Sunday, 16 October 2016

ሰበር_መረጃ አስቸኳይ የፋይናንስ አዋጅ ሊታወጅ እንደሆነ ተሰማ

ሰበር_መረጃ….አስቸኳይ የፋይናንስ አዋጅ ሊታወጅ እንደሆነ ተሰማየብሔራዊ ባንክ ውጭ ምንዛሪ ካዝና ባዶ ነው

October 16, 2016

የኢህአዴግ ጽ/ቤት በትርምስና የእርስ በእርስ ውንጀላ ላይ ነው። በውጪ እና በሀገር ውስጥ ኢንቬስተሮች ከኤክስፖርት ይገኝ የነበረው የውጭ ምንዛሪ በ5 ወራት ውስጥ በ71.1 በመቶ በመቀነሱ ለመጀመሪያ ጊዜ የ1.9 ቢሊዮን ዶላር የገቢ ውድቀት ታይቷል። ከተጠበቀው በታች በመቀነሱ ይሄንን የህዝብ አገልግሎት ሰጪ የሆኑ የትምህርት ቤት በጀት (የመምህራን ደሞዝን ጨምሮ)፣ የጤና አገልግሎት፣ ትራንስፖርት፣ ከፍተና ወጪ ያስከተለው የፖሊስ ሰራዊትና የወታደሮች ደሞዝ በዚህ የበጀት ቀውስ ምክንያት በመስተጓጎሉ አዲስ አዋጅ ማስፈለጉ ተሰምቷል።

ከሁሉም አስከፊ የሆነው ከቻይና ሌሎች አበዳሪዎች ለኢንቨስትመንስት ጉዳይ ተብሎ የተገኘው ብድር 16 ቢሊዮን ዶላር በመድረሱ በመጀመሪያው የክፍያ በ2016 አመት አስከፊ የፋይናንስ ቀውስ መገባቱ ምክንያት ሆኗል። ኢትዮጵያ በአሳሳቢ የዕዳ ሽክም ከአለም 11ኛ ሆናለች። ከዚህ ባለፈ ለውድቀቱ ተጨማሪ ምክንያት የሆነው እርዳታ ሰጪ ሀገሮች በየጊዜው የሚያስገኙት የበጀት ድጋፍ እየቀነሰ በመምጣትና ወደ ሰብዓዊ አስቸኳይ የምግብ ርዳታ ላይ ትኩረት በማድረጋቸው መሆኑም ጭምር ነው።
http://www.satenaw.com/amharic/archives/23331

Monday, 3 October 2016

የኢሬቻ በዓል ጭፍጨፋ

ፕሮፌሰር መስፉን ወ/ማሪያም
የኢሬቻ በዓል ጭፍጨፋ፡--- እንደሰው ያሳዝነኛል፤ ያሳፍረኛል፤ እንደኢትዮጵያዊ ዜጋ ያዋርደኛል፤ ያሳጣኛል፤ አለኝ የምለውን የጨዋነት ባህል፣ ይሉኝታና ክርስስቲያናዊ ሰብአዊነት ያጎድፍብኛል፤ ራቁቴን በዓለም ሕዝብ ፊት ያቆመኝ ይመስለኛል፡፡
ለሥልጣን ብዙ ሰዎች ሰዎችን አጫርሰዋል፤ ብዙ ንብረትን አውድመዋል፤ የብዙ ሕዝቦችን የእድገት እርምጃ አግደዋል፤ ወደኋላም መልሰዋል፤ ሞት እየቀጠፋቸው ሥልጣናቸው ባልወደዱት እጅ ገብቷል፡፡
ለሀብት ብዙ ሰዎች ሰዎችን አጫርሰዋል፤ ከሰው ልጅ ሕይወት፣ ከሰው ልጅ ምቾት ሀብት በልጦባቸው ጤንነታቸውን እያጡ በማያሸንፉት ሞት ተቀጥፈዋል፤ ከሰው ልጅ የበለጠባቸው ሀብት እንኳን ለነሱ ለልጆቻቸውም ሳይሆን ተዝረክርኮ ቀርቷል፡፡
የባለሥልጣንና የሀብታሞች ሎሌ በመሆን ወንድም ወንድሙንና እኅቱን ገድሎ፣ ጎረቤቶቹንና ወገኖቹን አስቀይሞ ከውርደት ኑሮ በቀር ክብርንና ኩራትን አያገኝም፤ የሠራውን ሥራ፣ ወንድሙን ወይም እኅቱን መግደሉን፣ ከእሱ በቀር የሚያውቀው የለም ይሆናል፤ ይህ አእምሮውም ውስጥ ልቡም ውስጥ የተለጠፈ እውቀት በመቃብርም ሆነ ከመቀብር ውጭ አይለየውም፤ ማናቸውንም ምቾት ይነሳዋል፡፡
መግደልም ሆነ ማስገደል የመጨረሻው የውድቀትና የጻዕር ምልክት ነው፤ ወይም የታቀደ የመጨረሻው እልቂት መጀመሪያ ነው፤ የተጠቂው ወገን ሲመርረው አጥቂው ካልጎመዘዘው፣ አጥቂው እስቲጎመዝዘው ድረስ የተጠቂው ምሬት ቋቅ እስቲለው ይቀጥላል፤ የተጠቂው ምሬት ቋቅ የሚያስደርግ ደረጃ ላይ ሲደርስ የአጥቂውም መጎምዘዝ ወደምሬት ያሸጋገራል፤ ትእግስት የጎደለው የአጥቂ ጉልበተኛ ምሬትና ቋቅ የሚል የተጠቂ ምሬት ሲጋጠሙ ውጤቱ እልቂት ነው፤ ጉልበተኛ ጉልበቱ እስቲሰበር የሞተ ኅሊና (እንጉርጉሮ ወይም አሁንም እንጉርጉሮ) በሚለው ግጥሜ በከፊል የሚከተለውን ብዬ ነበር፡---
ከሳሽ፣ ተከሳሽ፣ ዳኛ መሆን
እንዴት ይችላል መበየን?
ሲፍነው ግን ኅሊናውን፣
አይለይም ጨለማውን ከብርሃን!
ኅሊናውን የገደለ ሰው
ማን ሊቀረው? ምን ሊያቅተው?
የጉልበቱ መሣሪያ ነው፤
ጊዜ ጉልበቱን እስቲሰብረው!
እግዚአብሔር ከመጨካከን ፉክክር ይጠብቀን፡፡