎንደሩ ለባሌ፤ የሸዋው ለአሩሲ፤ የትግራዩ ለባህርዳር፣ የደሴው ለለቀምት ፈጽሞ ባዕድ እንዲሆን፤ በጥርጣሬም እንዲጠባበቅ፤ በሰበብ አስባቡም እንዲቆራቆስ አድርጓል። ወያኔ፣ የኢትዮጵያን ወጣት በኢትዮጵያ ወጣት ላይ እንዲዘምት አድርጓል።
ያም ሆኖ ግን የወያኔ ፋሺስታዊ የጥፋት ፕሮጀክት እየተናደ ነው። በተስፋና በወኔ የተሞሉ ከሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተውጣጡ ወጣቶች በበረሃዎችና በሜዳዎች ላይ በአንድነት ሲዘምሩ ስናይ የኢትዮጵያ ትንሳኤ ቅርብ መሆኑ ይሰማናል። አዎ!!! የኢትዮጵያ ወጣቶች ከየአቅጣጫው እየመጡ ነው። መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ህልማቸውን ያልማል፤ ዜማቸውን ያዜማል። ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ሁሌም አብሯቸው ነው። ኢትዮጵያ በወጣቶቿ ብርቱ ትግል ከአገዛዝ ነፃ ትወጣለች።

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከተናገሯቸው ንግግሮች ጥቂቶቹ፡
ሁሉንም ዜጎች በእኩልነት የምታስተናግድ፣ አንድነቷን የጠበቀች፣ እውነተኛ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመመሰረት እና በግንባር ቀደም መሰዋእት ለመሆን ግንቦት 7ን ተቀላቅያለሁ፤ ለድል ለመብቃትም ቆርጨ ተነስቻለሁ።
የዴሞክራሲ ስርአት በሀገራችን መመስረቱ አይቀሬ ነው! ትክሻ ለትክሻ ተደጋግፈን በጽናት በመታገል ከግብ እንደርሳለን።
ሁሉም ዜጎች በፍላጎታቸውና በምርጫቸው የመስራትና የመኖር ሰበአዊ ነጻነታቸው የወያኔም ሆነ ሌላ የፖለቲካ አሽከር አደግዳጊና ፍላጎት ፈጻሚ በመሆን የሚያገኙትን እርጥባን ሳይሆን፤ በዜግነታችን በሰውነታችን የታደልነው መብት መሆኑን የተቀበለ አዲስ ስርአት መመስረት የሁላችን ሃላፊነት ነው።
ነጻነቴን እመርጣለሁ ትላለህ? ወይስ የቤተሰብ ሃላፊነትን ምክንያት በማድረግ የምትወዳቸውን ልጆችህና ቤተሰቦችህን በባርነት ማኖርን ትቀበላለህ? ነጻነታችን እንዲህ አይነቱን አሰቃቂ ምርጫ ይዞብኝ መጥቷል። እኔ ግን ምንም እንኳን አማራጮቹ ስቃይን የሚያበዙ ቢሆኑም ወስኛለሁ…ኢትዮጵያ ለዘላለም ተከብራ ትኑር ብያለሁ…

ከአንዳርጋቸው ጽጌ መታስር በኋላ የወያኔ የአፈና ተቋም በአገር ውስጥ ያሉትን የተቃዋሚ መሪዎችን ማገት ቀጣይ ተግባሩ ሆኗል ፤ የአንድነት ፓርቲ ወጣት መሪዎች አቶ ሐብታሙ አያሌውና ዳንኤል ሺበሺ ማዕከላዊ ተጋዙ፣ የሰማያዊ ፓርቲው የሺዋስ አሰፋም ታስሯል...አሁን ደግሞ አብርሃ ደስታ ከፍተኛ ድብደባ ደርሶበት ወዴት እንድወስዱት አልታወቀም፤ እስሩ በዘመቻ መልክ ቀጥሏል ......ትግሉ ሁላችንም ተያይዘን ለነጻነት ድምጻችንን የምናሰማበት ወቅት ነው ...መከፋፈላችን የጠቀመው ይሄን አፋኝ ስራአት እድሜ እየስጠው ነው፤ ኢትዮጵያውያኖችም ቁጣችን ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ነው ....ትግሉ በየትኛውም አቅጣጫ ተፋፍሞ መቀጠል አልበት .....ለዚህ አፋኝ ስርአት ፋታ መስጠት አይገባም......ትግላችን ከሰላማዊ ሰልፍ ካፍ ባለ እና በተቀናጀ ምልክ መቀጠል አለበት....ኢትዮጵያን የመታደግ ጊዜው አሁን ነው!! ኢትዮጵያን እግዚአብሄር ይጠብቃት!!
• የከተማ አውቶቡስ ድርጅት 80 አውቶቡሶችን አቅርቧል
• ‹‹ምኒልክ ለኢትዮጵያ ምንም ካላበረከቱ ለምን ከእሳቸው ዘመን ጀምረን ዘመናዊ ኢትዮጵያ ብለን እንጠራለን?›› ሰልጣኞቹ
• ኦነግ በትግሉ ወቅት አልነበረም መባሉ በኦህዴድ ካድሬዎች ዘንድ መነጋገሪያ ሆኗል

