ዳባት አመረረ ውጥረቱ አይሏል! ነገሩ ከቁጥጥር ውጪ እየሆነ ይገኛል። የጎንደር ህዝብ ተማሯል በወልቃይት ጠገዴ ዳንሻ አርማጮሆ ቃብቲያ የነበረው ቁጣ አሁን ወደ ዳባት እየዘመተ ነው፡፡ በዳባት የህዝቡ ምሬት አስፈሪ አድርጎታል፡፡ ተነቅሎ ሊወሰድ የነበረው አላስነካም ማለቱ ዳባት እንደቀድሞ አይደለችም፡፡ ገበሬው ሳይቀር የከተማው ነዋሪ ጡሩንባ እየነፋ የክተት ጥሪ አውጇል፡፡ ትንሽ ትልቁ ሁሉም ነቅሎ በመውጣት ቁጣው አደገኛ ደረጃ ደርሷል፡፡ መንገድ ተዘግቷል የአስተዳር ፅ/ቤት ተቋረጠ ለስብሰባ የመጡ የመንግስት ባልስልጣናት በዱላና ድንጋይ አባሯል፡፡ ዳባት በዚህ ሰዓት በፌደራል ፖሊስ ከተማዋ እየታመሰ መሆኑ #በኢሳት ራዲዮ እየተሰማ ነው፡፡ ነዋሪው በቃ.መሮናል ከዚህ በላይ አንፈልግም አንገሸገሸን በማለት እንደ ቃብቲያ ቆርጦ መነሳቱ በዳባት ውጥረቱ እየተገለፀ ይገኛል። ጉድ በል ዳባት !!
Friday, 10 June 2016
Thursday, 9 June 2016
Breaking news
የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የክልሉ የግብርና ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ጀማነህ ታሰሩ
የቀድሞው የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የክልሉ የግብርና ቢሮ ኃላፊ በዛሬው ዕለት አስቸኳይ ስብሰባ ባደረገው የጨፌ ኦሮሚያ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ከተደረገ በኋላ በደብረ ዘይት በክልሉ ፖሊስ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል። ዘላለም ስልጣናቸውን ያለአግባብ በመጠቀም የግል ሀብታቸውን በህገወጥ መንገድ ሲያካብቱ መቆየታቸውን የክልሉ የፀረ ሙስና ኮሚሽን ማስታወቁን ፋና አትቷል ።
Wednesday, 8 June 2016
11% economic growth Vs reality in Ethiopia
እነዚህ ፎቶዎች የተነሱት በባህርዳር ከተማ ድባንቄ መድሃኒያለም ቤ/ክ አካባቢ በሚገኝ የአትክልት የቆሻሻ መድፊያ ቦታ ላይ ነው። ከሰቆጣ በድርቁ ምክንያት የተሰደዱ ዜጎች ከእንስሳቱ ጋር እየተጋፉ የማንጎ ትራፍራፊ ሲለቅሙ ይታያል። ፎቶዎችን ለላኩልን ወገኖች ምስጋናችንን እንገልጻለን።
ሰበር ዜና ( breaking news)
ዳባት ዛሬ በተኩስ ስትናወጥ ዋለች። የከተማዋን ትራንስፎርመር ነቅለው ወደ ትግራይ ክልል ለመውሰድ የተደረገውን ሙከራ ህዝቡ እርምጃ ወስዶበታል። ትራንፎርመሩን የጫነው ከባድ ተሽከርካሪ ተቃጥሏል። ዳባት ማምሻውንም በውጥረት ላይ ነች። መንገዶች ተዘግተዋል። የከተማው ታጣቂ ሃይል ከአቅሙ በላይ በመሆኑ ፌደራል ፖሊስ ገብቷል።
Tuesday, 7 June 2016
አቶ ሃብታሙ አያሌው በእስር ቤት የገጠመውን ልብ የሚነካ ሁኔታም ተናግሯል::
በቅርቡ ከእስር የተፈታው የቀድሞው አንድነት ፓርቲ አመራር አቶ ሃብታሙ አያሌው እስር ቤት እያለ በደረሰበት እንግልት በደረሰበት ህመም የተነሳ ለህክምናው ወጪ በሚል በዘ-ሐበሻ አዘጋጆች አስተባባሪነት በድረገጽ; በአዲስ ድምጽ ራድዮና ሕብር ራድዮ ድጋፍ የገንዘብ ማሰባሰብ ተደርጎ ነበር:: ኢትዮጵያውያን ይህን ጥሪ ከመላው ዓለም ተቀብለው $23,344 በኢንተርኔት አዋጥተው ለሃብታሙ አያሌው ጤናው እንዲመለስለት ተመኝተዋል:: ሃብታሙ የተዋጣለትን ገንዘብ ሰሞኑን ከተቀበለ በኋላ ከሕብር ራድዮ ዳይሬክተር ሃብታሙ አያሌው ጋር ልዩ ቃለምልልስ አድርጎ ሕዝቡን አመስግኗል:: በእስር ቤት የገጠመውን ልብ የሚነካ ሁኔታም ተናግሯል:: ያድምጡት – ሼር ያድርጉት::
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/61743