የህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ የብሔራዊ መረጃ ስብሰባ ያደረገ መሆኑን መረጃዎቻችን በርግጠኝነት ተናግረዋል -
” የአርበኞች ግንቦት 7 የስለላ መረብ እንዴት ከዉስጣችን ሊገባ ቻለ? የሚለዉ ትልቅ መነጋገሪያ የነበረ ሲሆን
” በተለይ የኤርትራዉ የጸጥታ ሐይል ሐላፊ መያዝ ክፉኛ አስደንግጧል!
” በተለይ የኤርትራዉ የጸጥታ ሐይል ሐላፊ መያዝ ክፉኛ አስደንግጧል!
እነዚህንና መሰል የተዛመዱ ጉዳዮችን ሰብሮ መግባት በሚያስችል መልኩ ልንበለጥ የቻልነዉ በምን መልኩ ነዉ? በገንዘብ አቅም? ወይስ እርስ በእርሳችን ባለመተማመን? ወይስ ደግሞ የርበኞች ግንቦት 7 ስለላ መዋቅር ነዳፊዎች በደርግ ሰልጥነዉ የነበሩ የመረጃ አካላትን ለማካተት በመቻሉ? አለበለዚያስ ከአርበኞች ግንቦት 7 ጀርባ ሌሎች አካላት ስለ አሉ? በሚሉ አጣብቂኝ ጥያቄዎች ዙሪያ ከፍተኛ ስብሰባ የተደረገ ሲሆን። በመጠይቆቹ ዙሪያ የተለያዩ አስተያየቶች ተሰንዝረዋል በተለይም ከሰሜን ክፍል የመረጃ አባላት የተሰነዘሩ ነጥቦች እንደጠቆሙት . . . ዛሬ የምናወራዉ ብቻ ሳይሆን የምንበላዉና የምንጠጣዉ ሁሉ በጠላቶቻችን የሚታወቁ ሆነዋል!!! የኤርትራዉ ጸጥታ ሐይል በቁጥጥር ዉስጥ እንዲዉል በግንቦት ሰባት የቀረበዉን ማስረጃ ኤርትራ ተቀብላዋለች። በዚህም ምክንያት ምን ማድረግ አለብን የሚለዉ ነዉ አፋጣኝ መልስ ማግኘት ያለበት፤ ግንቦት 7 የኤርትራ መንግስት ቀኝ እጅ በመሆን ታማኝነቱን እያስመዘገበ ነዉ የሚገኘዉ።
እራሱ የኤርትራ ህዝብ ሁሉ ለዚህ ድርጅት ድጋፉን እየሰጠ ይገኛል አርበኞች ግንቦት 7 የተባሉ ቡድኖች ወያኔን ብቻ ማስወገድ ነዉ አላማችን የኤርትራ ህዝብ በነጻነት እስከዘላለም ይኖራል እያሉ ነዉ የሚሰብኩት!! ስለ ዉህደት እየሰበኩ አይደለም ፖለቲካ የሚሰሩት። በማለት ብዙ ብዙ የዘበዘቡ ሲሆን በአጠቃላይ የዚህ ስብሰባ መሪ የነበሩት ግለሰብ ከኤርትራዉ የጸጥታ ሐይልች ጋር ግንኙነት አላቸዉ የተባሉ ማንኛዉም ንክኪዎች እንዲጸዱ የሚል ማሳሰቢያ አሳልፈዋል።
መላ ቅዱሱ በጠፋዉ በዚህ ግምገማ አይሉት ጥናት ወይም የጥያቄና መልስ ስብሰባ ላይ ከተሳተፉት ጥቂት ግለሰቦች መካከል የወያኔን ዉድቀት በማፋጠን ስራ ላይ የተሰማሩ ዉስጣችን የተኮለኮሉ አካላት መጣራት አለባቸዉ እጅግ የተቸገርነዉ እዚህ ዉስጥ ነዉ በማለት እርስ በእርስ ያለመተማመንና ያለመግባባቱን የሚያጧጧጡፍ ንግግር ከሰብሳቢዉ በኩል ተሰንዝሯል።