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ከነሃሴ 27 ጀምረው በየ ትምህርት ቤቱ በፕላዝማ ስልጠና ጀምረዋል፡፡ ስልጠናውን በበላይነት የሚመራው የኢህአዴግ ጽ/ቤት መሆኑ ታውቋል፡፡ ሰልጣኞቹን ለማመላለስ ከአንበሳ የከተማ አውቶቡስ 80 አውቶቡሶችን ጠይቆ መውሰዱን ድርጅት ሰራተኛ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ የተለያዩ የኢህአዴግ አደረጃጀቶችን የወከሉ ካድሬዎችን ጨምሮ የሀይማኖት አባቶችም የሚገኙበት ሲሆን ለስልጠናው አበልን ጨምሮ፣ የከተማ አውቶቡስ፣ ትምህርት ቤትና ሌሎች የህዝብ ገንዘብ እየወጣ እንደሚገኝ ሰልጣኞቹ ገልጸዋል፡፡
በፕላዝማ የሚሰጠው ስልጠና በታሪክ ላይ ያተኮረ ሲሆን በተለይም አጼ ምኒልክ ከፍተኛ ጥፋት እንደፈጸሙና ለዛሬይቱ ኢትዮጵያ ይህ ነው የሚባል አስተዋጽኦ እንዳላበረከቱ መገለጹ ታውቋል፡፡ በተቃራኒው የኢህአዴግ አባላት ሳይቀሩ ‹‹በታሪክ አዲሲቱ ወይንም ዘመናዊ ኢትዮጵያ ብለን የምንማረው ከምኒልክ ዘመን ጀምሮ ያለውን ነው፡፡ ምኒልክ ምንም ካላበረከቱ ለምን ከእሳቸው ዘመን ጀምረን ዘመናዊ ኢትዮጵያ እያልን እንጠራለን?›› የሚል ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
ገዥው ፓርቲ አሸባሪ ብሎ የሚጠራቸውን ጨምሮ በሰላማዊ መንገድ የሚቃወሙት ፓርቲዎችም ወቀሳ የቀረበባቸው ሲሆን ኢህአዴግ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳበረከተ ተገልጾአል፡፡
ስልጠናው ላይ ሌሎች ፓርቲዎች የኢህአዴግን ያህል አስተዋጽኦ እንደሌላቸው በስፋት የተገለጸ ሲሆን ለአብነት ያህልም ‹‹ኦነግ ትግሉ ላይ አልነበረም›› መባሉ በኦህዴድ ካድሬዎች ዘንድ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡ አንድ ስልጠናው ላይ የሚገኝና ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ የኦህዴድ ካድሬ ‹‹የኢህአዴግን ታሪክ ለማግነን ሲባል የምናውቀውን ታሪክ ሁሉ እየካዱ ነው፡፡ ምንም አይነት የትግል ስልት ይከተል ረዥም የትግል ታሪክ ያለውን ድርጅት ትግሉ ላይ አልነበረም በማለት ከትዝብት ውጭ የሚያስገኘው ውጤት አይኖርም፡፡ የኦህዴድ አባል ብሆንም በመዋሸት ኦነግን ልታገለው አልችልም፡፡ ይህ ጉዳይ የመወያያ ርዕስ ሆኖ መቀረቡም የሚያስገርም ነው፡፡›› ሲል ሁኔታውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡

Subscribe to:
Posts (Atom)